የመጀምሪያ የእርሻው መስክ ችግር መፍትሄ የመሬት ስሪት ነው ፣ መሬትን ከጎሳ የፖለቲካ ነጋዴው የዘር ከበርቴ ማላቀቅ ነው ።
ሌላው በክልል እስር ቤት የታጠረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እስትራክቸርና የገበያ ሲስተም ነው ። በመሰረቱ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለህዝብ የሚበቃ ሽንኩርት፣ ዶሮ፣ በግና በሬ ጠፍቶ አይደለም ዶር በ1500 ብር የሚሸጠው። ዘፋኟ ጂጂ እንዳለችው ባሌ ያረሰውን ሲዳማ ካልገዛ፣ ጎጃም ያረሰውን ሱማሌ ካልገዛ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ቀልድ ነው የሚሆነው ።
በሌላ አነጋገር የክልል እስር ቤቶች ፈርሰው ኢትዮጵያ አንድ የኢኮኖሚ ሲስተምና አንድ የገበያ ፍሰት እስካልሆነች ድረስ ያቺ አገር የማምረት ብቻ አይደለም ገበያ አይኖራትም ። ድሮ በ1500 የሚሸጠው ሌባ የሰጠው ምክንያት ዶር ካገር ጠፍቷል አላለም፤ ሰላም ስለሌለ ማጓጓዝ አልቻልንም ነው ያለው ።
ሰላማዊ ብሄራዊ ገበያ የሌለው የትግሬ ወያኔ ባቆመው የጎሳ ኤትኖክራሲና የአቢይ መንግስት በተራው በተቀመጠበት የዘር የክልል ኤትኖክራሲ መንግስትና ኢኮኖሚ ስርዓት ሳቢያ ነው ።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስትና ኢኮኖሚ ስርዓት ለጎሳ ከበርቴ፣ ለጎሳ ደላላና ለጎሳ ሌቦች እንዲያገለግል፤ በክልል መንግስት ስም 100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ለመበዝበዝ የቆመ ስርዓት ነው ። ለዚህ ነው ይህ ቆሻሻ የጎሳ ጨረባ ተዝካር እንዳይሻሻል፣ እንዳይለወጥ ጥርስ ነክሰው የሚከላከሉት !
ዝሆኑን በስሙ ጥሩት! የጎሳ ስርዓት ይባላል!!!