Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Assegid S. » 27 Apr 2022, 10:11

or1 wrote:
27 Apr 2022, 05:09
slowly the truth is coming out
ወይዘሪት (ወ/ሮ) ቤተልሔም ታፈሰ ከ fundamental journalism principles በተፃራሪ ባላት ዘረኛ ምልከታ የተነሳ ብዙም ባልከታተላትም፥ በእኔ አይን ግን ከባድ ሚዛን ፖለቲከኞች ናቸው ወይም ነበሩ የምላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ በቁጥር ኣራት የሚሆኑ ቃለመጠይቆቹዋን በሚገባ ተመልክቻለሁ። የዚህ አስተያየቴ ትኩረት ደግሞ ጋዜጠኛዋ ሳትሆን በቅርቡ እንግዳዋ ሆነው የቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ ይሆናሉ። በእርግጥ ለመናገር፦ በቃለ-መጠይቁ ቆይታቸው … የቀድሞው ባለስልጣን የጋዜጠኛዋን ድብቅ የብሔርተኝነት ወጥመድ በማምከኑ ረገድ የተዋጣላቸውና በሳል ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

ያ አጠቃላይ ግምገማዬ ሲሆን፥ ለዚህ thread ልመዘው የፈለኩት የአባ ዱላ ገመዳ መልስ ደግሞ … ዘር በ DNA የሚታወቅ ነገር አይደለም፤ ኣንድ ሰው የኣንድ ዘር ክፋይ መሆኑ የሚታወቀው ለዛ ማህበረሰብ በሚያከናውነው መልካም ተግባር እንጂ ገላው ተቆፍሮ በሚመረመር ደም አይደለም … የሚለው ምልከታቸውም ነው። ይኽን እኔም ቀድሞ ብየዋለሁ፥ አሁንም ሙሉ በሙሉ እስማማበታለሁ። ይሰማል በድኑ ብአዴን?!

ስለዚህም፦ እከሌ የእንትን ዘር ነውእንትና ከእንትን ወገንና ትውልድ ናት የሚለው ሐሳብ ሁሌም ያስቀኛል። በተለይ ደግሞ በዚህች ምድር ላይ የሌለን ግለሰብ በማንሳት የእንትን ዘር ነውNo! አይደለም! ከእንትን ነው የመጣው … ብሎ መከራከር ፍፁም ሊገባኝ የማይችል የሞኞች ለቅሶ ነው፤ የሚደጋገም። አሁን ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ሰው እንደ አልዓዛር መቃብር ቆፍሮ ወጥቶ ለዛ ማህበረሰብ የሚያበረክተው አንዳች ፍሬ ላይኖር፥ የእንትን ዘር ነውNo የእንትን ነው ብሎ መከራከር ጥቅሙ ምንድነው? Nada!

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጣም ቆየት ያለ ጊዜ የሰማሁትን ቀልድ መሳይ ቁምነገር የአስተያየቴ መቋጫ ላድርገው።

ሁለት የማይተዋወቁ ግለሰቦች (ኣንድ ጣልያናዊና ኣንድ የእስራኤል ዜጋ) የጠርሙስ ህይወት በኣንድ ባልኮኒ ላይ ያገጣጥማቸውና ጨዋታ መሰል ነገር ይጀምራሉ። በጊዜው የሮማው ፓፓስ John Paul I ነበሩና … ጣልያናዊው ከጎኑ ለተቀመጠው እስራኤላዊ፦ "የዓለም የካቶሊክ እምነት መሪ፣ የሮማው ፓፓስ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?” ሲል ይጠይቃል። እስራኤላዊውም "አላውቅም" ሲል መለሰ። ጣልያናዊውም “John Paul I ይባላል" አለው። እስራኤላዊው አመሰገነ። ወዲያውም አስከትሎ ጣልያናዊው መሸተኛ፦ "የ ጆን ፖል ኣንደኛ ዜግነት ምን እንደሆነ ታውቃለህ?” አለው፤ እስራኤላዊውም አያውቅም ነበርና “No” አለ። ይኼኔ ጣሊያናዊው በኩራት "የ Italy ዜጋ ናቸው" አለ ልቡን ነፍቶ … በቀኝ እጁ ደረቱን መታ መታ እያደረገ የእኔ ወገን ናቸው ለማለት።

