ጉራጌ የኬር ካልቸር ሕዝብ አገር፣ የሰላምና ፍቅር ምድር ናት ። በመሆኑም አስራ አንዱም የጉራጌ ክልል ዞኖች ለእድገት፣ ለመሰረተ ልማት፣ ለዉበት እየተጣደፉ ነው ። ማንም እንደ ሚያውቀው የጉራጌ ክልል በሰለጠነ የሰው ሃይልም ሆነ በኢንቨስትመንት ካፒታል በአጭር ግዜ ውስጥ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የራሱ ተወላጆች ጉልበት አለው ። ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ባለሃብቶችና አለም አቀፍ ግዙፍ ኩባኛዎች ምርምር እያደረጉበት ነው።
በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሳይንስና አርት መመጠቂያ ግዜው እሩቅ አይደለም! በነዚህ መስኮች ሁሉ በቂ ምሁራና ሳይቲስቶች ስላሉን ።
እስከ ዛሬ በእንሰት እና ሌሎች ሆርቲ ካልቸር የሚታወቀው ጉራጌ ዛሬ በእርሻና በእርሻ ሳይንስ እየመራ ይገኛል። ከበቂ በላይ የእርሻ ሳይንቲስቶች አሉን።
በንግድ፣ ሆቴል፣ በእደ ጥበብ፣ በክራፍት እና ባንክ የሚታወቀው ጉራጌ ዛሬ በሁሉም የኢንዱስትሪ መስኮች ከእርሻ እስከ ምግብ ፕሮሴሲንግ፣ ከማዕድን እስከ ብረታብረት፣ ከጨርቃ ጨርቅ እስከ ቆዳ፣ ከፕላስቲክ እስከ ወረቀት፣ ከሲሚንቶ እስከ ግድብ ግምባታ ብቃት ያላቸው ኢንዱስትሪያሊስቶች ባለቤት ነው የጉራጌ ሕዝብ።
በአንድ ቃል የጉራጌ ጠ/ግዛት ሁሉም ለሚመኛት ባለጸጋይቱ ኢትዮጵያ የኢንኩቤሽን፣ የፈጠራና ፍልሰፋ፣ የዘመናዊ ቢዝነስ ጀግኖች መፍለቂያ መሰልጠኛ ት/ቤት እየሆነች ነው ። ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ የጉራጌ ሕዝብ የኬርነት፣ የመልካምነት፣ የሰላም፣ የፍቅርና የቸርነት ሳይኮሎጂና የስራ ክቡርነት ካልቸሩ ነው! ኬይር ማለት በሂንዲ ቋንቋ ደህነንት (ዌል ቢኢንግ) ማለት ሲሆን በኡርዱና አረብኝ መልካምነት (ጉድነስ) ማለት ነው !! በጉራጌኛ መልካምነት፣ ደህነንት፣ መሉነት እና ሰላም ማለት ነው!!!