Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum



Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: Unable to travel to Wollega, journalists are forced to use satelite data to invesigate massacre

Post by Revelations » 07 Jul 2022, 19:24

THREAD: ሰኔ 11 እለት በጊምቢ ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹዓን አማራዎች በግፍ ተጨፍጭፈዋል። በአከባቢው ባለው የድህንነት ስጋት ጋዜጠኞች እስካሁን ድረስ ወደ ስፍራው ማምራት አልቻሉም። ከሩቅ ባደረግነው ምርመራ ተጨማሪ መረጃ መሰብሰብ ችለናል።





ታጣቂዎቹ በቶሌ ቀበሌ የሚገኙ 5 መንደሮች ላይ ወንድ ሴት የ15 ቀናት እድሜ የነበራት ህጻናት ሁሉ ሳይለዩ ህዝብን በጥይት፤ በስለትም ገድለዋል። ቤቶች ተዘርፎ ወድመዋል። ከጥቃቱ የተረፉት አሁንም ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ይሄ ሁሉ ግፍ እንዴት ተፈጸመ የሚለውን ይበልጥ ለመረዳት ወደ ስፍራው ማቅናት ይጠበቅብን ነበር። የድህንነት ስጋት ባይኖርም እንኳን ነጻ ፕሬስ በነጻነት በማይንቀሳቀስበት ሃገር ቶሌ ድረስ ሂዶ ምርመራ ማካሄዱ ለግዜው የማይታሰብ ነው።

ጉዞውን በሳተላይት ማድረግ ነው ያለን አማራጭ። የ @sentinel_hub ሳተላይት ምስል በመጠቀም ቦታውን ለመዳሰስ ስንሞክር ግን ለግዜው የክረምት ዳመና አከባቢውን ሸፍኖታል። ጥቃቱ ከተፈጸመ ከሳምንት ቦኋላ የተወሰደ ምስል ነው።



ሌሎች አማራጮች አሉ። በቶሌ ቀበሌ በርካታ ቤቶች፤ መስጊድም ሳይቀር በእሳት መጋየታቸውን ሰምተናል። የእሳት ቃጠሎ ለመከታተል ናሳ ያሰማራው የራሱ "ፊርምስ" ተብሎ የሚጠራ ሳተላይት የመጠቀም አማራጭም አለ።



አብዛኛዎቻችን የአከባቢው ተወላጅ ባለመሆናችን በቶሌ ቀበሌ እነ "ስልሳሰው" ተብሎ የሚጠሩት የአከባቢው መንደሮችን መለየት ላይ እንቸገራለን። ሆኖም ግን የናሳ መረጃን በመጠቀም ቃጠሎ የፈጸመባቸው ቦታዎችን መለየት ችያለሁ። ተመልከቱ...



ለተቃጠሉት ስፍራዎች ስም ባይኖረን ከናሳ coordinates በመሰብሰብ መንደሮቹን መለየት ችለናል። ጉግል ማፕስ ላይ ሞልተናቸው ቦታዎችን በቅርብ እንመርምራለን። ከGoogle Earth የተወሰደ ምስል ነው፤ ቃጠሎ የገጠማቸው አከባቢዎችን በምልእክት ለይቻለሁ።



በጨቆርሳ የነበሩት ከጥቃቱ የተረፉትን ሳነጋግር ታጣቂዎች መኪና ይዘው እንደነበር አካፍለውኛል። እንግዲህ ተመልከቱ። ያለው ነገር ሲጣራ በእሳት የጋዩት መንደሮች በሙሉ በሃገር አቋራጩ የA4 አስፋልት መንገድ የምንደርስባቸው ናቸው እና...



ይሄ ውድመት የገጠመው አንዱ አከባቢ ነው። የነዋሪዎች ቤት፤ የንግድ ተቋማት፤ የእርሻ መሬት ያለበት ቆንጆ መንደር ትመስላለች። ይሄኔ ብዙዎች ተገድሎባታል :( መንደሩን ለ2 የምትሰነጥቃት መንገድ አዲሳባ እና ጋምቤላን የሚያገናኛቸው መንገድ ነው።



ይሄ ሌላኛው ነው። ከአገር አቋራጩ የA4 መንገድ በጥቂት መቶ ሜትር የምትርቅ ጫካ እና መኖሪያ ቤቶች ያላት ናት። በእርሻ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ይሆናሉ። የነዚህ ቤት ነዋሪዎች የገጠማቸው ሳስብ ይጨንቀኛል። ስንቀጥል...



