የአብይ የሰጠው አንዳንዶቹ ገለጻዎች ጥልቀት ያላቸው ሌሎቹ ደግሞ ማንም ቅን አሳቢ ሰው ሊገልጻቸው የሚችል በሰፊው የሚገልጹ በተለመዶ የሚዘዋወሩ እውቀቶች ናቸው ፤ ባጠቃላይ ጥሩ ሀሳቦች ናቸው በዚህ በኩል ምንም ብዙ ሂሶች ማቅረብ አይቻልም ፤ የአብይ ትልቁ ዲፊሲት ተግባር ላይ ነው በተለይ ደግሞ በጎሳ ትብታብ ውስጥ ገብተው ትክክል ማየት ላቃታቸው የጎሳ እውሮች ይህንን መደስኮሩ ፤ ይህንን ቁምነገር ሳይገነዘቡት ቀርተው ሳይሆን ያላቸውን ቦታ በእውቀት ሳይሆን በጎሰኛነታቸው ያገኙት ስለሆነ አሁን የሚያደርጉትን የማግለልና የማሰወገድ ዘመቻ ልክ እንደ ስራ ዋስትና ስለሚቆጥሩት አሁን ስብሰባው ጨርሰው ሲሄዱ የዛው የወንጀል ስራቸው ላይ ነው የሚዘፈቁት ፡፡
አብይ በዋናነት የሚያሰወግዳቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው ፤ አንደኛ የፌደራል ስርአት አረዳዱ በጣም የተንሸዋረረ ነው፤ የፌደራል መንገስቱ ጣልቃ አይገባም 100% ማለት ምን ማለት ነው? ፌደራል ማለት ኮንፌደሬት ማለት አይደለም፡፡ የፌደራል መንግስቱ የኢትዮጵያዊን ዜጋዎች ላይ ጥቃት ከደረሰ የተባለው የፌዴሬሽኑ ስቴት የኢትዮያዊን የመከላከል ፍላጎት ወይም ችሎታ ከሌለው የፌደራል መንግስቱ የመግባት ግዴታ አለበት፤ በአሜሪካን ፌደሪሸን ህግ በተለያዩ ስቴቶች ማህከል የሚካሄዱ ንግዶች ነጻ እንዲሆኑ ሀላፊነት ተስጥቶታል ፤ ስለዚህ አንድ ስቴት ንግዱን የሚያስተጓጉል ህግ ቢያወጣ ፌዴራል መንግስቱ ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤት ወስዶ ህጉ እንዲወድቅ ያደርጋል ፤ ለምሳሌ የደቡብ የአሜሪካ ስቴቶች ትምርትቤቶች ጥቁር ተማሪዎች ከነጮች ጋር አብረው ይማራሉ ብሎ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲወስን ተቃውሞ ሲያደርጉ የፌደራል ወታደሮች ገበተው ነው ህጉ እንዲፈጸም ያደረጉት ፤ ስለዚህ በፌደራል አደረጃጀት 100% የሚባል ነገር የለም ፤ ይህንንም አብይ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፤ ለምን እንዲህ እንደሚል ግን የአራት አመት ስራው በማየት መረዳት ይቻላል ፡፡
ሌላው ደግሞ ህግን ማስከበር ላይ ያለው በጣም መሰመር የለቀቀ ወንጀለኛ በሚያሰደርገው ደረጃ ያለው አመለካከት ነው፤ በየአካባቢው የሚደረጉት ህገ ወጥ የመንገስት የጸጥታ አስከባሪዎችን ስራ ከማውገዝና እንደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሁሉም አስተዳደሮች ህግ የማስከበር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የሞራልም ፤ የአስተዳደርም መመሪያ ከመስጠት ወንጀል የሚያበረታታ አመራር የሚስጥ ነው የሚመስለው ፤ እኔ ሀላፊነቴን እንደጠቅላይ ሚንስቴር እየወጣሁ ነው በአካባቢ ያሉት” “ሚሊሻዎች መሪ አይደለሁም” ፤ “ ተመልከቱኝ እኔ የምኖርበት በተመንግስት አካባቢ የሚኖሩትን እያፈናቀልኩ አይደለም “ በአጭሩ በየአካባቢው ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች ህግን የማስከበር ሀላፊነትም ግዴታም አለባቸው ብሎ ሊተወው ይችል ነበር ፤ መሪዎች ሁሉም ቦታ መገኝት የለባቸውም ግን ያላችውን ጠንካራ አቋም መግለጽ ለሁሉም የመንግስት ስራ አስኪያጆች ትክክለኛና የማያወላዳ መልከት መላኩ በቂ ነው ፤ ግን እንደዚህ አይነት ፎሽፋሻ መልክት በመላክ በመንግስ ውስጥ ያሉ ዱርዬዎች ወንጀላቸውን እንዲቀጥሉ አርንጓዴ መብራት እያሳየ ነው ያለው፤
