የትግራይ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚኪኤል
ዶክተር ደብረጽዮን 126ተኛው የዓድዋ ጦርነት ድል አስመልክተው በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የዓድዋ ድል የትግራይ ህዝብ እና ሰራዊት የሀገር ዳር ድንበር ለማስከበር ሲያካሂዱት የነበረው ተከታታይ ውጊያ እና ያስመዘገቡት አንጸባራቂ ድል ተቀጥያ እና ማጠቃለያ መሆኑን አብራርተዋል።
ይህ ሁነትም የትግራይ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ጭቆናን ፍጹም የማይቀበል የህዝቦች መብት እንዲረገጥ የማይፈቅድ ሉአላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማረጋገጥ ወደ ኋላ የማይል ባጠቃላይ ለብሄራዊ ክብሩ እና ማንነቱ የማይደራደር ህዝብ መሆኑን ያረጋገጠበት መሆኑን በጽሁፋቸው አስፍረዋል።
በሌላ በኩል የትግራይ ህዝብ በየምዕራፉ የገጠሙትን አምባገነኖች እና አፋኝ መዋቅራቸውን እየደመሰሰ ፈታኝ መድረኮችን እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሰናክሎችን አልፎ ሀያልነቱን ያረጋጋገጠ እና የአሸናፊነት ዘውድ የደፋ ጀግና ህዝብ ነው ሲሉ ዶክተር ደብረጽዮን በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፋቸው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም ቢሆን የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ከቅርብ እና ከሩቅ ሀይሎች ጋር ተጣምረው በትግራይ ታሪክ በርካታ አካላት የተሳተፉበት ጦርነት በመለኮስ እንደ ህዝብ ሊያጠፉን ተንቀሳቅሰዋል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚኬል የትግራይ ህዝብ ግን አንደነቱን በማጠናከር እንደ ሁልጊዜው በከፍተኛ ትግል ወራሪ ጠላቶችን እየደመሰሰ ህልውናው ማረጋገጡን ገልጸዋል።
የዓድዋ ጦርነት ድልን ክብር ለማስጠበቅም በብሄራዊ አላማችን ጸንተን ከበባዎችን ሰብረን በድል ለመውጣት የጀመርነውን ሁለንተናዊ ትግል ልናጠናክር ይገባል ሲሉ ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚኪኤል ገልጸዋል።

https://www.facebook.com/dimtsiweyane1/ ... 3533452338