የጭካኔው ማሳያና የአውሬነት መገለጫ የሆኑት የፋሽስት አብይ ወታደሮች በትግራይ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ዘግናኝን ግፍና ጭፍጨፋ ቀኑን ጠብቆ ቀስ በቀስ እውነታው በማስረጃነት ተደግፎ እየወጣ ይገኛል።
በደብረ አባይ ንፁሃን ወጣቶች ላይ የፈፀሙት ጅምላ ግድያ የነዚህን ደመኛ ጠላቶች የጭካኔ ጥግ ያሳየ ነው። በደብረ አባይ በወቅቱ ከነበረው ጦርነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበራቸውን ንፁሃን ወጣቶች ከየቤቱ እየገፈፈ በማስወጣት ጎዳና ላይ በጥይት ሩምታ አርግፈዋቸዋል።
የትግራይን ህዝብ ደም በከንቱ በማፍሰሳቸው የአውሬነት ደስታ ሲያንፀባርቁ ከዚህም በላይ የትግራይ ህዝብ እንደህዝብ የማጥፋት እቅዳቸውን ሲናዘዙም እርስ በራሳቸው በተቀረፁት ቪዲዮ አስመልክተውናል።
ከአውሬነት ተራ የሚሰለፉት እነዚህ የፋሽስቱ ቡድን ወታደሮች ታድያ በደብረ አባይ በአንድ ጀምበር በጅምላ በግፍ የገደሏቸው ንፁሃን ወጣቶችን ከመግደላቸው በፊት ዘግናኝ የሚባል እንግልት ያደረሱባቸው እንደነበር የሚያሳይ አዲስ ተንቀሳቃሽ ምስል ተገኝቷል።
የካቲት 16/2014 ዓም
ድምፂ ወያነ ትግራይ
Please wait, video is loading...