ሌላው ደግሞ በአማራና በኦሮሞ መሀከል ጉልበት የለሽ ገላጋይ መስሎ የሚቀርብበት ዘይቤ ነው፤ እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ሁሉም ግዛቶች ላይ የበላይ ቦታን ይዞ እየመራ ያለ ሰው ነው ፤ ሁሉም ላይ ተጸእኖ አለው ፤ ስለዚህ ማተኮር ያለበት ምን ፕሪንሲፖል ኢትዮጵያዊያንን መምራት እዳለበት፤ በዚያም መሰረት እንዲተባበሩ ተጽእኖ ማሳደር ነው፤ እርግጥ ነው ኢትዮጵያ የሁለቱ ብቻ አይደለችም ግን ሁለቱን በፕሪንሲበል ተባብረው እንዲሰሩ ካላደረገ መርከቧ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረጋ አችልም ፤ ስለዚህ ምንም ችሎታ እንደለለው ከመመሰልና ሲያሰኘው ደግሞ መወገኑን በግጽ እያሳየ ጉልበት እንደሌልው ሆኖ መቅረግ ተገቢ አይደለም ፤
የህግ የበላይነትን ማስከበር 50% በላይ የኢትዮጵያን ችግር ያሰወግዳል ፤ የህግ አስፈጻሚው ከፖለቲካ ነጻ መሆኑን በህዝቡ ዘንድ ታእማኔነት እስካገኝ ድረስ ፤ ለምሳሌ ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም የአለፈው ምርጫ ተቀባይነት ያገኝበት ምክንያት ታእማኔ ሁኔታዎችን መፍጠር ስለተቻለ ነው ፡፡ አብይ ተግባር ፤ እስካሁን የተናገርካቸውን እሩቡን እንኳን ተግባር ላይ በታውል ትልቅ የተሳካለ መሪ መሆን ይችል ነበር ፤ ግን ንግግሩና ተግባሩ _ ፊየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲ ሆኖ ህዝቡ አመኔታ ካጣ ቆይቷል፡፡
Re: የአብይ ንግግሮች አራምባ የአብይ ተግባሮች ቆቦ
TGAA
አንተ የምትለው አይነት ስልጣንና እምነት ያለው ፌዴራል መንግስትማ ኢጎሳዊ የሆነ በጎሳ ክልል ያልቆመ እና በጎሳ መብት ሳይሆን በግለሰብ መብት ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝም ቢሆን ነበር። በቃ የኢትዮጵያ ቅርቃር ያ ነው። ይህ የጎሳ እስትራክቸር ቢያንስ አሜንድ እስካልተደረገ ድረስ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ኢትዮጵያ አይኖራትም። ያ ወያኔ ሆን ብሎ የሰራው ነው ። አቢይ ይህን ለማፍረስ ይችላል ወይ? መርጠው እዚያ ያስቀመጡት የጎሳ መብት አስከባሪዎች ናቸው ። በእኔ እምነት ለየት ያለ የሃይል አሰላለፍ ተፈጥሮ የጎሳ ከበርቴውን የሚነቀንቅ ሃይል ሲፈጠር ብቻ ነው ።አቢይ አሁን እያደረገ ያለው የጎሳው ፌዴርዝን በማሽሞንሞን 'ህብረ ብሄርዊ' እናደርገዋለን የሚል ነው ። አሁን ያሉት ብሄረ ሰብ መንግስታት በሆነ ሞቲቬሽናል ንግግር ተደምረው 'ህብረት' ይሆናሉ ነው የሚለው ። ባንድ ቃል ሬቮሉሽን ፍሮም አበቭ የሚባለው አይነት ሙከራ ነው የያዘው ። ምናልባት ይህን ሊያሳካ የሚችለው ጠንካራ ከጎሳ ውጭ ካሉ የዜጋ ሃይሎች ድጋፍ ጠይቆ አላያንስ ከፈጠረ በጎሳ ከበርቴዎች ላይ ሚዛን ሊወስድ ይችላል። አለዚያ በነሱ ድጋፍ ላይ ቆሞ ሺ ግዜ ትሬኒንግ ቢሰጣቸው በጎሳቸው ውስጥ የያዙትን ስልጣን በቀላሉ የሚለቁለት አይመስለኝ። ይህን ሁሉ የምለው እሱ የምር ጸረ ጎሳ ፖለቲካ ከያዘ ማለት ነው። ይህ ለመሆኑ ሙሉ ማረጋገጫ የለንም ። ለዚህ ነው ጥሩ ሲሰራ እየደገፍን በተበላሸው የምንተቸው !

