Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by sarcasm » 09 Feb 2022, 18:11

በእንዚህ ነገሮች ላይ ብሔራዊ መግባባት እንዲኖር ይፈልጋል :- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ - ብልፅግና ፓርቲ


በእንዚህ ነገሮች ላይ መግባባት consensus እንጂ ለውጥ change የለም



አገሩን የሚወድ ሰው ሁሉ በመሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖረው ይፈልጋል። ብሔራዊ መግባባት ማለት ሁሉንም ጨፍልቆ አንድ ማድረግና በአንድ ሃሳብ እንዲስማማ ማድረግ ሳይሆን መሠረታዊ በሆኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አተያይ መያዝን የሚመለከት ነው።

ምክንያቱም በአንድ አገር ወይም በአንድ ቤተሰብ ውስጥ እንኳን አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ስለማይኖር ሕዝብም በሁሉም ነገር ላይ ይግባባል ማለት አይቻልም። ሆኖም ልዩነቱን አቻችሎ ለድርድር በማይቀርቡ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለአገር በሚጠቅም መልኩ በጋራ መስራት የግድ አስፈላጊ ነው።

ከአገር እና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም አንጻር ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦችን በመለየት የጋራ እስቤና መግባባት መያዝ የሚገባን ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ መወያየት ያስፈልጋል።ለአብነትም፣ በመሰረታዊነት ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ መግባባት ያስፈልጋል።

ምክንያቱም ሕገ መንግሥቱ ላይ መግባባት ካልተቻለ አብሮ መኖርም ሆነ እንደ አገር የሚታሰበውን ብልጽግና ማምጣት ያስቸግራል።ከሕገ መንግሥቱ በተጓዳኝም በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አስፈላጊ ነው። የፌዴራል ሥርዓቱ ላይም ብሔራዊ መግባባት መፍጠር መቻል ሊፈጠሩ ከሚችሉ አላስፈላጊ ክስተቶች ይታደጋል።
Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 42901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by Horus » 09 Feb 2022, 18:24

የኢትዮጵያ መሰረታዊ በሽታ የትግሬ ባንዳዎች በኢትዮጵያ ላይ የጫኑት የዘር ሕገ መንግስት ነው። ያ ነው የሚለወጠው ፤ የቀሩት ሁሉ ከዞያ የመነጩ ናቸው ። ያ የትግሬ ዘረኛ ወረቀት ካልተለወጠ በትክክል ኢትዮጵያ ዳግማዊ የካቲት አብዮት ይጠብቃታል።

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by Abere » 09 Feb 2022, 18:39

በቃ አብይ አህመድም፤ወያኔም ተደምስሰዋል - ተሸንፈዋል። ህገ-መንግስት አንጻራዊ እንጅ ፍጹማዊ አይደለም። እንኳን የደደቢት የውስጥ ደንብ መለኮታዊ አስተምሮ እና ቀኖና እንኳን እንደ ማህረሰቡ ዕድገት ደረእጅ ይቀያራሉ። በመሰረቱ የወያኔ እና ኦነግ ኢ-ህገ መንግስት ከተሻረ ቆይቷል- አማራ ጭራሽም አያውቀው። የወያኔን ህገ-መንግስት እየቀደደ የስኳር እና ቅመም መጠቅለያ የህጻንት መጸዳጃ እና የእጀራ መጋገሪያ ካደረገው 30 አመታት ሞልቷል።አብይ አህመድ ሰላም ማምጣት እንደ ማይችል የተረጋገጠ ቢሆንም በዚህ ያህል ፍጥነት ግን እንደ ሚወድቅ ግን የጠበቁ ብዙ ያሉ አይመስለኝም። እንደ እኔ ዐብይ አህመድ በኦፊሴል ዋና ከተማውን ለምን ነቀምት ወለጋ አያደርገውም - ከኦነግ ማዘዣ ጣብያ ላይ።

eden
Senior Member
Posts: 10144
Joined: 15 Jan 2009, 14:09

Re: በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by eden » 09 Feb 2022, 19:08

ሆረስ፣ ወደ ቅይጥ መጥቻለው ያልክ መስሎኝ? የዜጋና ህብረብሄር ፌደራሊስም ቅይጥ የሆነ ነገር (ለግዜውም ቢሆን) ይሁን ብለህ ነበር መሰል? እንዴት ነው?

ለግዜው እሱን ተወውና፣ ለምን (ሁሌም እንደምትለን) አንድ ብሄር ላይ አላከክ? ማለት፣ አገሩ ውስጥ ብዙ (የብሄር) ነፃ አውጪ ስብስቦች ነበሩ፣ አሁንም አሉ። ይሄን በስሜት ሳይሆን በሎጂክ እስኪ አስረዳን? ልረዳህ ብችል ብዬ ነው ጥያቄ ማንሳቴ።

ምንም ክፉ ቢወጣህ፣ ምናልባት ቢያንስ ራስህን እንደ ክፉ ታያለህ ተብሎ ስለማይታሰብ፣ የህወሃት መርህ ከኦነግ፣ ኦብነግ ውዘተ ወዘተ በምን ተለይቶ ነው፣ አንዱ ላይ ብቻ ማተኮርህ?

