Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by Abere » 02 Mar 2022, 09:46

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፥
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 7435
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by Naga Tuma » 11 Mar 2022, 16:06

Abere wrote:
02 Mar 2022, 09:46
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፥
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

ታሪካዊ ዘገባ።

ነገር ግን የትርጉም ስህተት የለበትም? ሰዉን እንደ ተባይ እና ኣእምሮ የለሽ ማሰብ እና ክብሩን እንንጠቅ ማለት ኣብረዉ ይታሰባሉ?

1991 በኣ. አ. ኮሌጅ እያለን ኣንድ የማከብረዉ ጓደኛዬ ኣሜርካ ባግዳድን ያጠቃች ቀን ለሊት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዜና ዘገባ ለማዳመጥ ሄደ። ዶርማችን ተመልሶ ዜናዉን ኣሜርካ ባግዳድን ኣሽመደመዳት ኣለ። ወድያዉ ፈገግ ብዬ ለመሆኑ የትኛዉን የኢንግሊዘኛ ቃል ነዉ ወደ ኣሽመደመዳት የተረጎምከዉ ብዬ ጠየኩት። ፈገግ ኣለና ከፊቴ ዘወር ኣለ። እኔም እያጠናሁ ወደ ነበረዉ ተመለስኩኝ።

ይህን ዘገባ ሳዳምጥ የትኛዉ የኢንግሊዘኛ ወይም የጀርመንኛ ቃል ነዉ እንዲህ የተተሮጎመዉ ኣልኩ። ተብሎም ቢሆን ለታዳጊዎች ማስረዳት የሚሻል ቃል ታጣ? ወይስ ኣንድ የፖለቲካ ምሁር እንዳለዉ "they put us down and we are putting ourselves downer" እያልናቸዉ ነዉ? አረ መተርጎም እየተስተዋለ።

Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by Abere » 11 Mar 2022, 16:27

ማንኛውም ስነ-ቃል ይሁን የግጥም ስንኝ በነበረው ጊዜ ውስጥ በሚኖረው የአድማጭ ህዝብ አረዳድ ዘይቤ ይወሰናል። የዛሬውን ትውልድ ጽሁፍ ከዛሬ 120 አመታት በፊት ለሚኖር ህዝብ ቢቀርብ ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። በዚህ ትውልድ እንኳን በዕድሜ እና በአኗኗር ምክንያት ከፍተኛ የመረዳት ችግር አለ። ለምሳሌ ስንት በገጠር የሚኖር ህዝብ በተለይም እድሚያቸው ከፍያለ የሬድዮ ዜና መረዳት እንደሚችሉ ግራ ይገባኛል። ለማንኛውም ስለ አጼ ምኒልክ የተገጠመው ትርጉሙ ግልጽ ነው።

ጣልያኖች እንጀራ አይበሉም፡ ፉርኖ እና እንቁላል ነበር መግባቸው። ስለዚህ ጣልያን ቢያሸንፍ ኑሮ አበሻ ታክስ ወይም ግብር የሚያቀርበው እንቁላል ነበር። በቀላል አማርኛ ነጭ ድሃ ነጭ ማር ግብር ይከፍላል ማለት ነው። የጥንት የዶሚተሪ ጓደኛህ የተናገረው ለእኔ ግልጽ ነው። ኢራቅ ተሽመደመደች ማለት ሺባ ሆነች(militarily paralyzed/ ወይም የአሜሪካ ጦር የኢራቅን አከርካሪት ሰበረው ማለት ነው። በነገራችን ላይ አማርኛ ቋንቋ በቃላት እጅግ የበለጸገ ነው - ማንኛውንም ነገር መግለጽ ይችላል - ቁሳዊ ይሁን ረቂቅ ሃሳባዊ። ኢትዮጵያ በዚህ በኩል ታድላለች።