ነገሩ ግን በዚህ አላበቃም፤ ጣልያናዊው እንዳትረሳው ብዬ ነው እያለ በየ 5ደቂቃው እስራኤላዊውን ኣንድ አይነት ጥያቄ እየጠየቀ አሰለቸው። ይኼኔ እስራኤላዊውም በተራው፦ "የናዝሬቱ እየሱስን ታውቀዋለህ?” አለው ... ጣልያናዊውም "አላውቀውም" ሲል መለሰ። እስራኤላዊውም፦ " :mrgreen: "

የቀረውን ታሪክ እናንተው ጨርሱት 8)

Abere
Senior Member
Posts: 15502
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Abere » 27 Apr 2022, 10:58

To validate this claim it is essential to evaluate the chronology of events. Such as;
a) When was St.Yared born
b) When was the Oromo migration to Ethiopia take place?
c) When was the first historical account of Oromo migration written by Aba Bahrey?

If the facts add up, it is worth claim. If the facts do not add up, that is a foolish claim and is an open robbery. As to me St. Yared was born in 505 AD and Died in 571 AD.

Whereas Oromo migrated to Ethiopian in the 16th century. In the period of 1562-1579 the Oromo began migrating to the southwestern region of present-day Ethiopia. And In 1684-1685 Oromo fought against Emperor Iyassu I in Wollo and Gojjam. In 1694 the Gugru-Oromo attacked Gojjam and Bagemder.

Thus, there is no relation at all between Oromo and St. Yared. Oromo came to Ethiopia as pagan, without any religion. They later adopted Christainity and Islam from Amhara and Tigres. የኦሮሙማዎች ነገር ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች ሆነ እኮ። የሚያምር እና ግም ውሸት አለ እኮ። የኦሮሙማዎች ደግም የግም ግም ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Horus » 27 Apr 2022, 13:28

እኔ በእዚህ ንትርክ ውስጥ መግባት አልፈልግም፤ ብዙ ሰዎች ስለ ቋንቋ ምርምር ሆነ ሳይንስ ወይም የቋንቋ ታሪክ እውቀትም ሆነ ክህሎት የሌላቸው በስመ ነጋ በድምጽ መመሳሰል ይህ ቃል እንዲ ከሚል መጣ የሚሉ ምሁራዊ ሃላፊነት የጎደለው ብያኔ ሲያስተላልፉ ኖረዋል። በኢትዮጵያ የቋንቋ እስኮላርሺፕ ውስጥ አንድ ቃል በቅድመ ቅጥያና በድህረ ቅጥያ (ፕሪፊክስ እና ሰፊክስ) ሳቢያ እንዴት እንደ ሚራባና የቃላቶዝ ትርጉም እንጂ ሳይንሳዊ የሆነ የቃላት ስረ ጽንስ (ኢቲሞሎጂ) እና የቃላት ስነ ታሪክ (ፊሎሎጂ) የለም። አንድ ቃል እንደ ማንኛው የሰው ስራ (ካልቸር) ታሪክ አለው ። ማን ጀመረው? ማ ተዋሰው? ማ ምን ጨመረበት? ማ ምን ቀነሰ? ተብሎ የሚሰራ የቃላት ታሪክ አለ። እያንዳንዱ ቃል ከልዩ ልዩ ድምጾች የተፈተለ፣ የተሰውሰው ህንጻ ነው ። በመሆኑም የዚያን ነጠላ ቃል ጽንስና ሽመና አመጣጥ ያላጠና ሰው ዝም ብሎ ተነስቶ በድምጽ መመሳሰል መደምደሚያ መወርወር በኢትዮጵያ እጅግ ግዙፍ የእውቀት ችግር ሆኖ አለ።

ለምሳሌ ከዚህ ቀድም እዚህ ፎረም ላይ እንደ ለጠፍኩት 'ት ስ ዕ ር ' ማለት ማሸነፍ ማለት አይደለም ብዬ ነበር ። 'ጽር' ጥሩ፣ ንጹ፣ ጽራይ ፣ ያስተጸርይ፣ ነጻ ማለት ነው። ስለሆነም ትግራይ ት ስ ዕ ር ማለት ትግራይ ነጻ ትሆናለች ማለት እንጂ ትግራይ ታሸንፋለች ማለት አይደለም ብዬ ነበር ።

