Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"ለኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ መድማት የቀድሞ ግንቦት ሰባት የአሁኑ ኢዜማ ውስጥ ያለ አንድ ቡድን ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል" ሀብታሙ አያሌው Ethio 360

Post by sarcasm » 11 Mar 2022, 08:59

Yeshiwas Assefa (EZEMA Party Chairman)

ለወንድሜ አብርሃ ደስታ!

የተናገርከውን ሰምቼ፣ ገፅታህን አይቼ የስሜትህን የጉዳት ጥልቀት ተረዳሁት። እኔም፣ አንተም ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም የታገልነው፣ አብረን የታሰርነው የማዕከላዊን፣ የቂሊንጦን እና የቃሊቲን የግፍ ፅዋ አብረን የተጎነጨነው፣ ብዙዎች የተሰደዱት፣ የቆሰሉት፣ የተሰውት ለሁሉም ዜጎች እኩልነት እና ፍትሃዊነት ነበር።

ከዚያ ሁሉ መከራ በኋላ ውጤት አለማየት አርሶ እንደተራበ፣ ተምሮ እንደወደቀ፣ ነግዶ እንደከሰረ፣ ያንገበግባል። በትግራይ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮም እና ባቤንሻንጉል የምናየውን የዜጎች ስቃይ ያመጣብን ኢህአዴግ እና ይዞት የነበረው የተበላሸ ሥርዓት መሆኑ ግልፅ ነው።

እጣ-ፈንታው አብሮ የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ መፍትሄ ካላበጀንለት ትላንት በሰሜን የታየውን ምስቅልቅል ነገ በምዕራብ፣ በደቡብ፣ በምስራቅ ወይም በመሐል አገር የማናይበት ምንም ዋስትና የለንም።

በግለሰቦችና ቡድኖች ክፉ እሳቤ እና ሥራ ምክንያት በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ፣ በተለይ በአፋር፣ በአማርና በትግራይ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ልጆች እና ህፃናት የደረሰውን መከራ ሳስብ የእኔም ሀዘን ጥልቅ መሆኑን ልገልፅልህ እፈልጋለሁ። ፈጣሪ ይሄንን አሳልፎ ዜጎች በፍቅር የሚተቃቀፉበትን ጊዜ እንዲያመጣልን እንናፍቃለን። እስከዚያው ግን ፈጣሪ ያበርታህ።



Habtamu Ayalew Teshome

የሸዋስ እውነት ለመናገር ለኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ መድማት የቀድሞ ግንቦት ሰባት የአሁኑ ኢዜማ ውስጥ ያለ አንድ ቡድን ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል ። የህዝብ ትግል ቤተመንግሥት ምንጣፍ ስር በመጣል አድርባይነትን ከጦርነት ያከበደ የኢትዮጵያን ህዝብ ትግል ለቡድን ጥቅም ሲል ለኦህዴድ የሸጠ ታሪክ የማይረሳው ክህደት ፈፅሞ የግል ሹመትን እንደ ድል የቆጠረ ቡድን … ለማንኛውም ታሪክ ሁሉንም ይመዘግበዋል።
Please wait, video is loading...