Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42918
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by Horus » 23 Mar 2022, 14:59

እኔ ሆረስ ቃላት መሸንሸን አይጥመኝም! እቅጩን እነግርህና ስራህ ያውጣህ ነው ምልህ!

አቢይ አህመድ አሜሪካኖች ከስልጣን ሊያነሱት አንድ ሃሙስ ሲቀራቸው መላ ኢትዮጵያን የኢትዮጵያ ባንዲራ አሲዞ ክተት አገር አድን ብሎ ስልጣኑን ባዳነ ማግስት የኢትዮጵያ ዜጋ ሰንደቅ አላማህን ይዘህ ጥምቀት አትወጣም ተብሎ ተገደለ። ከዚያ የላቀ ምን ክህደት ይኖራል! ትላንት ሌቦች የጎሳ ከበርቴዎቹን ሰብስቦ ብልጽኛ ባለ 12 ሚሊዮን ያፍሪካ ግዙፍ ፓርቲ ነን ፣ ከኛ ሌላ የኢትዮጵያ ፓርቲ ላሳር ሲል የመጨረሻ ወያኔያዊ እብሪቱን ላለም አወጀ!

ሞኝና ገንዘቡ አብረው አይቆዩም ይባላል ! ያንድ ጎሳ ግሩፒዝም የሚያስከትለው ዝቅጠት ይህን ይመስላል!

የጎሳ ፖለቲካ ሁሉምንም ይደመሳሳል ስል 30 አመት ሞላኝ! ያ ደሞ ሃቅ ነው ! ልብ በሉ!

ትግሬ ፈርሷል
አማራ ተከፋፍሎ ከፈረሰ ስንብቷል
ኦሮሞ ከላይ እስከ ታች ተከፋፍሎ ሸኔ፣ ኦነግ፣ ፒፒ ተባብሎ እየተዋጋ ነው
ቤኒ ሻንጉል አመጽ ነው
ሱማሊን እንዲሁ ቀውስ ነው

የኢትዮጵያ የጎሳ ከበርቴዎችና የጎሳ ነጋዴ ካድሬዎች አንድ ሙሉ አገር፣ አንድ አገር አቀፍ የጦርነት ፣ አምጽ፣ ሁከትና ቅውስ አውድማ ናቸው ። "ብሄር ብሄርሰብ ሕዝቦች" በጎሳ ፖለቲካ ደቀው በብሄር ጥያቄ ፈራርሰዋል !

ለዚህ ሁሉ ዘላለማዊ ቀውስ መፍትሄ የጎሳን ስርዓት ባስቸኳይ ማፍረስ ነው !!!

ሃቁ ይህ ነው! በቃ ! ዝብዝብ ቢበዛ ባህያ አይጫንም !!


Last edited by Horus on 24 Mar 2022, 01:52, edited 1 time in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by Abere » 23 Mar 2022, 15:25

ዐብይ አህመድ ከኢትዮጵያዊያን ጋር አኩኩሉሽ ጨዋታ እጫዎታለሁ ብሎ በእራሱ ላይ እየቀለደ ነው - ህዝብን ያታለለ መስሎታል። ብሄር፥ብሄረሰቦች፥ ህዝቦች ፥ ቅራቅንቦዎች ወዘተ.. እያላዘነ እንደ ወያኔ እኖራለሁ ብሎ ሰፊ የንጉስ እራት ግብዣ በየዕለቱ ያደርጋል። የ4ኪሎ ቤተ-መንግስት አንድ ቀን ተቀዶ በእራሶ ላይ ዶፍ እንደሚያወርድ አልገባውም። ለነገሩ ከሱሉልታ በፈረስ ዘመዶቸ መጥተው ይቀውጡታል - አንድ ሰው ዝንቤን እሽ ቢል ብሎ ነገሮናል - የአገሪቱ ህዝብ የመረጠው ጠ/ሚንስትር። :lol: :lol: :lol: ወደው አይስቁ አሉ።


Horus
Senior Member+
Posts: 42918
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by Horus » 23 Mar 2022, 17:19

የኦሮሞ ተረኛነት እንዴት አዲስ አበቤ እንዴት እንደ ቀጠቀጡት ስሙ! አዳነች አቤቤ ለምን ከአዲስ ከተማ እቆቆ መስማት ሸሸች?

