ሆረስ፥Horus wrote: ↑02 May 2022, 13:54ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝብ የገጠማቸው የእውቀትና ባህል ችግር እጅግ ግዙፍ ነው ። በዚህ አለም ላይ ተፈጥሮ ወይም ኔቸር የሚባል ነገር አለ። ይህ ሰው የሰራው፣ ሰው የፈጠረው አለም አይደለም። ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ የተፈጥሮ አለም ውስጥ ስለሚኖር የፍጥረትን ጸባይ ማወቅ ግድ ይለዋል ። ከተፈጥሮ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር አለበት ። ያ ካልሆነ ሰው እራሱ ይጠፋል።
ሁለተኛው አለም የሰው ልጅ እራሱ የፈጠረው ካልቸር ወይም ባህል ይባላል። ለምሳሌ መኪና፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ዶሮ ወጥ እና ቀሚስ የሰው ስራዎች፣ የሰው ባህል፣ የሰው ካልቸር ናቸው። ሌላው ትልቁ እና አደገኛው ሰው ሰራሽ ነገር ሃሳብ ወይም እምነት ነው። ለምሳሌ አለምን (ኔቸርን) የፈጠረ እራሱ ፍጥረት ሳይሆን አላህ ነው፣ እግዚአብሄር ነው። ጎድ ነው። ጌታ ነው። ያዌ ነው፣ ቡድሃ ነው፣ ዋቃ ነው፣ ወዘተ የሚባሉት የሰው ሃሳቦች ናቸው ። እነዚህን ሃሳቦች የፈጠረው ሰው እራሱ ነው።
በአንድ ቃል እምነት ወይም ሃይማኖት ካልቸር ነው፤ ባህል ነው በቃ! የሰው ልጅን ውድቀት እያስከተለ ያለው የዘመናት ስህተት የሰው ልጅ ኔቸርና ካልቸርን ለያይቶ፣ አንዱ ካንዱ አቃርኖ፣ አንዱ ያንዱ ጠላት አድርጎ የሚደመድም ደደብ ሃሳብ መፍጠሩ ነው። ይህ ልክ እነ ዴካርት የሰው አካልና የሰው አይምሮ የተለያዩ ነገሮች ናቸው፣ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው እንዳሉት ማለት ነው።
የሰው ልጅ አለምን አልፈጠረም። የሰው ልጅ እራሱ በተፈጥሮ የተፈጠረ ነገር እንጂ እራሱ ሕይወትን የፈጠረ ሃይል አይደለም። ካልቸር ወይም ባህል የሰው ልጅ ከፍጥረት የኮረጀው ሞዴል ነው ። ፈረስ አራት እግሮች ስላሉት ሰው አራት ጎማ ያለው መኪና ሰራ። የሰው ችሎታ ተፈጥሮን መኮረጅ ነው። የሰው ልጅ የተፈጥሮን አመክኞ ምን እንደ ሆነ አያውቅም። ፈረስ ለምን አራት እግር እንዳለው አያውቅም።
ስለ እምነትም፣ ስለሃይማኖት፣ ስለሌላ አለማዊ፣ ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና መለኮታዊ ነገሮች ሁሉ ያለው ግንዛቤ ተመሳሳይ ነው። በኮረጃቸው ነገሮች ያምናል። ያን እምነት ሃሳብ የለዋል። ያን እምነት ስለደጋገመው፣ ደጋግሞ ስላመነው እውቀት ይለዋል ። የሰው ልጅ በራሱ ካልቸር፣ በራሱ ባህል፣ በራሱ ሃሳብ ታስሮ ተቀፍድዶ በራሱ እስር ቤት ውስጥ የሚማቅቅ አሳዛኝ እንሰሳ፣ አሳዛኝ ፍጡር ነው ።
ኢትዮጵያዊያን የጎሳ እምነት፣ የሃይማኖት እምነት፣ የካልቸር እምነት ሁሉም ሰው ሰራሽ ባህሎች፣ ሰው ሰራሽ አርቲፋክቶች መሆናቸውን እስካልገባቸው ድረስ ከዚህ የአመጽ መከራ ሊላቀቁ አይችሉም። ምክንያቱም ካልቸር የአንድ ሰው ማንነት አይደለም። ካልቸር የአንድ ሰው ምንነት አይደለም ። ባህል ወይም ካልቸር የሰው ተግባር፣ የሰው ስራ፣ የሰው ስነምግባር ነው እንጂ የሰው ምንነት አይደለም። ሰው ምንድን ነው? ሲባል መልሱ ሰው ተፈጥሮ የሰራው እንሰሳ ነው ። የሚያስብ እንሰሳ ነው ። ካልቸር፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ ዘፈን፣ ሃሳብ ምንድን ነው? ሲባል መልሱ የሰው ስራ፣ የሰው ተግባር፣ የሰው ቢሄቪየር ነው ።
ታዲያ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸው በሰሩት እምነት፣ እራሳቸው ባመኑት እምነት፣ እራሳቸው በፈጠሩት ባህል እርስ በርሳቸው ሲተላለቁ፣ ሲሰቃዩ፣ ሲሰደዱ፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲያለቅሱ ከማየት የበለጠ ምን የሚያሳዝን፣ ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሰው ሰራሽ ባህል ተከፋፍለው እንዲህ ሲፋጁ ማየት የሰዎች የማሰብ ችሎታ ዝቅጠት ብቻ ሳይሆን እራሱ የባህሉ፣ የእምነቱ፣ የሃይማኖቱ ደካማነትን ያሳያል። ኢትዮጵያዊያን ከዚህ የጭለማ እምነት ወጥተው ወደ ብርሃን ሃይማኖት ካልገቡ የነገ ሕይወታቸው የመከራ ዘመን እንደ ሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው!