ሌላ ምሳሌ ከጥቂት ቀናት በፊት 'አዱሊስ' ስለቢባለው ቃል ታሪክ ውይይት ሲደረግ አንዱ ሰው ይህን ብሎ ነበር ። 'አ' የሚለው የቃሉ ፕሪፊክስ 'አዲ' (ቦታ) መሆን ስለማይችል አዱሊስ የእስሌቮች ቦታ/አገር ሊሆን አይችልም ሲል ድምዳሜ ሰጥቶ ነበር ። ያ ስህተት ነው ፣

ለምሳሌ በጉራጌ የሴም ቋንቋ 'አዝንደ' የሚባል ቃል አለ ። እዚህ ቦታ፣ ይህው እዚህ ፣ ይህውልህ ማለት ነው ። ይህ ቃል ' አ ዘ እንደ (እንዳ) ' ከሚለው የተፈተለ ነው ። ዘንድ ማለት ቦታ ማለት ነው። ዘንድ የመጣው 'ዘ እንዳ' ከሚለው ግዕዝ ነው ። እንዳ ቦታ ነው ። 'ነ' ብዙ ግዜ ቃላት ለማለስለስ የሚጨመር እንጂ የቃሉ ስር ' አዲ' የሚለው ነው ። ስለሆነም 'አ' የሚለው አመልካች ፕሪፊክስ በሴም ቋንቋ፣ በግዕዝም በጥቅም ላይ አለ። በመሆኑም አዱሊስ በሚለው ቃል ውስጥ 'አ' የቦታ አመልካች ሊሆን ይችላል። ይህን መሰል የአንድ ቃል ታሪክና አሰራር ስይመረምሩ የሚነታረኩ ብዙ ተምረናል አውቀናል የሚሉ አሉ ። አትመኗቸው ! እታንዳንዱ ቃል እንደ ባዮሎጂ ጂን ታሪክና አሻራ ወይም የመጣበት ዲካ አለውና!

Abere
Senior Member
Posts: 15502
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Abere » 27 Apr 2022, 15:49

ሆረስ፤

እንደ እኔ ይህ ንትርክ ሳይሆን ሀቁን በማስረጃ በማስቀመጥ የታሪክ ሌባዎችን እጅ ከፍንጅ ማዋል ነው። የህዝብ ታሪክ ሰርሳሪዎች ካልተጋለጡ በስተቀር ውሸቱን ድርቅ ብለው በመደጋገም እውነት የማድረግ ስራ ይሰራሉ። በተለይ ኦሮሙማዎች 24/7 የሚለፉት በአንድ ጉዳይ ላይ ምንም ታሪክ ከሌላቸው ፈጠራ ይሰራሉ፤ የተበለጡ ከመሰላቸው ደግሞ የሌሎቹን ቀምተው እንደምንም አስታከው የእኛ ታሪክ ነው ብለው ድርቅ ይላሉ። መቸም በአንድ አገር ውስጥ ነው ያለነው እያልን ታሪኩ የትም አይሄድም እያልን ዝም ስንላቸው ሜዳ ገብተዋል። ለምሳሌ ስመ ጥሩ ዐርበኞችን እንደ ፊታውራሪ ሃብተ ጊዮርጊስን፤ ባልቻ ሳፎን አገር ያወቃቸውን በድርቅና ኦሮሞ ናቸው ይሉሃል። ሰሞኑን እንኳን ዐብይ አህመድ በቅርብ የምናውቀውን የመሬት ለአራሹ ታሪክ ሙልጭ አድርጎ ሰርቆ ባሮ ቱምሳ የሚባል ኦሮሞ ሰውየ ነው የፈጠረው ብሎን እርፍ አለ። እንደ ሚታወቀው ይህን እንቅስቃሴ የፈጠሩት እና የመሩ እርሳቸው የሰሜን ባለባት አማራ ተማሪዎች ናቸው። እነኝህ ውሸታም ኦሮሙማዎች መከሰት ያስፈልጋል። መከሰት ደግሞ ንትርክ አይደለም - ለእውነት መቆም ነው። አሁን ደግሞ ጭራሽ ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው ሲሉን እየሳቅን ዝም እንበላቸው እንደ። የአገሬ ሰው ሲተርክ ቧልት እና ቅዘን ቤት ያበላሻል ይላል። ኦሮምማዎች ሽቅብ እየቀዘኑ ነው ያሉት - ከላይ እስከ ታች። ቆሻሻቸውን እንድ ገነዘቡ እውነቱን ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው።