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by TGAA » 24 Mar 2022, 01:37

Horus wrote:
23 Mar 2022, 14:59
እኔ ሆረስ ቃላት መሸንሸን አይጥመኝም! እቅጩን እነግርህና ስራህ ያውጣህ ነው ምልህ!

አቢይ አህመድ አሜሪካኖች ከስልጣን ሊያነሱት አንድ ሃሙስ ሲቀራቸው መላ ኢትዮጵያን የኢትዮጵያ ባንዲራ አሲዞ ክተት አገር አድን ብሎ ስልጣኑን ባዳነ ማግስት የኢትዮጵያ ዜጋ ሰንደቅ አላማህን ይዘህ ጥምቀት አትወጣም ተብሎ ተገለ። ከዚያ የላቀ ምን ክህደት ይኖራል! ትላንት ሌቦች የጎሳ ከበርቴዎቹን ሰብስቦ ብልጽኛ ባለ 12 ሚሊዮን ያፍሪካ ግዙፍ ፓርቲ ነን ፣ ከኛ ሌላ የኢትዮጵያ ፓርቲ ላሳር ሲል የመጨረሻ ወያኔያዊ እብሪቱን ላለም አወጀ!

ሞኝና ገንዘቡ አብረው አይቆዩም ይባላል ! ያንድ ጎሳ ግሩፒዝም የሚያስከትለው ዝቅጠት ይህን ይመስላል!

የጎሳ ፖለቲካ ሁሉምንም ይደመሳሳል ስል 30 አመት ሞላኝ! ያ ደሞ ሃቅ ነው ! ልብ በሉ!

ትግሬ ፈርሷል
አማራ ተከፋፍሎ ከፈረሰ ስንብቷል
ኦሮሞ ከላይ እስከ ታች ተከፋፍሎ ሸኔ፣ ኦነግ፣ ፒፒ ተባብሎ እየተዋጋ ነው
ቤኒ ሻንጉል አመጽ ነው
ሱማሊን እንዲሁ ቀውስ ነው

የኢትዮጵያ የጎሳ ከበርቴዎችና የጎሳ ነጋዴ ካድሬዎች አንድ ሙሉ አገር፣ አንድ አገር አቀፍ የጦርነት ፣ አምጽ፣ ሁከትና ቅውስ አውድማ ናቸው ። "ብሄር ብሄርሰብ ሕዝቦች" በጎሳ ፖለቲካ ደቀው በብሄር ጥያቄ ፈራርሰዋል !

ለዚህ ሁሉ ዘላለማዊ ቀውስ መፍትሄ የጎሳን ስርዓት ባስቸኳይ ማፍረስ ነው !!!

ሃቁ ይህ ነው! በቃ ! ዝብዝብ ቢበዛ ባህያ አይጫንም !!