አበሩ፣ ቢያንስ፣ ትንሽ አስፍታው፣ ህውሃትና ኦነግ ብላለች።

ሱማሌ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል፣ ሲዳማ ወዘተ ወዘተ ከትግራይና ኦሮሞ ማህበረሰብ በምን ይለያሉ ይሄን ፌደራሊዝም በመፈለጋቸው ደረጃ?

ይሄን ሁሉ የምለው ለአንድ ወይ ሁለት ማህበረሰብ በተለየ ሁኔታ ለመቆርቆር ሳይሆን፣ ወይም ፌደራሊዝሙን ለመከላከል ሳይሆን፣ በርግጥ ጉዳዩ የተወሰነ ሰፈር አለመሆኑን፣ ይልቁኑ የብዙ ነው ከሚል ነው።

ይሄን ፌደራሊዝም የሚሻው፣ ህወሃት (ወይም ትግሬ) ብቻ ቢሆን እኮ፣ ሲጀመር አይተገበርም ነበር፣ ቢተገበርም ቶሎ ይገረሰስ ነበር። ያልገባኝ አንተ ግን የገባህ ነገር ምንድን ነው ይሄን በተመለከተ?

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by sarcasm » 10 Feb 2022, 08:35

አለቀ! ሕገ መንግሥቱ አይቀየርም። ሕገ መንግሥቱ ለድርድር አይቀርብም!

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: በብልፅግና ፓርቲ ለድርድር የማይቀርቡ ነጥቦች:- የፌዴራል ሥርዓቱ፣ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ፣ ሕገ መንግሥቱ

Post by Abere » 10 Feb 2022, 09:38

ሆረስ፤

--- የችግሮች እናት የሆነው የትግሬ ወያኔዎች የደደቢት ኢ-ህገ መንግስት ነው። በዓለም ላይ ጎሳ አገር ያለው፥ዜጎች ደግሞ አገር ዐልባ የሆኑበት ቦታ ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ኢ-ሳይንሳዊ እና ኢ-ማህበረሰባዊ የሆነ ስርዐት ማንም ሊያስቀጥለው አይችልም - በእራሱ የፈረሰ ነው። ቤት የሚሰራው በምድር ላይ ባለ መሰረት ነው እንጅ በአየር ላይ ቤት መስራት አይቻልም - ምናልባት ፊኛ ወይም ባሉን/Balloon/ ማንሳፈፍ ይቻላል። ዐብይ አህመድ የሚፈልገው በአየር ላይ የሚንሳፈፍ ፊኛ ከሆነ በእራሱ ላይ ይፈነዳል።

-- በመሰረቱ ውይይት ማለት፥የመወያያ አጀንዳ ሲኖር ነው። ያለ አጀንዳ ውይይት የለም። በዚህ መሰረት አገራዊ ውይይቱ በምን ጭብጥ ጉዳይ ላይ ነው። ጉዳይ የለም ማለት ነው። ስለዚህ ውይት አይኖርም - ግጭት እና ጦረነቱ ይቀጥላል ማለት ነው። የጠባብ የጎሳ ኩባንያወችን ፍላጎት ለመጫን ከሆነ ውይይቱ ሳይጀመር ፈርሷል። ይህ ደግሞ ዐብይ አህመድ እሞትለታልሁ የሚለው ህገ መንግስት ፈርሷል - አገራዊ አይደለም ኢ-ህገ መንግስት ነው። በውይይት ላይ ይህን አትንኩብኝ ይህን ብቻ ማለት አይቻልም። ዐብይ አህመድ ወይም ኦነግ አገራዊ አጀንዳውንም የማስያዝ ስልጣን የለውም ወኪልም ሊሆን አይችልም - አጀንዳውን የሚያቀርቡት ተወያይወች ናቸው። ከወትሮም የበለጠ አሁን በትክክል የደደቢት ኢ-ህገ መንግስት ተደምሥሷል። ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት ገብተናል ብቻ ነው ማለት የምችለው። በማን? በአብይ አህመደ እንዝህላልነት እና የሞኝ ሴራ። ሴራ ደግሞ ባለቤቱን ይበላል። ስለት ድጓሱን ሴራ ባለቤቱን ይሉ ዘንድ።

Horus wrote:
09 Feb 2022, 18:24
የኢትዮጵያ መሰረታዊ በሽታ የትግሬ ባንዳዎች በኢትዮጵያ ላይ የጫኑት የዘር ሕገ መንግስት ነው። ያ ነው የሚለወጠው ፤ የቀሩት ሁሉ ከዞያ የመነጩ ናቸው ። ያ የትግሬ ዘረኛ ወረቀት ካልተለወጠ በትክክል ኢትዮጵያ ዳግማዊ የካቲት አብዮት ይጠብቃታል።

Post Reply