Debre Tabor University
April 16 at 8:03 AM ·
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሮኬት ሳይንስ ማዕከል በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የተሰየመ ሮኬት በተሳካ ሁኔታ አስወነጨፈ።
***
ዛሬ ሚያዚያ 8/2014 ዓ.ም በአሞራ ገደል አካባቢ በተከናወነው የሮኬት ማስወንጨፍ መርሀ ግብር ላይ የዩኒቨርሲቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ዳይሬክተሮች፣ ዲኖች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሮኬቱን የቴክኖሎጂ ተማሪዎችና መምህራን በጥምረት እንዳዘጋጁት በትግበራው ወቅት ተመላክቷል። ይህ የተሳካ ሙከራ የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ-ሰማዕት መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ የተከናወነ ነበር። የሮኬት ማስወንጨፍ ሂደቱ ብዙዎችን ተጋባዥ እንግዶች ያስገረመ ሲሆን እስከ አምስት ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያላቸው ሮኬቶች በዩኒቨርሲቲው የሮኬት ሳይንስ ማዕከል መፈጠራቸው ተገልጿል።
ነፍጠኞች የተኮሱት ርችት
Please wait, video is loading...
የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የተኮሱት ሮኬት