ከነዚህ መንደሮች ውጪ ሰው አልተገደለም ማለት አይደለም። እሳት የተነሳባቸው ብቻ ናቸው የለየናቸው። በየ ጫካውም የሰው አስክሬን ተገኝቷልና እነዚህ ካርታዎች ሙሉውን የግድያው ስፍራ ላያሳዩ ይችላል። በአካል ሄዶ መጎብኘቱን የሚተካው ነገር የለም።

ለምሳሌ፤ የቶሌ ነዋሪዎች "ጨፌ" የተባለ ጫካ ላይ በርካታ ሴቶች ተወስደው መገደላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። አከባቢውን በደንብ የሚያውቅ ሰው ምናልባት ጨፌን ሊለይልን ይችል ይሆናል።

የእሳት ጋይታ የተከሰተባቸው መንደሮች መካከል የ4 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት አለ። ታጣቂዎች በነጻነት መንቀሳቀሳቸው የሚያሳይ ነው። ከተደበቁበት ጫካ ወጥተው ድንገተኛ ጥቃት ፈጸሙ ብለው መግለጫ ያወጡ መሳሳታቸውን ያሳያል።

[ Image]https://pbs.twimg.com/media/FXFHzVBXgAE ... ame=medium[/image]

ታጣቂዎቹ ቀኑ ሙሉ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ነፍስ ሲያጠፉ፤ ቤት ሲያቃጥሉ፤ ውለው ከርመው ለነዋሪዎቹ የደረሰላቸው አልነበረም። አከባቢውን ለመጠበቅ የተመደበ የክልሉ መንግስት ሚሊሻ ሰኔ 11 አንድ ሁለት ቀናት ሲቀረው አከባቢውን ለቅቀው ወጣ።

የንጹዓኖች እልቂት ለ8 ተከታታይ ሰዓታት ያለማቋረጥ በሚከናወንበት ግዜ በግምቢ ከተማ ከስፍራው በመኪና የግማሽ ሰዓት ርቀት ላይ የነበረው የወረዳ ፖሊስ እና የክልሉ ልዩ ሃይል ንቅንቅ አላለም።



እሺ የክልሉ ፖሊስ ምናገባኝ አለ እንበል። በነቀምቴ ከተማ ዙሪያ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ሃይል የአንድ ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ የማንን ጎፈሬ ሲያበጥሩ ነበር? ያውም በአስፋልት መንገድ። ቀበሌው በፖሊስ እና በወታደር ተከብቦ ነው ሰው ያለቀው።



በአከባቢው የስልክ እና የኢንተርነት መስመር ባለመኖሩ እነኚህ ሃይሎች መረጃው ቆይቶ ነው የደረሳቸው የሚሉ ይኖራሉ። ከጥቃቱ አምልጠው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ሄደው የድረሱልኝ ጥሪ ለፖሊስ፤ ለመከላከያ ለአክቲቪስት ሁሉ ሳይቀር ያደረሱ አሉ።

የፌዴራል እና የክልል ሃይሎች የ30 ስከ 60 ደቂቃ ቅርበት ላይ በተመሸጉበት የታጣቂ ሃይሎች በመኪና ተጭነው አስፋልት መንገድ ዳር ያሉ መንደሮች ገብተው ለ8ተከታታይ ሰዓታት ሰው መጨፍጨፉን....ያለ ምንም ዋስትና ያደርጉታል ብሎ ማመኑ አስቸጋሪ ነው!

የሳተላይቱ ዳሰሳ የሟቾቹን ቁጥር አያረጋግጥም። ስለ ታጣቂዎቹ ምንም መረጃ አይሰጠንም። ቅድም እንዳልኩት በዓካል ሄዶ ምርመራ ማድረጉን የሚያክል ነገር የለም። ቢሆንም ያለው መረጃ ብዙ ነገር ግልጽ ያደርጋል....

1 በግብር ከፋዩ የሚደገፈው የሃገራችን የድህንነት ሃይሎች ለግብር ከፋዩ ደንታ
እንደሌላቸው ግልጽ ነው (እስካሁን ግልጽ ያልሆነለት ካለ ማለት ነው)።

2 ዶክተር ሀንጋሳ አህመድ የተናገሩት ነገር ውሸት ነው ለማለት እየከበደን ነው።



በፖለቲካዊው ትንቅንቅ አዛውንቱ እስከ ህጻኑ ሁሉ ህይወቱ የሚቀጠፍበት ሃገር። ቦታውን ተመልከቱት። ለህይወታቸው ዋስትና እንጂ ነዋሪዎቹ ችግኝ አላጡም ነበር። ምን ዋጋ አለው...ይሄን አይቶ ቢያንስ በሞቱበት የችግኝ ጥላ አለ የሚሉንም አይጠፉም።




N.B....whole thing will be tweeted in English, today or tomorrow. That's not an issue. I just felt that this needed to reach Ethiopian audiences first and foremost.

Revelations
Senior Member+
Posts: 34573
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

Re: Unable to travel to Wollega, journalists are forced to use satelite data to invesigate massacre

Post by Revelations » 07 Jul 2022, 19:37

It's nice to know this cruel jock of fascist Abiy will be incorporated in the news.



Post Reply