ሌላው ስለ ቃላት እና ቃላት መመሳሰል ያልከው በእኔ እይታ ትክክል ነው። ስም ያለው ሞኝ ይሉ ዘንድ ከወያኔ ወድህ ያለው ነገረ-ስራ ይች ስም ትግርኛ ወይም ኦሮምኛ ትመስላለች ስለዚህ ይህ ቀበሌ ወይም መንደር የትግሬ ወይም የኦሮሞ ነው ይሉሃል - ካርታም ይሰራል። የውጭ ስም ያላቸው ቦታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሞልተዋል - እንድሁ በአጋጣሚ እንጅ ከሩስያ ወይም ጃፓን መጥተው ሰፍረው አይደለም። የፈርንጅም የጥቁርም የቻይናም ህጻን አፍ ሊፈታ ሲማር ባባ ማማ ይላል። እነ ጎሰኞች ይህ ህጻን ትግሬ ነው ባባ ይላል አቦይ ነው ሊሉህ ይችላሉ።
Horus wrote:
27 Apr 2022, 13:28
<እኔ በእዚህ ንትርክ ውስጥ መግባት አልፈልግም...>

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Horus » 27 Apr 2022, 16:01

አበረ፣
ያልከው ትክክል ነው፤ ለማለት የሞከርኩት የቅዱስ ያሬድም ሆነ 'ወየነ' የሚለው ቃል ታሪክ ስራዬ ብዬ ያጠናሁት ስላልሆነ እንጂ የእውቀት ሌብነት ሲካሄድማ በማውቀው ነገር ላይ ዝም አልልም። ልብ በል እውቀት ልክ እንደ እቃ ይሰረቃል፤ ለዚህ ነው copyright, patent, logo, etc የተፈጠሩት ።

Abere
Senior Member
Posts: 15502
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Abere » 27 Apr 2022, 16:30

ሆረስ፤

አሁን ግልጽ ሁኖልኛል።ለትውልድ የሚተላለፍ ብቸኛ ቅርስ ታሪክ ነው። እውነተኛውን ታሪክ ጠብቀን ለትውልድ ማስተላፍ አለብን። ቀበኛ ሰርሳሪን ማሳፈር ያስፈልጋል።በእየሩሳሌም ደር ሱልጣን ገዳም ግብጾች ሰላማዊ መስለው ሾከክ ብለው ገብተው ነው ዛሬ የእኛ ነው እያሉ በፈጣጣ ያስቸገሩት። ቀደም ብሎ ያ ትውልድ ቢረዳ የአሁኑ ትውልድ ድንጋይ ሲወራወር አይውልም ነበር። ኦሮሙማዎች የያዙት ነገር በጣም የሚያስጠላ ነው። እውነት ቢኖር እኮ የኢትዮጵያ የሆነው ታሪክ ሁሉ የእያንዳንዱ ዜጋ ነው። ኦሮሙማዎች ቀምተው በሞኖፓሊ መያዝ ነው ዋና አላማቸው።

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Meleket » 28 Apr 2022, 04:00