ሆረስ ሀሳብህን በደንብ ሸንሽነህ አስቀምጠሀዋpል ምንም ጭማሪ አያስፈልገውም ፤ የጎሳ አጋፋሪዎቹ የተቀመጡበት ዙፋን ሲንቀጠቀጥ ነፍሳችውን ለማዳን የለመዷትን ስልጣን ለመቀጠል ፤ አቤቤ ወደ ጣይቱ አብይ ወደ ምንይልክ ተቀየሩ ፤ በህዝቡ ደማን ገንዘብ ነፍሳቸው አድነው የውጪው ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የአፍሪካ ዲያስፖራ ያልተሰራ ፤ አሜሪካንን ያሳሰበ ንቅናቄ አድርጎ ቤቱ ሳይደርስ ነው እነኝህ የካሀዲ ስብስቦች የጎሳ ፖለቲካቸው ውስጥ ተዘፍዝፈው ጥይታቸውን ሰላማዊ ህዝብ ላይ ያርከፈከፉት ፤ መቼም አንዱን ከዳተኛ ከሌላው ከዳተኛ ማወዳደር ባይገባም ፤ መለስ ከመነሻው እስከ ሞቱ ድረስ ሰለኢትዮጵያ ያለው ጥላቻ ሳይቀንስ ነው የሞተው ፤ አብይ ግን በስሩ የሰበሰባቸውን የሞጋሳ ቅልቦቸን ስልጣንና ገንዘብ እየመደበ ፤ በሁሉም መንገድ የጎሳ ፖለቲካን እንዲያስፋፉ ፤ ጭፍጨፋ በከለላ እንዲያኪያሄድ እያደረገ ፤ ህዝቡ እርሱ ላይ እንዲያቶኩር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የፈጸመው ክህደት የክህደት ጥግ ነው ፤ የሚያሳዝነው ግን ከወያኔ በአጠረ ጊዜ ይወድቃል ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በፊትም ሞኝ አልነበረም አሁንም አይደለም ግን ለሁሉም እድል ይሰጣል በሰአቱ ደግሞ እድልም ይነሳል ፤ እንደ አብይ ግን የህዝብ ድጋፍ ያገኝ ሰው መሪ ሆኖ አያውቅም ፤ እንደርሱም ህዝብን የከዳ ሰው የለም ፤

Horus
Senior Member+
Posts: 42918
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by Horus » 24 Mar 2022, 02:25

TGAA
አቢይ አህመድ እንደ ጎርፍ የፈሰሰለትን የሕዝብ ድጋፍ ከረሜላውን ለነገ ማሳደር እንዳቃተው ህጻን እስኳንደር ስላደረገ ነውኮ A Fool and His Money Are Soon Parted የሚባለውን ዊዝደም የተረትኩበት! በሱ ቤት ብልህነት መስሎታል፣ ግን ግዙፍ የግምት ስህተት ነው የሰራው ። እንደ ምታቀው ትልቅ የስትራተጂ ሳይንስ ጌም ቲኦሪ የሚባል አለ ። ሁለት ተፎካካሪ ተጫዋቾች እንዴት አንዱ ያንዱን ብልሃትና ስልት ቀድሞ በማሰብ ጨዋታውን እንደ ሚያሸንፍ የሚያስተምር ስሌት ነው። ዛሬ አሉ የሚባሉት የሚሊታሪና የቢዝነስ ሊቃውንት የሚመሩበት ሳይንስ ነው። እናም በጌም ቲኦሪ መሰረት አንድ ታክቲክ ወይም እስትራተጂክ እርምጃ የተሳካ ሆኖ ካሸነፈ በኋላ ያ ስልት ወይም እርምጃ በመሰረቱ ዋጋ አይኖረውም ። የታወቀ እርምጃ ስለሆነ! በመርካቶ ቋንቋ የተበላ ዕቁብ እነለዋለን! አቢይ ሲደላደል እብሪትና ሌሎችን ዝቅ ዝቅ ማድረግ! ሲወጠር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚለው ታክቲኩ አሁን የተበላ ዕቁብ ይባላል! ጌም ቲኦሪን በወረደ የሚያነቡት ግን ምን ማለት እንደ ሆነ፣ እንዴት እንደ ሚተገበር ያልገባቸው ሰዎች ስህተት ያን ይመስላል! አንዴ ያሸነፍንበት ስልት መድገም ካካ ነው! ጠላት ያወቀው ስለሆነ !! የአቢይ እና አማካሪዎቹ አለመብሰል የምታቀው በዚህ ነው ።

TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: በብሄር ጥያቄ የወደሙት "ብሄር፣ ብሄረሰብ እና ህዝቦች" A Fool and His Money Are Soon Parted!

Post by TGAA » 24 Mar 2022, 12:28

Well said brother Hours.
Fool me once, shame on you; fool me twice, shame on me.
I always wonder why leaders underestimate the collective wisdom of their people? It is just like a sailor headings into the sea despite a tsunami warning. Abiy"s PP not only did they betray people's genuine trust but their condescending tone,the Cockiness displayed on the stage was a complete turn off.

Post Reply