Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Horus » 13 Jun 2022, 15:19

በሚቀጥለው አመት ጂቡቲና ኬኒያ ስንዴ ከኢትዮጵያ ይገዛሉ ። በሚቀጥለው 3 አመት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የምግብ ነጻነት ታገኛለች! የምግብ ነጻነት የሌለው ሕዝብ የፖለቲካ ነጻነት ሊኖረው አይችልም!

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Ethoash » 13 Jun 2022, 19:42

አንድ እርምጃ ወድ ፊት ሁለት ወድ ዋኋላ ማለት ይህ ነው። እንዴት ተደርጎ ነው የዲዘል። የናፍጣ የሚስራ የኤሌትሪክ ሀይል አብይ የሚያስገባላቸው።

በሚቀጥለው ስንዴ ተመረተ ብለው እልልልል ብለዋል። ነገ አዋሽ ይደርቃል ፣ ትልቅ ሰህተት ነው በመስኖ ማልማት የቀረ ቴክኖለጂ ነው ። ወሃውን ያባክናል ጨዋማ መሬቱ ያረገዋል። ይህ ብቻ አየደለም በመስኖ ከዚህ በፊት በትግሬዎቹ ዘመን መጠቀም ተጀምሮ ነበር ብዙ ሐይቆች ደርቀዋል እሪ ለማን ይባላል።

መስኖ ቀርቶ በእንጥባጤቤ መስኖ ተጠቀሙ ማንን ጎዳ ይህን ማለት


who killed solar pump

DireTube News - Ethiopia's leap toward solar energy

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Horus » 13 Jun 2022, 20:23

Ethoash

Why do you rush to critic and belittle everything? Do you that that is a type of psychological illness? Ethiopia has massive amount of rainwater than can be collected in artificial lakes. Ethiopia has rivers after rivers that all years round and in fact carrying away Ethiopian soil to Sudan and Egypt which we can use for any kind of irrigation. Ethiopia has many lakes that can used doing dry season and that fill up during winter. Ethiopia has massive under water we can pump out and use. Ethiopia has massive amount of wind, sun, natural gas, and even petroleum. snap out of your Tigrean mindset. No, your job in Tgray is not trying to cute by carrying guns and issuing fake reality to the world. You need to restore your soil, your vegetation, your air, and your water. Just forget about these other parts of Ethiopia. They are taking off. Period!

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Ethoash » 14 Jun 2022, 10:41

እኔ አንዳንዴ ይገርመኛል ስው እንዴት እንደሚያስብ፣ እኔ ብቻ ነው የመለስኩልህ ያንተን ስንዴ ንዛዜ ምን አርግ ብለህ ነው የምትነዘንዘኝ። ወይስ ማንበብ አትችልም ። አዎ ኢስ ስጥቻለሁ ደግሞም መፍት ሄውን አቅርቤያለሁ። ኢስ ብቻ አቅርቤ ዝም ብል ኖሮ የምትለው በተገባኝ ነበር።

ደግሞ አንተ ምን አገባህ ብክልልህ ብለኸኛል። በሁለት ቢላዋ መብላት አትችልም የመለስን ክልል ሳትደግፍ ስለክልል መናገር አትችልም እኔ ይህንን መልስ የምስጠው ላንተ ብዬ ሳይሆን ወይም ያንተ ትላቻ ፈንቅሎኝ ሳይሆን ወገኖቼ በረሃብ ሲያልቁ ዝም ማለት ስለማልፈልግ ነው። በቦረና ፣ በሱማሌ ከብት እያለቀ ነው። ለምን ብትል ወሃ ስለጠፋ ፣ ወሃው የጠፋው ደግሞ ከብቶቹ ስለበዙ ሳሩን ግጠው ስለጨረሱት ነው ። መሬቱ በሙሉ አዋራ በአዋራ ሆኖዋል በንፋስ አዋራውም ተጠርጎ ይሄድና እወነተኛ በረሃ ይሆናሉ አንዴ ለም የነበሩ መንደሮች ለዚህ ውሃን አቅሮ የመያዝ ዘዴ፣ የዝናብ ውሃ የማቆር፣ የስራ እና የሀገሬዎችን የዛፍ ዝሪያዎችን መትከል። የድንጋይ ግድብ መማረግ ወንዞቹ በፍጥነት አይጎረፉ መሬቱን እንዳይሽረሽሩት ፍጥነቱን መቀነስ ወዘተ ዜዴዎች ተጠቅሞ የመሬት ለምነት ማስጠበቅ ይቻላል።