ወዳጃችን Horus
ቃላት መፍለጥ እንደማይመችህ ብናውቅም፡ እታች ካቀረብካቸው ቃላት ኣኳያ እስቲ እነዚህን ቃላት መርምራቸውና ሃሳብህን ኣካፍለን
ሰዐረ
ሥዑር
ጸዐረ
ጸረየ
Horus wrote:
27 Apr 2022, 13:28
. . . ለምሳሌ ከዚህ ቀድም እዚህ ፎረም ላይ እንደ ለጠፍኩት 'ት ስ ዕ ር ' ማለት ማሸነፍ ማለት አይደለም ብዬ ነበር ። 'ጽር' ጥሩ፣ ንጹ፣ ጽራይ ፣ ያስተጸርይ፣ ነጻ ማለት ነው። . . .
ስለ ኣዱሊስ ያልከውንም Enno Littmann ከጠቆመው ኣባባል ጋር ኣያያዞ ኣንባቢ ግንዛቤ ያገኝ ዘንድ ከምንጩ እዚህ ኣምጥተነዋል
Horus wrote:
27 Apr 2022, 13:28
. . . ሌላ ምሳሌ ከጥቂት ቀናት በፊት 'አዱሊስ' ስለቢባለው ቃል ታሪክ ውይይት ሲደረግ አንዱ ሰው ይህን ብሎ ነበር ። 'አ' የሚለው የቃሉ ፕሪፊክስ 'አዲ' (ቦታ) መሆን ስለማይችል አዱሊስ የእስሌቮች ቦታ/አገር ሊሆን አይችልም ሲል ድምዳሜ ሰጥቶ ነበር ። ያ ስህተት ነው ፣ . . .
Meleket wrote:
25 Apr 2022, 10:05
. . .ይህ ተመራማሪ ምን እያለ ነው፡ እስቲ እንስማው!
From the sea any journey into the interior and to Axum itself had to begin from the port city of Adulis, which lay just a few kilometers inland from the western shore of the Gulf of Zula. It is the very name of Adulis that passed into that of Zula by way of a deformation as Azulis. The etymology of the word Adulis remains a mystery to this day, because it could be either Greek, or Semitic, and there is no way of telling which it is. If Greek, the word would imply, from the privative prefix a-, an absence of slaves (douloi), but such an explanation seems highly implausible. Scholarly efforts to turn the name into a reference to a settlement of former slaves, who, being no longer enslaved, might be said to live in a “slave-less” place, are desperate measures that few have been willing to accept. But if the word is not Geek but Ethiopic, which is a Semitic language, the *ad* element would mean “place,” and that seems much more promising. A tribal designation of some kind might follow, and so “place of the Uli or Ule” may be the answer to this puzzle, exactly as Enno Littmann once suggested.[“The Throne of Adulis, Red sea wars on the eve of Islam, by G.W. Bowersock page 8]
https://www.amazon.com/Throne-Adulis-Is ... 0199739323

:mrgreen:

Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Horus » 28 Apr 2022, 12:52

መለከት፣

እንደ ምታየው 'ሰዐረ'፣ 'ሥዑር' ፣' ጸዐረ' ፣ 'ጸረየ' የሚሉት ቃላት ብዙም በአማርኛ ወይም ጉራጌኛ ውስጥ ስለ ማንጠቀምባቸው ዛሬ ያካባዊው ህዝብ (በትግራይና ኤርትራ) ምን እስፔሲፊክ አጠቃቀም እንዳላቸው ስለማላውቅ የዩዜጅ ስህተት ከሰራሁ አርመኝ።

ለምሳሌ ሥዑር የሚለው ቃል በተለምዶና በጉራማይሌ ርዑስ ከተባለ ራስ የሚል ትርጉም ይወስድና አንዳንድ ሰዎች ዑር ማለት ራስ ማለት ነው ይላሉ።

ከዚያ በተረፈ የላይኞቹ ቃላት ሁሉም ግንዳቸው አንድ ነው ። የሴም ቃል የሆነው 'ዑር' ነው። ሌሎች 'ኧል/ኤል' የሚሉት ነው ። ከዚህ ቀደም እንዳልኩት ትርጉሙ ፀሃይ፣ ብርሃን፣ ምስል፣ እንደ ብርሃን የጸዳ፣ የነጻ፣ ወዘተ እያለ እንደ ሜታፎርና ምሳሌ በብዙ መንገድ ይገለጻል።

ለምሳሌ ጸረየ ነጻ፣ ጸዳ ፣ ወደ ሃይማኖት ከወሰድነው ደሞ ስርየት አገኘ፣ ንስሃ ገባ ወዘተ እያለ ይቀጥላል።

ለምሳሌ ሰዐረ አሁን ምን ትርጉም እንደ ምትሰጡት ባላቅም ዘ አረ ማለት 'ነጻው' ማለት ነው ። አረ ፣ አርነት፣ አርአያ የሚባሉትን ቃላት የሚሰጠን ስረ ቃል ነው ። እንደ ብርሃን ንጹህ የሆነ ከሚለው የተወሰደ ሜታፎር ነው ። አርነት ነጻነት ማለት ነው ። አርአያ ምሳሌ፣ ምስል ማለት ነው ። ምስል፣ ምሳሌ፣ ስዕል ወይም ኢሜጅ ከብርሃን ጋራ እንደ ሚሄድ ከላይ ብዬዋለሁ።

የቀሩትን አንተው ዲኮድ አድርጋቸው መሰረታዊ ሜትዶሎጂውን አስጨብጬሃለሁ! ኬር!

