Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42983
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአቢይና ኡሁሩ ኩርፊያ፡ በአገሩ ውስጥ ደካማ መሪ በውጭ ጉዳይም ደካማ ነው!

Post by Horus » 12 Jun 2022, 03:09

የኬናው ኡሁርና የአቢይ ግልጽ የሆነ ይፋ ጠብ እጅግ አደገኛ ነው። በአቢይ አህመድ ላይ ካሉበት ችግሮች ምናልባትም እግጅ ግዙፉ ሊሆን ይችላል ። መጀመሪያ የግጭቶቹ ዝርዝር እንመት ።
(1) አቢይና ኡሁሩ እንደ ግለሰብ ጥሩ ኬሚስትሪ የላቸውም ። ኡሁሩ የጆሞ ኬኒያታ ልጅ ስለሆነ እራሱን እንደ ኬኒያ መስፍን አድርጎ ይመለከታል። አቢይ የኢትዮጵያዊ ኩራት ጋር ስለ ሚቀርበው የሁለቱ ሰዎች ፐርሶናሊቲ እንደ ኮሬንቲ የሚባርቁ ናቸው ።

(2) አቢይ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ቀንድና የአፍሪካም መሪ አደርጋታለሁ እያለ የተናገረው ለኬኒያ በፍጹም አልተዋጠላትም። ኬኒያ እራሷ የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ሃውስ ነኝ ብላ የስበት ማዕከል ለመሆን አሜሪካና አውሮፓን (የቅኝ ጌቶቿን) ተማምና የአቢይን አምቢሽን እማክሸፍ እየሰራች ነው።

(3) በዛሬይቱ ጥቁር አፍሪካ እንደ ኬኒያ ያለ የነጭ አሽከር፣ ያውሮፓና አሜሪካ ሰላዮች ማዕከት እንደ ኬንያ ያለ አገር የለም ። ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ወዳጅ አገሮች ምስራቅ አፍሪካ ሳይሆን ምዕራብ አፍሪካ የሆኑት ። ይህ ዩጋንዳን ታንዛኒያን፣ ሩዋንዳ ሁሉ ያካትታል። በዚህ ላይ የሱዳንና ግብጽ ጨዋታ አለ።

በሌላ ቋንቋ አሜሪካና እንግሊዝ ኢትዮጵያን የሚጎዱበት እና የአቢይ አላማ የሚያክሽፉበት ትልቁ ፕሮክሲ ኬኒያ ነች፣

(4) በኦሮሞ ጎሳና በኩኩዩ ጎሳ መሃልም እንዲሁ ቅራኔ እየበቀለ ነው ። የኬኒያ ኦሮኦሞች ሙስሊሞች ናቸው፣ እንደ ሉዎ ጎሳ ማለት ነው ። ኬኒያን ያለ ማቋረጥ የሚገዙት ኩኩዩ ናቸው ። አሁን ኦሮሞች የምስራቅ አፍሪካ ጎሳ ነን የሚል ጉራ አዘል ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨታቸው የኢትዮ ኬኒያ ነገር አካሮታል።

ብቻ ምን ያደርጋል ከሩጫ ጀምሮ እስከ ኢኮኖሚ እድገት፣ ከ አካባዊው መሪነት ጀምሮ እስከ አፍሪካ መሪነት ሁለቱ አገሮች ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ።

(5) የሁለቱ አገሮች ድምበር ጉዳይ፣ የኦነግ ጦር ካምፕ በኬኒያ ያለው፣ የሶማሌ አል ሻባ ወዘተ የመሳሰሉ ሌሎች ችግሮች አሉ።

ይህ ሁሉ እንደለ ሆኖ የአቢይ ትልቅ ችግር ከራሱ ሕዝብ ጋር የገባው አለመታመን፣ ድጋፍ መጥበብ፣ ያገሪቱን የጎሳ ችግር መፍታት አለመፈልግ ሌላው ትልቁ የድክመቱ መሰረት ነው። የኦርሞ ዶሚኔሽን እንኳን ኢትዮጵያዊያን ኬንያም ፣ ዩጋንዳም፣ ሩዋንዳም አይፈልጉትም።

ስለሆነም በራሱ ሕዝብ ገሸሽ ሲደረግ ያየው ኡሁሩ አቢይን አለቅጥ እየናቀው ነው ፣ ይህ ጥሩ አይደለም ። አቢይ በዝናና መወደድ የሚገፋ መሪ ስለሆነ ለሞራሉ ጥሩ አይደለም ።

ዞሮ ዞሮ የሁለቱ ሰዎች ኩርፊያ መነሾ (1) በካባቢው ሃያል ማነው ? (2) ማነው ይበልጥ የበለጸገና የስበት ማዕከት? (3) ማነው ከኔና አንተ ይበልጥ ዝነኛ? (4) የክብርና ማንነት ግጭቶች ናቸው

ለዚህ በእኔ እምነት አቢይ አህመድ ለግዜው አፍሪካን የመምራቱን ምኞት ገታ አድርጎ በኢትዮጵያ የሚጠየቁትን ሪፎርሞች አምጥቶ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የሚደገፍና የሚወደድ መሪ መሆንን ማስቀደም አለበት ። የውጭ ፖሊሲ የውስጥ ፒሊሲ ነጸብራቅ ነው ። አቢይ ፈረሱን ሳይሆን ጋሪውን ነው ያስቀደመው!


Right
Member
Posts: 4882
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የአቢይና ኡሁሩ ኩርፊያ፡ በአገሩ ውስጥ ደካማ መሪ በውጭ ጉዳይም ደካማ ነው!

Post by Right » 12 Jun 2022, 03:45

Abiye as an incapable leader. The expectation was enormous at home and abroad when he assumed power 4 years ago. Quickly the world noticed he is an incapable leader and lost respect. As far as domestic politics is concerned, obviously he wants to continue the TPLF ethnic policy which by all means was designed to divide and rule. He failed to contain or destroy the TPLF. The latest news is that he is negotiating with the same group he designated as a terrorist. That is not only a big failure but it is also dangerous. The diplomatic failure doesn’t need any explanation. Over a year Sudan is occupying a massive land and engaged and planned in a long term farming.
No nation would have tolerated this kind of aggressions. This would never have happened under Derg or the Weyannies. The Sudanese also noticed how he handled the war with a TPLF, a sieged rag tag army with less human and material resources.
Abiye is a dead man walking.

Horus
Senior Member+
Posts: 42983
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የአቢይና ኡሁሩ ኩርፊያ፡ በአገሩ ውስጥ ደካማ መሪ በውጭ ጉዳይም ደካማ ነው!

Post by Horus » 12 Jun 2022, 12:52

ኬኒያ የአሜሪካ ብቻ ሳይሆን የግብጽም ፕሮክሲ ነች

Post Reply