የዚህ ኮሚቴ የዚያ ኮሚሽሽ፣ የዚህ ፓርላማ የዚያ ምክክር በሉት፤
ሺ ግዜ የኦሮትግሬ፣ የኦሮማራ፣ ያማራትግሬ ምናምን ሚዛን ቢቀመር ቢፈርስ፣
በየአመቱ አዲስ ቲኦሪ ቢደመር ቢቀነስ ቢሰበክ ቢከለስ፤
ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ ዜጋዎች የራሳቸውን ሰንደቅ አላማ መያዝ እስካልቻሉ ድረስ፤
ሕዝቦች በዘር ክልል እስር ቤት ታጉረው የጎሳ ከበርቴና የጎሳ ባለመሬት ባላባት እንደ መስፍን በልዩ ሃይል አፍኖ መግዛት እስከ ቀጠለ ድረስ፤
የትግሬ ባንዳዎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጠፈጠፉት ሕገ ጎሳና የጎሳ ፓርላማ ጸንቶ ኢትዮጵያዊያን ንጹህ ዉሃና ዘይት እንዳያገኙ እስከ ተደረገ ድረስ።
ባንድ ቃል ይህ ቆሻሻ የጎሳ ስርዓት መለወጥ፣ ማፍረስ እስካልተጀመረ ድረስ ሁሉ ያሻውን ሊዘባርቅ ይችላል።
ግን መንግስት የሚባል ነገርም አይረጋም፣ ሰላም የሚባል ነገርም አይኖርም፣ እድገት የሚባል ነገርም የኢትዮጵያ እድገት ሳይሆን የመሬት ባላባት የሆነው የጎሳ ከበርቴና በጉቦና በሌብነት የሚከብረው የጎሳ የቢሮ ከበርቴ ብልጭልጭ ማዘናጊያ ሆኖ ይቀራል ።
በመንግስት ላይ ትችት፣ ነቀፋ ወይም ቅዋሜ አለኝ የሚሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ኢጎሳዊ ሰርዓት እንዲመጣ እስካልሰሩ ድረስ እራሳቸው የችግሩ አካል እንጂ የመፍትሄ አካል አይደሉም! አይሆኑም!
የጎሳ ፖለቲካ ገና ሁሉንም ይደመሳሳል!