ነገር ግን አሁን ወንዝ አለን ተትረፈረፎዋል ብለን በመስኖ መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። ስለዚህ መፍት ሄው የጠብ ጠብ መስኖ ነው። የውሃ ፓንፕንም በሶላር መጠቀም አለብን ። የዝናብ ወሃመ ማቆርያ መስራት አለብን ያለውን ማባከን አይደለም ለምን ቢባል በአዋሽ ወንዝ ከአስር ሚሊዬን ስዎች በላይ ያርሱበታል ታድያ ለሁሉም እንዲበቃ መቆጠብ አለብን ባይ ነኝ።

ግብፅ እኮ ኢትዬዽያ ግድብ አት ስራ የሚሉት ውሃው ይቀንስብናል ብለው ነው። ብዙ ቦታ ግብፆች መሬታቸው ከጨዋማነት በመጠቃት ፣ የመሬቱ ለምነት በመቀነሱ እኮ ነው ስንዴ ከውጭ የሚያስገቡት ። አሁንም አላውቁበትም ውሃ በነፃ የተገኝ በጣም ያባክናሉ ። ታድያ ግብፅ አባከነች ተብሎ እኛ ማባከን አለብን ወይ። ግብፅ ውስጥ የቤት የመጠጥ ውሃ ቆጣሪ የለውም ማለትን ስምቻለሁ በጣም ነው የሚያባክኑት። ወሃ እንኩዋን ብሮራቸው የውሃ ጡር አለ እኮ።


Haramaya:ሐይቅ የደረቀው በወተር ፓንፕ ምድረ ገበሬ ሲያለማ ማንም ለወንዙ ጥንቃቄ አላረገም ስለዚህ ሐይቁ ድረቀ ታድያ የሀራማያ ዩኒቨርስቲ ጥናት አርጎበት ወሃው እንዲመለስ ሆኖ ነበር ግን ወድያው ገበሬዎቹ የለመዱትን ፓንፕ አውጥተው በመስኖ ማልማት ጀመሩና ሀይቁን እንደገና አደረቁት።

በደቡብ ሱማሌና በቦረና የከብት እልቂት ቪድዬ መለጠፍ አልፈለግሁም በጣም ይስቀጥጣል ስለዚህ በዚሁ ተረዳ ብዬ ነው። የሐረማያን ብቻ የለጠፍኩልህ ግዜ ወስደህ ተመልከተው።



this boat guide cry for Harmamaya lake .... he knows the value of the lake.. he cry his heart out watch it until the end..

Abere
Senior Member
Posts: 15502
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Abere » 14 Jun 2022, 11:21

ስለ ዓለማያ ሀይቅ መድረቅ እና የገበሬዎች የውሃ እጥረት ስጋት ሊያሳስብ የሚገባ ጉዳይ ነው። ለገፀ-ምድር ውሃ መቀነስ በርካታ መንስ ዔዎች ሊኖሩ ይችላሉ - ለምሳሌ አሁን በሰፊው እያከራከረ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ ሲሆን ሌላው ደግሞ የልማዳዊ አጠቃቀም ችግር ነው። ልማዳዊ የአጠቃቀም ዘይቤ በተለይም የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሂድ ተጽ እኖ ሊፈጥር ይችላል። ይህ ችግር በዓለማያ ሀይቅ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሃይቆችም ላይ ችግር እየፈጠረ ያለ ነው። አካባቢን ከመንከባከብ ጋራ ሌሎች አማራጭ የውሃ ሃብት ምንጮችን ማፈላለግ ተገቢ ሊሆን ይችላል። በእርግጥ ኢትዮጵያ በርካታ የዝናብ እና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብት አላት - ይህን ሃብት በዘመናዊ ቴክኖሎጅ እና ሰው ሃይ በመጠቀም አገልግሎት ላይ ማዋል ነው። በበሬ ብቻ ማረስ እና በክረምት ዝናብ ብቻ የማምረት ባህላችን መሻሻል አለበት። ለዚህ ደግሞ አገራችን ሰላም እና መረጋጋት የማስፈን ስራን ቅድምያ ለማከናወን የሚያስችል ቅን የፓለቲካ መዋዕል ማፍሰስ አለባት። ፓለቲካው ሊያሰራ፤ፈጠራ ሊያሳድግ እና ሃብት ንበረት ለማፍራት ዋስትና መስጠት መቻል አለበት። እስከ አሁን ያለው ሁኔታ ትርምስ ነው - ዝርፊያ- ኬኛ ወዘተ ነው። ዛሬ የዓለማያ ሀይቅ መድረቅ ብቻ ሳይሆን የሚያስለቅሰው፤ ንጹሃን ወጥተው መግባት ሳይችሉ ተገድለው መንገድ ላይ ስለመጣላቸው፤ ታፍነው ስውር ቦታ ስለመዘጋታቸው ጭምር ነው።

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by Ethoash » 14 Jun 2022, 12:02

በጣም ለማከብረውና ለምወደው ወድ ወንድማችን አቶ አቡዋራው። እንደምን ስነበት ህ ። እዚህ መድረክ ላይ መጥተህ ምስክረነት ህን ስለስጠህ በጣም ነው የማመስግንህ።

