
ኢትዮጵያ አንድ አላት አንድ ጀግና፡ አንድ ቅኑ ምርጥ ዜጋ፡ -[ሰሞንኛው ‘ኤርትራዊ’ ግጥም]
በአሉባልተኞች ስሙን ለማጠልሸት የፈጠራ ወሬ ቢንጋጋ፡
በተንኮለኞችና ሴረኞች ደባ፡ ማእከላዊ ውስጥ ቢዘጋ፡
ሁሌ ሚጨልም መስሏቸው፡ ጭራሽ ሌሊቱ የማይነጋ፡
ቅስሙን ለመስበር ትንታጉን፡ የነማሞ ቂሉ ላንቃ ቢያዛጋ፡
ምንም ኣልመሰለውም ያ ኣንበሳ፡ ፍርሃት ልቡ’ጋ ሳያስጠጋ፡
በማግኘትም በማጣትም፡ ሁሌ መንፈሱ የተረጋጋ፡
እርሱን ጠልፎ ለመጣል፡ ሽ መሰናክል ቢዘረጋ፡
“እኔ ኅሊና ኣለኝ” በማለት፡ በንጽሕና የሚፈጋ፡
የዘመኑን ባንክ ቀያሪ፡ ከቆላም ይሁን ከደጋ፡
ኣእምሮውን በኣእምሮው ተቆጣጥሮ፡ ለለውጥ ዘወትር የሚተጋ፡
እውቀት ከችሎታ አጣምሮ፡ ለሃገሩ እድገት ፍለጋ፡
ስንቱን የኔቢጤ ወጣት የታደገ፡ ከሃሳብና ተስፋ ጥውለጋ፡
ኢትዮጵያ አንድ አላት አንድ ጀግና፡ አንድ ቅኑ ምርጥ ዜጋ፡
በልበ ሙሉነት ሓቅ የሚገልጥ፡ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ፡ በእርሱነቱ የማይሰጋ፡
ማነው ብላችሁ አትጠይቁ፡ እርሱ ነው ኤርምያስ ጠቅል ኣመልጋ!!!!
በኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንዲሁም በኤርምያስ ጠቅል አመልጋ አድናቂዎች የተገጠመ ግጥም ነው።
https://addisinsight.net/ermias-amelega ... ix-months/

https://typicalethiopian.com/yemayesebe ... as-amelga/