Naga Tuma wrote:
11 Mar 2022, 16:06

Post by Naga Tuma » 12 Mar 2022, 03:29

አበረ፥

ሀሳቤን የጨመርኩኝ በተባላዉ ላይ ገንቢ ሊሆን ከቻለ ብዬ ነዉ።

ዘገባዉ ዉስጥ ሁለተኛ ምንጭ ወይም ሰከንደሪ ሶርስ የሆኑ ቃላት ኣሉ። ተባይ ያልኩኝ ቃሉን ላለመድገም ነዉ። ጀርመን ዉስጥ በወቅቱ የተባለዉ ዋነኛ ምንጭ ወይም ፕራይመሪ ሶርስ ነዉ። የእኔ ጥያቄ በኣጭሩ በዋነኛ እና ሁለተኛ ምንጮች መካከል የትርጉም ስህተት ኣለ ወይስ ዬለም ነዉ። መልሱን ኣላዉቅም። ዘገባዉን ያዘጋጀዉ ያዉቃል ወይም ማወቅ ኣለበት። የእኔ መላምት ተባይ እና ኣእምሮ የለሽ ብሎ ማሰብ እና ክብሩን እንንጠቅ ማለትን ኣንድ ኣእምሮ ማሰብ ኣይችልም ነዉ። ዘገባዉን ያቀረበዉ ይችላል ካለ መተንተን እና ማሳመን ይችላል። ይህን ነጥብ ነዉ መጨመር የፈለኩኝ።

የማከብረዉ ጓደኛዬ ጥያቄዬን ሰምቶ ፈገግ ብሎ ዘወር ኣለ እንጂ መልስ ለመመለስ ኣልሞከረም። ለዚህም ነዉ ያከበርኩት። ብዙ ንጽሃን፣ ህጻናትን ጨምሮ፣ የሚኖሩባት ታሪካዊ ከተማ ተሽመደመደች ማለት ይከብዳል። ጓደኛዬ ሰከንደሪ ሶርስ ነበር። ፕራይመሪ ሶርስ ያለዉን ኣላዉቅም። ጓደኛዬም ይህን የእንግሊዘኛ ቃል ነዉ የተረጎምኩኝ ኣላለኝም።

በቅርቡ ስለ ንገስት ሳባ ክርክር ተነስቶ የተከራከርከዉን ኣንብቤኣለሁ። እዚህ ያለዉ ሁለት መስመር ስንኝ ክርክሩ ኣጥጋቢ ሆኖ ነዉ ብዬ እራሴን ጠይቄኣለሁ። ፕሮፌሰር ዶናልድ ለቪን እንደጻፉት የኢትዮጵያ ታሪክ ወይ ከንግስት ሳባ ጉብኝት በፊት ጀምሮ የነበረ ነዉ። ወይ ደግሞ ከዛ በሁዋላ የጀመረ ነዉ። ሁለቱንም ሊሆን ኣይችልም። ፕሮፌሰሩም የመከሩት ይህቺዉ ናት። እኔ ጉብኝቱ የታሪክ አካል ቢሆንም ታሪካችን ከጉብኝቱ በፊት ጀምሮ የነበረ ነዉ ከሚሉት ጎራ ነኝ። እዚህ ያለዉን ሁለት መስመር ስንኝ የምያቀነቅኑት ታሪካችን ከጉብኝቱ በሁዋላ የጀመረ ነዉ የሚሉት ጎራ ነዉ።

ሌላኛዉ ጎራ የሚለዉ፥
ምኒልክ ተወልዶ ባይሆን አባ ብያ
ግብሯ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ኢትዮጵያ
Abere wrote:
11 Mar 2022, 16:27

ማንኛውም ስነ-ቃል ይሁን የግጥም ስንኝ በነበረው ጊዜ ውስጥ በሚኖረው የአድማጭ ህዝብ አረዳድ ዘይቤ ይወሰናል። የዛሬውን ትውልድ ጽሁፍ ከዛሬ 120 አመታት በፊት ለሚኖር ህዝብ ቢቀርብ ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። በዚህ ትውልድ እንኳን በዕድሜ እና በአኗኗር ምክንያት ከፍተኛ የመረዳት ችግር አለ። ለምሳሌ ስንት በገጠር የሚኖር ህዝብ በተለይም እድሚያቸው ከፍያለ የሬድዮ ዜና መረዳት እንደሚችሉ ግራ ይገባኛል። ለማንኛውም ስለ አጼ ምኒልክ የተገጠመው ትርጉሙ ግልጽ ነው።

ጣልያኖች እንጀራ አይበሉም፡ ፉርኖ እና እንቁላል ነበር መግባቸው። ስለዚህ ጣልያን ቢያሸንፍ ኑሮ አበሻ ታክስ ወይም ግብር የሚያቀርበው እንቁላል ነበር። በቀላል አማርኛ ነጭ ድሃ ነጭ ማር ግብር ይከፍላል ማለት ነው። የጥንት የዶሚተሪ ጓደኛህ የተናገረው ለእኔ ግልጽ ነው። ኢራቅ ተሽመደመደች ማለት ሺባ ሆነች(militarily paralyzed/ ወይም የአሜሪካ ጦር የኢራቅን አከርካሪት ሰበረው ማለት ነው። በነገራችን ላይ አማርኛ ቋንቋ በቃላት እጅግ የበለጸገ ነው - ማንኛውንም ነገር መግለጽ ይችላል - ቁሳዊ ይሁን ረቂቅ ሃሳባዊ። ኢትዮጵያ በዚህ በኩል ታድላለች።