ይህን ጥልቅ ማስተዋል እና ትንታኔ ኣንብቤ ሳስታዉስ ሰነበትኩ። ኣሁን ፈልጌ ኣገኘሁት።
የሰዉ ልጅ የፈጠረዉን ቆም ብሎ ማስተዋል የነበረዉን ያስታዉሳል፣ ወደ ፊት ያሳያል።
እኔ ስለዚህ ርዕስ በቂ ትምህርት እና ዕዉቀት የለኝም። ለማወቅ ጥረት ማድረጉ ኣብሮኝ ሰንብቷል። የእኔ የኢትዮጵያ ህዳሴ የሰነበተ ደወል ስለዚህ መሰረታዊ ርዕስ ነዉ።
የእድሜ ባለፀጋ ለመባል የበቃሁ ይመስለኛል። ባህልም የእድሜ ባለፀጋ ነዉ መባል የሚችል ይመስለኛል። ከዚህ ኣንፃር የኢትዮጵያ ባህል ትልቅ የእድሜ ባለፀጋ ነዉ መባል የሚቻል ይመስለኛል። ይህ በብዙሃን ኣልተስተዋለም ማለት ከሌሎች ኣንፃር ሲታይ ፀጋዉ ብዙ ጉድለት ኣለዉ ማለት የሚቻል ኣይመስለኝም።
ትልቁ ጉድለት የምለዉ በብዙሃን ኣለመስተዋሉ ነዉ። በ1983 (እ ኢ ኣ) ኣከባቢ የማስታዉሰዉ ኣንድ የኦቦ ሌንጮ ለታ የቭኦኤ ቃለ መጠይቅ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ሆኖ ነዉ እንጂ በዛን ወቅት ኢትዮጵያ ዉስጥ የበዛ እልቂት ሊከሰት ይችል ነበር የሚል ኣይነት ነበር።
የህዝቡ ባህል ግዝፈት ከነፃ እንዉጣ ማስተማር የገዘፈ የነበረ ሆኖ ይሁን?
ከወራት በፊት ድፌንድዘትሩዝ (ማን እንደሆነ ኣላዉቅም) እዚህ ፎረም ላይ ተደራጁ የሞል ምክር ጽፎ ሳየዉ ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ የተደራጃ ኣለ ወይ ብዬ ዝም ኣልኩኝ። ምክንያቱም ህዝባችን በባህል እንደ ቤተሰብ፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ፣ በነገድ፣ በደቦ ጭምር የተደራጀ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። ስለዚህ እጥረቱ መደራጀቱ ላይ ነዉ ወይስ ዉጤት ማምጣቱ ላይ ነዉ ብዬ ራሴን ጠይቄ ዝም ኣልኩኝ።
ከዓመታት በፊት ከኣንድ ጓደኛዬ ጋር የሃይማኖት ዉይይት ጀመርን። አንድ ቅጽበታዊ ቃላቶቼን ኣልረሳቸዉም። እንካፓስቴቲ ስ ጎዸ ኣልኩኝ። እንካፓስቴት ያደርገሃል ማለት ነዉ። እኔም ኢቶንግልሽ እናገራለሁ። ሆሌ ባይሆንም። I remember it as one of my spontaneous outbursts. The strong reaction I got was that the complexity of human biology can not be explained without leaving it to God. I stand to be corrected if I misheard or misunderstood that strong reaction to my spontaneous outburst.
ከዛ ከዓመታት በሁዋል ልያጫዉተኝ ጠይቆ ብቅ ያለ እንግዳ ስለ እግዝኣብሔር መንግስት በዉስጥህ መሆን ስንኝ ልያስተምረኝ ዳዳ። ኣዉቀዉ ስለነበረ መለስኩለት። ከዛም የኣዉሮፓ ትራንስፎርሜሽን እና እድገት የመጣዉ ያንን ከተገነዘቡ በሁዋላ ነዉ የሚለዉን ሊጨምርልኝም ዳዳ። ያም ኣንብቤ ኣስተዉዬ የነበረ ነዉ።
ማስተዋል ብቻ ሳይሆን ስለርዕሱ እዛም እዚህም ስቀባጥር ሰንብቻለሁ። ካልዘነጋሁ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ የተለያየ ጊዜ እዚህ ፎረም ላይ ስታስተምር ስለዚህ ርዕስ ኣንስቻለሁ። ኣሁን ኣንስቼ ነበር ለማለት ሳይሆን የርዕሱ ቁምነገርነት የበለጠ እንዲስተዋል ተጨማሪ ከሆነ ብዬ ነዉ።
ስለዚህ ርዕስ ኣንድ ቁልፍ ግንዛቤ ነዉ ብዬ የማስበዉ ዋቅን ኡማ ዸ የሚል ነዉ። ትርጉሙም ዋቃ ተፈጥሮ ነዉ ማለት ነዉ። የማክበር እና መስገድ ልዩነት ማስተዋልም ይህንን ቀልፍ ግንዛቤ ከማስተዋል የሚመጣ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ። እስከዛሬ ነበርሽ እንዴ የሚሉ ለዚህ ኣይኖቻቸዉን መጀመርያ ከከፈቱ።