Please wait, video is loading...
"እኔ እስከማውቀው ለትግራይ የተሰጠ 100 ቢልዮን ብር የለም። 1.2 ቢልዮን ብር ነው። እሱም ለትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ነበር፤ ተከፍሏል።"
100 ቢልዮን ብር ለትግራይ? እኔ እስከማውቀው ለትግራይ የተሰጠ 100 ቢልዮን ብር የለም። ወይም ለማን እንደተሰጠ ይነገረን! የተሰጠን 1.2 ቢልዮን ብር ነው። እሱም ለትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ነበር፤ ተከፍሏል። ከክልሎች የተሰጠን ድጋፍ ጠቅላላ 600 ሚልዮን አከባቢ ይሆናል። ትግራይ እያለን አልተነካም። ስለዚህ ኦዲት ይደረግ!
Re: "እኔ እስከማውቀው ለትግራይ የተሰጠ 100 ቢልዮን ብር የለም። 1.2 ቢልዮን ብር ነው። እሱም ለትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ነበር፤ ተከፍሏል።"
የሪፖርተር ቆይታ ከዶ/ር ሙሉ ነጋ ፣ የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ሪፖርተር ፡- በወቅቱ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን ያህል ገንዘብ ነበር ያገኘው? በበጀትም በድጋፍም? ገንዘቡስ የት ደረሰ? ገንዘቡ እንደባከነና በእርስዎ አስተዳደር ጊዜ ዘረፋ እንደነበረ ሁሉ ይነገራልና ገንዘቡን የት ነው ያደረጋችሁት?
ሙሉ (ዶ/ር)፡- ውሸት ነው፣ ይኼንን ልንገርህ፡፡ በገንዘቡ ደመወዝ ብቻ ነበር የሚከፈለው፡፡ እስከ ሦስትና አራት ወር፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የክልሎች ዕርዳታ እስከ 500 ወይም 600 ሚሊዮን ብር ገደማ የመጣው፡፡ እኔ እስከምወጣ ድረስ እሱ አልተነካም ነበር፡፡ አስረክቤ ነው የወጣሁት፡፡ ያልገባም ገንዘብ ነበር፡፡ ግን ግምቱ ወደ 600 ሚሊዮን ብር ይሆናል፡፡ የመጣልን የየክልሉ ደመወዝ 1.2 ቢሊዮን ብር አካባቢ ነው፡፡ እኛ ከደመወዝ በሚቆረጠው ግብር ነበር፣ ለአንዳንድ ነገር ስናውል የነበረው፡፡ ከክልሉ ትንሽ የተራረፉና ከአካውንት የተገኙ የተወሰኑትን ለመጠቀም ተሞክሯል፣ ግን ትንሽ ነው፡፡ እኛም ደግሞ በመጨረሻ አካባቢ ወደ 100 ሚሊዮን ብር አካባቢ ግብር ለመሰብሰብ ሞክረናል፡፡ እንቅስቃሴ አድርገናል፡፡ እና እንደሚባለው ይኼ 100 ቢሊዮን ብር ምናምን ልክ አይደለም፣ እኔ አላውቅም፡፡ እኔ የማውቀው ወደ እኛ የሚመደቡ በጀቶችን ለደመወዝ ነው የምናውለው፡፡ ለአራት ወር ደመወዝ ይከፈላል፣ ከዚህ ውጭ አልነበረም፡፡ ክልሎች የሰጡን ግን እንኳን ሊባክን፣ ሥራ ላይ እንዲውል ዕቅድ አውጥተን ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- ስለዚህ የፌዴራል መንግሥቱ በስምንት ወር አወጣሁት የሚለው 100 ቢሊዮን ብር ትክክል አይደለም ነው የሚሉት?
ሙሉ (ዶ/ር)፡- ልክ አይደለም፣ በየት በኩል? እኛኮ ሥርዓት አለን፡፡ ምናልባት ይኼ ለዕርዳታና ለእህል መግዣ ከሆነ፣ ያ ደግሞ እኛ ውስጥ አይደለም፡፡ የፌዴራል ነው፡፡
ሪፖርተር፡- መንግሥትም እኮ ለአስተዳደሩ ሰጠሁ አላለም፡፡ ለወደሙ መሠረተ ልማቶች ጥገናና ለሰብዓዊ ዕርዳታ ነው ወጣ ያለው፡፡
ሙሉ (ዶ/ር)፡- እሱም ቢሆን 100 ቢሊዮን ብር ብዙ ነው፡፡ ምክንያቱም የክልሉ በጀት 18 ቢሊዮን ነበር፡፡ የፌዴራል መንግሥት በየዓመቱ የሚልከው ደግሞ ስምንት ቢሊዮን ነበር፡፡ ስለዚህ ያንን ስምንት ቢሊዮን ብር ነው እንግዲህ፣ እሱ ደግሞ ገቢ ስላልነበረን ለደመወዝም አይበቃንም፡፡ ስለዚህ መጨረሻ ላይ ጠይቀን ነበር ሁለት ቢሊዮን ብር አካባቢ ለአንዳንድ የሥራ ማስኬጃ ተብሎ እንዲጨመርልን፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያዝ ገንዘብ ነበረ እርሱ እንዲለቀቅልን የተወሰነ እንቅስቃሴ አድርገን ነበር እንጂ ገንዘብ አልነበረንም፡፡

Continue reading http://webcache.googleusercontent.com/s ... clnk&gl=uk