@TGAA
The biggest failure of Abiy is caused by the following:
1) purposeful denial of the crisis
2) his partiality to his base tribe
3) his misguided thought that he can change things by doing things by himself
4) his zero knowledge about system management
@Horus
I agree on the fact that only a radical change of thoughts can help get out of the the current impasse. Abiy gives more weight for the extension of his power base rather than the people and the country. He has zero knowledge about system management. የሞራል ልእልናውን ያጣ ካለፉት መሪዎች ሁሉ የወረደ ውዳቂ ነው

Abiy lacks the character to be a leader of a complex country like Ethiopia. He is a good sales person but inconsistent, pathological lier, chamelonic, not trustworthy, dictator, too shallow ( lacks depth), may be controlled by Isaias or/and Arabs.
Re: የአብይ ንግግሮች አራምባ የአብይ ተግባሮች ቆቦ
አቢይ አህመድ ትሁት በመሰለ ባህሪ ውስጥ እብሪት ወይም አሮጋንስ ያለው መሪ መሆኑን እኔ ያስተዋልኩት ገና ስልጣን ላይ እንደ መጣ ነበር። ግን ወጣት ስለሆነ እኛ በዚያ እድሜ ተመሳሳይ ባህሪ ስለነበረን ሲስተም ውስጥ ገብቶ ሲታሽ ሚዛን ያገኛል የሚል እምነት ነበርኝ። እኔ ለአቢይ ምሬትና ጥላቻ አይደለም ያለኝ፤ ከፍዬ የቀጠርኩት ሰው ስላልሆነ ቁጣና መራር ጥላቻ እኔን እንጂ እሱን አይጎዳውም ስለምል እዚያ አልሄድም።
እኔ አቢይን ሆነ ብዬ እንዴት እንደ ሚያስብ እከታተላለሁ። አቢይ በቅርብ የሚያዳምጣቸው የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ፣ ቢሄቪየራል ኢኮኖሚክስና አዲስ ዘመን (ኒው ኤጅ) ህሳቤ ጉሩዎች በዙሪያው አሉ ብዬ አምናለሁ። ለምሳሌ በአጭር ማሰብና በረጅም ማሰብ፣ ቅርብ ማሰብና እሩቅ ማሰብ፣ ሎካል ማሰብና ግሎባል ማሰብ፣ በፍጥነት ማሰብና በዝግታ ማሰብ የሚባሉ አሁን ትልቅ ፋሽን ውስጥ ያሉ የህሳቤ ሞዴሎች ናቸው አማካሪዎች በያሉበት የሚቸረችሩት ። ሞዴሎቹ መጥፎ ናቸው ለማለት ሳይሆን እንደ አይዲዮሎጂ ሲወሰዱ አደጋ ያመጣሉ ። ምክኛቱም ሁሉም ሃሳብና ርዕዮቶች ስለሆኑ።
ከላይ ባሉት ሞዴሎች መሰረት (ለምሳሌ ዳንኤል ካህንማን ኖቤል ሽልማት ያገኘበት ማሰቢያ ሞዴል) ፈጣን ህሳቤ፣ በፍጥነት ማሰብ ወደ ስህተት ይወስዳል፤ ዝግ ብሎ ማሰብ ቢዘገይም ከስህተት ያድናል የሚል ነው ። አቢይ በትክክል ዝግ ብሎ ሃሳቢ ነው ። ሌላው ባጭር ማሰብና በሩቅ ማሰብ ነው። ባጭር የሚያስቡ ስለ ዛሬ፣ ስለ ወቅቱ ፣ ወራቱ ችግር የሚያስቡ የሩቁን ስለማያያዩ ወሎ አድሮ ስህተት ያስከትላሉ ። በሩቅ የሚያስቡ ጊዜይዊ ችግር አይፈቱም፣ ግዜያዊ ቀውስ ማኔጅ ማድረግ ተቀዳሚ ትኩረታቸው አይደለም። እነሱ የሚያስቡት የረጅም ያምስት፣ ያስር ፣ የ20 አመት ጉዳይ ነው ።
አቢይ አህመድ ክላሲካል ትግተኛ አሳቢና በረጅም አሳቢ ነው ። ስለሆነም ዛሬ ስለሚደረጉ ግጭቶች፣ ሁክቶች፣ መፈናቀሎች፣ ጩሀቶች ትኩረት አይሰጥም። ኢትዮጵያ ሁልግዜ የቀውስ የክራይሲስ አገር ስለሆነች አቢይ ደሞ ክራይሲስ ማኔጅመንት የሚፈልግ የሚወድ ሰው ስላልሆነ በትክክል የህዝብ ኤክስፔክቴሽን እና ያቢይ ቢሄቪየር ተቃራኒ ናቸው ፣ በኦፖዚት አቅጣጫ ነው የሚጓዙት ። ያቢይ አንጎል እንዴት እንደ ሚሰራ ማወቅ የሚፈልጉ ከላይ የስቀመጥኳቸውን ሞዴሎች ያጥኑ እላለሁ !