Meleket
Member+
Posts: 5087
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ቅዱስ ያሬድ ኦሮሞ ነው | ወያኔ ወየነ ከሚለው የኩሽ ቃል የመጣ ነው | ቄስ ግርማ ዘውዴ

Post by Meleket » 29 Apr 2022, 04:34

Horus ምልከታህ ግሩም ነው።

የኛ የትግርኛና የግዕዝ ቋንቋ ቁርኝት መቼም ምስክር አያስፈልገውም። ለአብነት የኛዎቹ የኔታዎች ያስጨበጡንን ሓቅ እስቲ ለአንባቢ እናጋራ፤ ቃላቶቹን እንዲህ አድርገው ፈትፍተዋቸዋል፡ ተግዕዙ እያጣቀሱ (ዲ) -ያሉት ከ1865ቱ የዲልማን የግዕዝ መዝገበ ቃላት የጠቀሱትን ነው፡ (ቅዳ) ያሉት ደግሞ ከሥርዐተ ቅዳሴ የወሰዱት መሆኑ ነው። ኪወ ያሉት ደግሞ ከኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበቃላት የወሰዱትን ነው። ቃላቶቹን ከሞላ ጐደል እንዲህ አቅርበዋቸዋል።

ሰዐረ
1. ጣሰ፡ አፈረሰ፡ ቃሉን ኣጠፈ፡ (ዲ-ሰዐረ ኪዳነ ዘኮነ ምስሌሁ ወምስለ አይሁድ። ሰዐረ ሰንበታትየ)
2. አራቀ፡ ኣተረፈ፡ ለቀቀ፡ ሰረዘ (ዲ-ሰዐረ እግዚኣብሔር ኵሎ ኣንብዐ እምኵሉ ገጽ።)
3 .(ከሥልጣን ወይ ሹመት) መሻር፡ ማሰናበት (ዲ-ያነብር ነገሥተ ወይሥዕር)
4. ደመሰሰ፡ ጠረገ (ዲ-እስዕር ትዕቢቶሙ ለኅጥኣን)
5. ተቋረጠ፡ ተሸነፈ፡ እንዲቆም ተደረገ፡ ተሰረዘ፡ ዋጋ ቢስ እንዲሆን ተደረገ፡ ከሸፈ (ዲ-ኢይስዐር እምኔክሙ ገብር)

ሥዑር
ሣር የበዛበት፡ ለም የለማ ( ቅዳ- ውስተ ብሔር ሥዑር ህየ ያኅድረኒ ወኅበ ማየ ዕረፍት ሐፀነኒ)

ሣዕር
1 ሣር ለም (ዲ-ከመ ያብቍል ሣዕረ ገዳም)
2 የሰፌድ እቃ በትግርኛ ዳጉድ፡ መኾምብያ፡ ሰፍኢ የምንለውንም ያጠቃልላል (ሰፌድ ወስከምቢያ እንደማለት ነው)
3. የውሃ ወይ የማር ወይ የወተት መያዣ እቃ (ኪወ- ሣዕረ ማይ። ሣዕረ ሐሊብ)

ጸዐረ
1.ተሠቃየ፡ ሥቃይ ወይ (ዲ- እስመ ጽዕረ ፈድፋደ)
2.አበርትቶና ጠንክሮ በኃይል ሰራ፡ ተጋ
3.አሠቃየ አሳመመ፡ እንዲሠቃይ አደረገ (ዲ -ትጼዕረኒ ልብየ)

ጸረየ(ጸርየ)
1.ነጥሮ ጠራ፡ ነጻ (ኪወ- ከመ ወርቅ ዘይጼሪ እምጺአቱ ይጸርዩ ቦቱ)
2.ንጹሕ ሆነ ጠራ ለኅሊና (ዲ- እምከመ ጸርየት ኅሊና)

ርእሰ፡ ረአሰ
ራስ ሆነ፡ አለቃ ሆነ መሪ ሆነ (ዲ-ረአሰ ውእቱ ለቤተ ክርስቲያን። ተለአኮ ለነግድ ከመ አብርሃም ወተተሐት ለዘትርእስ ላዕሌሁ ከመ ዳዊት)።

ረአስ
አለቃ፡ መሪ፡ የሁሉም የበላይ (ዲ - ረኣሶሙ ለነቢያት)

Post Reply