Naga Tuma wrote:
11 Mar 2022, 16:06
Abere wrote:
02 Mar 2022, 09:46
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ፥
ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

ታሪካዊ ዘገባ።

ነገር ግን የትርጉም ስህተት የለበትም? ሰዉን እንደ ተባይ እና ኣእምሮ የለሽ ማሰብ እና ክብሩን እንንጠቅ ማለት ኣብረዉ ይታሰባሉ?

1991 በኣ. አ. ኮሌጅ እያለን ኣንድ የማከብረዉ ጓደኛዬ ኣሜርካ ባግዳድን ያጠቃች ቀን ለሊት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ዜና ዘገባ ለማዳመጥ ሄደ። ዶርማችን ተመልሶ ዜናዉን ኣሜርካ ባግዳድን ኣሽመደመዳት ኣለ። ወድያዉ ፈገግ ብዬ ለመሆኑ የትኛዉን የኢንግሊዘኛ ቃል ነዉ ወደ ኣሽመደመዳት የተረጎምከዉ ብዬ ጠየኩት። ፈገግ ኣለና ከፊቴ ዘወር ኣለ። እኔም እያጠናሁ ወደ ነበረዉ ተመለስኩኝ።

ይህን ዘገባ ሳዳምጥ የትኛዉ የኢንግሊዘኛ ወይም የጀርመንኛ ቃል ነዉ እንዲህ የተተሮጎመዉ ኣልኩ። ተብሎም ቢሆን ለታዳጊዎች ማስረዳት የሚሻል ቃል ታጣ? ወይስ ኣንድ የፖለቲካ ምሁር እንዳለዉ "they put us down and we are putting ourselves downer" እያልናቸዉ ነዉ? አረ መተርጎም እየተስተዋለ።
Last edited by Naga Tuma on 12 Mar 2022, 03:37, edited 2 times in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by Abere » 12 Mar 2022, 11:05

እንደ እኔ ቁም ነገሩ አጼ ምኒልክ የዘመኑ ኢትዮጵያ መሪ ባይሆኑ፥ አገራችን በጣልያን ቀኝ ገዥ መዳፍ ትወድቅ ነበር - የኢትዮጵያዊያን ህብር የሆኑት የተለያዩ የጎሳ ባህል እና ቋንቋ ይጠፋ ነበር። ሌላው ንጉሳዊያን የእራሳቸው መዋዕለ መንግስት ጸሐፍት አላቸው። ስለዚህ የንጉስ ምኒልክ የጦር ይሁን የአስተዳደር መዋዕል የተዘገበ እና በጽሁፍ የሰፈረ ነው። ከየሜዳው የሚቃረም ግጥም ሳይሆን በመዋዕል የሰፈሩ መወድሰ ግጥም ላይ ነው ማተኮር ያለብን።

የአንድ መሪ ወይም ንጉስ ውሳኔ እና እርምጃ እንደት የአንድን አገር ህዝብ ህይወት ወደ መጥፎ ወይም መልካም መንግድ እንደሚወስድ በዐይናችን በዘመናችን እያየን ነው። በመሪዎች ግትርነት ወይም መጥፎ የውሳኔ ምርጫ ብቻ አንድ አገር ሊወድም፥ሊደፈር፤ሊቃጠል፤ህዝብ ሊሰደድ እንደሚችል እያየን ነው። በአገራችን አሁን እያየን ነው ለምሳሌ የትግራዩ ደብረጽዮን በስህተት መከላከያ በማሳረዱ፤ በማይ ካዲራ አማራዎች ላይ ጭፍጨፋ ውሳኔ በማድረጉ ይኸው ያን ተከትሎ በአገሪቱ ብዙ ነገር ወድሟል። በአለምም ዙርያ እንድህ ነው የሚሆነው። በአንጻሩ ደግሞ ብልህ እና ችሎታ ያላቸው መሪዎች ህዝባቸውን እና አገራቸውን ከውርደት ይታደጋሉ- በታሪክም ታይታዋል። አጼ ምኒልክ ቀዳሚ ተጠቃሽ ይሆናሉ።

