ዛሬ ለጄኔራል መኮንኖች የሰጠው ስልጠና ብዙ ነገሮችን ያዘለ ነው ።
የመጀመሪያው አቢይ ስለ ሲቪል ሚሊታሪ ግንኙነት ያቀረበው ሞዴል ነው ። በአንድ አገር መንግስት ተዋቀር ውስጥ የሲቪሉ ፖለቲካ ክንፍና የሚሊታሪው ክንፍ ያላቸው ትስስር እና ስልጣን አከፋፈል የሚወስንበት ሞዴል አለ (በፖለቲካ ቲኦሪ ውስጥ)። ሶስቱን አቢይ ጠቅሷቸዋል ።
አንዱ ሞዴል ሚሊታሪው ፍጹም ፕሮፌሽናል ተቋም ስለሆነ የአባላቱ ምልመላና ስብጥር ውስጥ የፖለቲካ (የጎሳ) ስሌት አያገባውም የሚል ነው።
ሌላው ሞዴል ሚሊታሪው ልክ እንደ ብልጽግና ፓርቲ በጎሳ ስሌት መሰረት በማዋቀር ሚሊታሪው የፓርቲው መሳሪያ የሚያደርግ ሞዴል ነው ። አቢይ እነዚህን ሁለት ሞዴል ይቃወማል።
ሶስተኛው ሞዴል አሁን ያለው ያቢይ ሞዴል እሱ ፕሉራሊስት ሞዴል ይለዋል። በዚህ ሞዴል መሰረት የሚሊታሪው ምልመላ ተዋጽኦ የጎሳ ውክልና ታሳቢ ያደረገ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ከብልጽግና ነጻ የሆነ፣ የብልጽግና ታዛዥ ያልሆነ ሚቲታሪ ነው እይተገነባ ያለው ።
ይህ ትልቅ ትልቅ ቁም ነገር ነው።
አቢይ በብልጽግና ፓርቲ ላይ እምነት ቢኖረው ኖሮ፣ ያቢይ ስልጣን መሰረት ብልጽግና ቢሆን ኖሮ አርሚው ለፓለቲካው ፓርቲ ታዛዥና ሚሊታሪው ለፖለቲካ እንዲገዛ ያደርግ ነበር። ያ ያልሆነበት ምክኛት የጎሳ ካድሬዎች በጎሳ ተከፋፍለው መንግስት ማቆም አይደለም፣ መንግስት መምራት የማይችል የጎሳ ጥርቃሞ እንደሆነ አቢይ ያምናል። ስለሆነም ሌቦች ነው የሚላቸው። ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ውስጥ አቢይ በግልጽ ብልጽግና በምንም አይነት ወደ ሚሊታሪው እንዳይደርሱ ሲል ጀነራሎቹን ትዕዛዝ ይሰጣል።
የዚህ ሁሉ ውጤት ምን እንደ ሚሆን መገመት ይቻላል።
አንደኛ ከዚህ በኋላ የአቢይ ስልጣን መሰረት የሚሆነው ሚሊታሪው እንጂ የኦሮሞ ወይም የአማራ ጎሳ ካድሬዎች አይሆኑም። ይህ ብቻ አይደለም። የትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሌላ የጎሳ ጦር ተነስቶ አቢይን ለማውረድ ቢሞክር በፌዴራል ሚሊታሪው ይመታል።
በሌላ በኩል ሚሊታሪው እራሱ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ እንዳያስብ ሚሊታሪው በጎሳ ስሌት ስለቆመ መፈንቅል ማድረግ የሚችል አንድነት ሊኖረው አይችልም ።
ስለዚህ በእኔ እምነት የሚሊታሪው ተጽዕኖ እያደገ ይመጣል፤ የአቢይ ዋና ደጋፊ ሃይል ሚሊታሪው ከሆነ የክልሎችና የብልጽኛ ተጽዕኖ እየቀነሰ ይሄዳል ። ለዚህ ነው አቢይ እራሱ ብልጽግና የሌቦች ድርጅት ነው የሚለው።
ከዚህ መደምደሚያ የሚነሳው አዲስ ጥያቄ አቢይ አህመድ በሚሊታሪው ተደግፎ ወደ አምባገነን መሪነት ያዘምም ይሆን ወይ የሚለው ነው?
