እስከ ጥር 19፣ 2014፣ ድረስ የሰዉ ልጅ የስልጣኔ ታሪክ በነዚህ ሁለት ቃላት ይደመደማል ብዬ ኣስቤ ኣላዉቅም ነበር። ያለኝ ኣስተሳሰብ ትክክለኛዉ ነዉ ማለት ኣልችልም። ማንም ግለሰብ ለብቻዉ ለማለት የሚችል ኣይመስለኝም። ያለኝ ኣስተሳሰብ ግን ይህ ነዉ ማለት እችላለሁ።
በእኔ ኣስተሳሰብ የሰዉ ልጅ ስልጣኔ የጀመረዉ ህግ ከጦር በላይ መሆኑን የተረታ ግዜ ነዉ። ጥነት ግዜ። ያንን መረታት የምያሳይ ጦርን ኣጋድመዉ ህግ የማዉጣት ባህል ነዉ። ሴረ ቱማ ተብሎ። በህግ ኣምላክን ተቀብሎ። የጥንት ግሪክ ስልጣኔ ይህን ኣስተዉሎ። ፈላስፋዎችን ጥንት ግዜ ፈጥሮ።
ሴረ ህግ ማለት ነዉ። ሴራ የሚለዉ ቀጥሎ የመጣ ይመስላል።
ጦር ከህግ የበለጠ የመሰላቸዉ ሮማኖች የጥንት ግሪኩን ስልጥኔ ወረዉ ኣዳከሙት። ለፍተዉ ለፍተዉ ከራሳችን ባህል ያዳከምናቸዉ ባህል ይበልጣል ብለዉ ኣምጠዉ ያ ባህል ዳግም ይወለድ ማለትን ጀመሩ። በርቶላቸዉ። ኣብርሆት ብለዉ። ህዳሴ ብለዉ።
ከዛም ወደ ኣሜርካ የተሰደዱት ቀጥለዉ እስቲ እንሞክር ኣሉ። ሙከራ ብለዉ። 25 ግዜ ህገምንግስታቸዉን ኣሻሽለዉ። የ250 ዓመታት የታሪክ ዘመን ሳይሞለቸዉ። የኣለም የብርሃን ከፍታ እኛ ነን ብለዉ።
ይህን ሁሉ ዘመን ህግ ረቶናል ኣላሉም። ጥር 19፣ 2014፣ ከዘጠኙ የሃገሩ ዋና የህግ ኣስከባሪዎች ኣንዱ ያለዉ መረታት ሳይሆን ሙከራ ነዉ። ያሃገሪቱ የመጀመርያዉ ፕሬዝዳንትም ኣለ የተባለዉ ሙከራ ነዉ። መረታትን ሳይሆን።
በህግ የበላይነት የተረቱ በህግ የበላይነትን እንሞክር ከሚሉት ከቀደሙ መረታቱ ከሙከራዉ ቀደመ ማለት ነዉ። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ርኮኒንግ የሚባለዉን መረታት ያልኩኝ። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ኤክስፐርመንት የሚባለዉን ነዉ ሙከራ ያልኩኝ።
እነዚህ ሁለት ቃላት ናቸዉ የሰዉ ልጅን የስልጣኔ ታሪክ የደመደሙ የምላቸዉ። ሁለቱም ስለ ህግ የበላይነት ያላቸዉን ግንዛቤ የምያንጸባርቁ ናቸዉ ብዬ ኣሰላስዬ።