Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ - በጤና ችግር ያሉትን አቡነ መርቆሪዎስን ይዘው ወደ ጠ/ምኒስትሩ ቢሮ ሄደው ነው አሁን ሸራትን አንሄድም የሚሉት?

Post by sarcasm » 02 Feb 2022, 20:30

በጤና ችግር በአርምሞ ያሉትን ብፁእ ወቅዱስ [ብ]አቡነ መርቆሪዎስን ይዘው ወደ ጠ/ምኒስትሩ ቢሮ እንኳን ደስ አለን ለማለት ሄደው ነው ታድያ ሸራትን አንሄድም የሚሉት፧ ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ
sarcasm wrote:
08 Oct 2021, 21:03
በአርምሞ ላይ ብቻ ሳይሆን በጤና ችግር ላይ ያሉትን ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስን የፓለቲካ መሳሪያ አድርገው የሚጎትቱና የሚያዋርዱ ሆዳም ጳጳሳትም ማዋረድ የሙሉ ቀን ስራው የሆነው አምባገነኑ አብይ አህሙድም ይሁን መዋዘ ጥበባት ከቤተክርስቲያናችን ላይ እጃቸውን ቢያንስ የሚበጅ ይሆናል።

ሀገር የምትፈርስ ከሆነ የምትፈርሰው ወጥ ረግጠው እምነታችንን ሀይማኖታችንን ለማፍረስ መሞከር ነው። አደጋ አለው። እምነታችንን በተመለከተ ሳይሞቱ ሞተናል የሚሉ አታላይ ሆዳም እና አድር ባይ ጳጳሳትንም ይሁን መንግስት ተብዬውን አንታገስም።

እጃችሁን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ላይ አንሱ ካልሆነ የማትወጡት ነውጥ ውስጥ ትገባላችሁ። ይህ ዛቻ አይደለም ቃል ኪዳን እንጂ! ከብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ላይ እጃችሁን አንሱ!!! በእምነት ቀልድ የለም!!!

89 ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለውና ምእመናኖቿ እንደ ከብት ታርደው የበረከት ዘመን የሚሉ ጳጳሳትም ይሁን መዋዘ ጥበባት የምንሰማበት ምክንያት የለም!!! ከበጎቻቸው ፊት ቀድመው ወጥተው መታረድ መሰደድ ሲገባቸው ለሚያርዳቸውና ለሚያሳርዳቸው መንግስት ሺ አመት ንገስ የሚሉ ከሆነ ተጠራርገው ቤተ መንግስት ወይም ገደል መግባት ይችላሉ። ይኸው ነው።


Please wait, video is loading...