ይህን ካልኩኝ ዘንድ የኢትዮጵያ ታሪክ ከነግስተ-ሳባ ይጀምራል ወይስ ከእርሷ በፊት ለሚለው ለእኔ ቀላል ጥያቄ ነው - የታሪክ ሰው አይደለሁም ግን ታሪክ ሳይንስም ሎጅክም ነው። ከዚያ አንጻር የግሌን ልሞክር። ታሪክ የሰው ልጅ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነበር ማለት ይቻላል። ግን ስዎች ቅድመ-ታሪክ (prehistoric) እና ታሪክ ዘመን (historic period) ብለው ያወራሉ። ቅድመ-ታሪክ ይሚሉት የጽሁፍ ማስረጃ ባልነበረነት ጊዜ እንደ ማለት ነው - ግን በአርኪዎሎጂካል ግኝት ቅድመ ታሪክ ይኖር የነበረውን ህዝብ ታሪካዊ ማንነት ማወቅ ይቻላል። የጽሁፍ ጊዜ ታሪክ ግን ተዘግቦ ስለሚገኝ ማወቅ ይቻላል - አስቸጋሪ የሚሆነው ግን ሳይንሳዊ ፍተሻ አድርጎ ያለ አድልዎ መተንተን ነው። ኢትዮጵያ በጣም ጥንታዊ አገር ናት- በመጽሀፍ ቅዱስ እንኳን በኦሪት እና በሃዲስ ስሟ ተደጋግሞ ተጠቅሷል። ይህም ከሰለሞን እና ከንግስተ-ሳባ ትውውቅ በፊት። የኢትዮጵያ ታሪክ ከሰለሞንዊ ንግስታት አይጀምርም - ከዚያ በፊት ብዙ ሺ አመታት ታሪክ አለ። Ethiopia is one of the oldest nation on earth, we don't have to doubt that.

Naga Tuma
Member+
Posts: 7435
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by Naga Tuma » 16 Mar 2022, 18:55

እዉነት ነዉ ኣበረ፣ "ታሪክ የሰው ልጅ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ነበር ማለት ይቻላል።"

ፕሮፌሰር ዶናልድ ለቪን ያለዉ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ የኖሩ ኢትዮጵያዉያን ይህንን በትክክል ማስተዋል ተስኖኣቸዉ ነበር ነዉ። ምክንያቱም "By the will of God, the children of Shem are blessed and the children of Ham are cursed" (paraphrased) ሰምተዉ ነዉ።

የእግዝኣብሔርን ፈቃድ መቃረን ኣልፈለጉም። በፊት የምያዉቁትንም ታሪክ መርሳት ወይም መተዉ ኣልፈለጉም። ይህ ሁኔታ ያዘገመ የማንነት ትግል (protracted identity struggle) ኣስጀመራቸዉ ይላል። ከሁለቱ ኣንዱን ተቀብለዉ በዛ ቢረጉ ይሻላቸዉ ነበር ነዉ ያለዉ። ከኢትዮጵያ እና ሀበሻ ኣንዱን ተቀብሎ መርጋት ማለት ነዉ። ሁላቱ ልዩነት እንዳላቸዉ ከተስተዋለ።

በዚህ ዘመን ይህ ከታረመ ከትግሉ ነፃ ወጣን ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

EPRDF
Member
Posts: 2162
Joined: 26 Jan 2010, 12:58

Re: ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፥ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ግዜ አበሻ።

Post by EPRDF » 16 Mar 2022, 23:56

ጋሽ አብሬ፣

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ ዕንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሐበሻ

ቅኔ ነው።

ሰሙ፣ ዕንቁላል ነበር። ሲሆን፣
ወርቁ፣ ዕንቁ ፡ ላልነበር። ነው።

እገረ መንገዴንም ለምኒሊክ የተገጠመ ሌላ አንድ ቅኔ ጀባዕ ልበለህ።

ይወዱኝም እንደሆን ይሄው አለሁልዎ፣ ይገድሉኝም እንደሆን ይሄው ቆምኩልዎ
የዓለም ጣዕም ምኒሊክ ብዬ ሰደብኩዎ

አይ ሆፕ የምታውቀው፣ ካላውቅከውም ፍቺው ላይ የምትደርስበት ይመስለኛል።
ችግር ካለ ሌት ሚ ኖው ተመልሸ እመጣለሁ።

Post Reply