Finfinne Times
ፊንፊኔ የፖለቲካ ቀውሱ ማቀጣጠያ የመጨረሻዋ አማራጭ እንደምትሆን ግልፅ ነው። በሌሎች የክልል ከተማዎችም እንዲሁ ሊደረጉ የሚችሉ አመፅና ሁከቶች ይኖራሉ።
የሀይል አሰላለፍ ለውጡ የሚያመጣቸው መዘዞች ከፍ ያሉ ናቸው። ተስፋፊው ልሂቁ ለዘመናት የገነባቸው የፖለቲካ ጥቅም አስከባሪና የተጠና ጫና ማድረጊያ መሳሪያዎቹ ብዙ ናቸው።
ተስፋፊው ልሂቅ ታች ህዝቡ ድረስ የሚዘረጉ የግርግርና የሁከት መዋቅሮች አሏቸው። ከፊት ሲታዩና ከጀርባ ያላቸው ሽፋን አራምባና ቆቦ የሆኑ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ሰንሰለቶቻቸች በቀጣይ መንዠዋዠዋቸው አይቀርም።
በአጠቃላይ የብልጽግናን የሶስት አመታት የፖለቲካ መንገድ ሲደግፉ የነበሩ መዋቅሮቻቸው ተገልብጠው ደግሞ ሁሉንም አይነት ቀውስ ማቀጣጠያ ነዳጅ እንደሚሆኑ ጥርጥር የለውም።
የባለፈው የአድዋ ድል በአል ሲከበር የታየው የሁከትና የግርግር ጩኸት የዚህ ኡደት አንዱ ማሳያ ነው። ይህ በትር መንግስት ላይ ብቻ ትኩረት ያደርጋል ማለት አይቻልም።
በህዝባዊ የአመፅ ሰንሰለት ስለተወጠረ በፖለቲካ ስም ማንነትን ሀይማኖትን ጨምሮ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ቤት ላይ መድረሱ አይቀርም።
ሲፈነዳ ሁሉንም ነካክቶ ሊሰበሰብ ቢችልም ምን ያህል ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ግን መገመት ከባድ ነው። ጉዳዩ ከመንግስት ፀጥታና ደህንነት መዋቅር ካፈተለከ ደግሞ የእሳት ንዳዱ በህዝባዊ እንቅስቃሴ ለማጥፋት ስለሚሞከር ከፍተኛ ቀውስ ምንአልባትም እንደ ሀገር የመፍረሳችን የመጨረሻው መንገድ ይሆናል።
የሆነው ሆኖ በዚህ ሰአት የቅድመ ስጋት የደህንነት ስራዎች ካልተሰሩ .. በፊንፊኔ ከተማ ከአምስት ወራት በፊት እንዲመዘገቡ የተደረጉ የጦር መሳሪያዎች በጊዜያዊነት ካልተሰበሰቡ .. ሁከት ቀስቃሽ አመፅ አቀጣጣይ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ካልታሰሩና ካልታገዱ .. በየ ኬላዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥረ ካልተደረገ
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች የገንዘብ ዝውውሮች በቅርበት ክትትል ካልተደረገባቸው .. የፀጥታ የደህንነት መዋቅሮች አሁን ያለውን የሀገሪቱን የልብ ምት በቅርበት ማዳመጥ ካልቻሉ ..
በየ መንግስት ተቋማት ያሉ ህቡዕ አሰራሮች ካልተፈተሹ .. የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገ በስተቀር የቀውስ ንዳድ እንፋሎቱ ህዝቡን ገርፎ መጥፎ ጠባሳ ሊያትም ይችላል።
ጠባሳው ደግሞ ቶሎ የማይሽር ወይም ደግሞ ለሌላ ሀገራዊ ቀውስ መንደርደሪያ ሆኖ ከቁጥጥር ሊወጣ ይችላል። በዚህ ሰአት በአራዳም በፋራም የሚባል አሰራር አያስፈልግም። የእያንዳንዱ ደቂቃዎችን ምት መስማት ካልተቻለ በፖለቲካ ንትርክ ሳይሆን በሰው ልጅ ህይወት የሚወራረድ ቀውስ ሊስፋፋ ይችላል !!
Finfinne Times
Please wait, video is loading...