1h ·
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጀኔራል ያሳር ጉሌር (General Yaşar GÜLER ) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑክ ቡድን የቱርክ መንግስት ባዘጋጀው የEFES 2022 ሚሊተሪ ኤክሰርሳይስ ላይ ለመሳተፍ ቱርክ ገብተዋል።
ከዝግጅቱ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በተጨማሪ በአቅም ግንባታና ወታደራዊ ድጋፎች በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