ነገሩ በጣም ቀላል ነው እኮ። እስራሄሎች ዜዴውን አግኝተውታል የእንጥብጣቢ መስኖ ነው መልሱ። ለምን ብትል የውሃ ፍላጎቱን በዘጠና በመቶ ይቀንስልሀል ።

ሁለተኛ ደግሞ ሳር መትከል ነው ምንም አይነት ተገላጭ መሬት እንዳይኖር ሳር መትከል ነው። ከዚያም የሀገሩን ዛፎች አራብቶ መትከል ነው።

ሶስተኛ ደግሞ ወንዞችን በሙሉ በሼክ ዳም ። ፍጥነታቸውን እንዲቀንሱ ማረግ ነው። በክረምት ጎርፉ ሞልቶ አፈሩን ጠራርጎ እንዳይወስደው የድንጋይ ክምር አርገህ መሀል ላይ ትደረድረዋለህ ታድያ ወሃው ፍጥነቱን ከመቀነሱ በላይ አፈሩ እዛው ግድቡ ስር ቀርቶ የተጣራ ውሃ ከካቡ ድርድር ያልፋል ውሃው ፍጥነቱን ሲቀንስ የጉድጎድ ውሃን ይሞለዋል ማለት ነው አካባባው በሙሉ እርጥበት ይኖረዋል ማለት ነው። ይዚህ የድንጋይ ካብን ጥቅም ዘርዝሬው አልጨርስም።

አራተኛ ጉድጋድ መቆፈርና ውሃው ከተራራው ላይ ሲመጣ እዚያ ጉድጋድ ውስጥ ገብቶ ፍጥነቱን ለመቀነስ ይረዳል ከዚያም ቁጥቆጦ መትከል ነው። እንዴ ሕዝብ በዘመቻ ውጥቶ ይህንን መስራት አለብት።

አምስተኛ፣ ለዘለቀታዊ ውጤት ተራሮቹን በግለስብ ባሌቤትነት አዛውሮ የምርት ትክሎች በመትከል ተጠቃሚ ይሆናል ዛፍ ጥድ የመሳስሉትም ቢተከሉ እንዳይቆረጡ በመክላከል ለስላሳ አመት ጠብቆ ያቆያቸዋል ይህ ማለት ለሳንቃ ምርት ድረሱ ማለት ነው የዛፎቹ ባለቤቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ

ስደስተኛ አውሎ ንፏስ ተነስቶ አቡዋራውን ሲያስነሳው ሴጣን ነው የሚሉትን ፈሊጥ አቆመው ። ይህ ወድ በረሃነት የመቀየር የመጀመሪያው ምልክት ነው ልክ ክረምት ሲገባ ሳር መትከልና አቡዋራውን ማቆም ይቻላል። ያለበለዚያ አቡዋራው ከቦነነ ወድ በረሃነት ነው የምንቀየረው።

ስባተኛ የውሃ ፓንፕ በሶላር እንዲስራ ማረግ ነው።

ስምንተኛ ሀይቁን የአሳ ምርት ማምረት ነው።

ስጠኝ። ቆሻሻ ወንዝ ዳርቻም ይሁን ሐይቅ ውስጥ የሚጥሉ በወንጀል እንዲቀጡ ማረግ ነው።

አስረኛ ለህብረተስቡ ይህንኑ ትምህርት መስጠት ነው። ቆሻሻን የሚጥሉትን ማጋለጥ ነው።

አስራ አንደኛ ። የተፈጥሮ ኮምፖስቶችን ማምረት ነው።

አስራ ሁለተኛ ፣ ባዬ ጋዝ ማምረት ነው። ይህ ጋዝ ለምግብ ማብስያ ስለሚጠቅም እንጨት ምቁረጥ ይቀራል ። ይህ ካልሆነ ግን እንጨት አትቁረጡ ብቻ ማለት ሞኝነት ነው።

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13262
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ስንዴ የዘመናችን ወርቅ! ኢትዮጵያ 5.1 ሚሊዮን ቶን ታመርታለች! የዘመኑ ቅኔ፣ የበጋ ስንዴ !!!

Post by DefendTheTruth » 15 Jun 2022, 13:58

Horus wrote:
13 Jun 2022, 15:19
በሚቀጥለው አመት ጂቡቲና ኬኒያ ስንዴ ከኢትዮጵያ ይገዛሉ ። በሚቀጥለው 3 አመት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ የምግብ ነጻነት ታገኛለች! የምግብ ነጻነት የሌለው ሕዝብ የፖለቲካ ነጻነት ሊኖረው አይችልም!
ወይ ጉድ፣ በዬት በኩል ነዉ ዛሬ ከ አልጋህ ላይ የተነሰሃዉ?

Post Reply