Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ፋኖ---> የአማራ ህዝብ ህልውናን የታደገው፤ ኢትዮጵያን የጠበቀው። እወነተኛ ፍቅር ነፃ ነው። ፋኖ ህይወቱን በነፃ የሰጠ የቁርጥ ቀን ኢትዮጵያ ጠባቂ።

Post by Abere » 02 Feb 2022, 11:31

ፋኖ---> የአማራ ህዝብ ህልውናን የታደገው፤ ኢትዮጵያን የጠበቀው። እወነተኛ ፍቅር ነፃ ነው። ፋኖ ህይወቱን በነፃ የሰጠ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ጠባቂ።
ብዙዎች የፋኖ ስም ሲነሳ እንደ በርበሬ ያስነጥሳቸዋል፡፡ እነርሱ ግን አገር ምጥ ውስጥ ስተወድቅ ሲፈለጉ አይገኙም - ከተገኙም መሳርያ እና ስንቅ እንደ ወደል አህያ ተሸክመው ለጥላት ይሰጣሉ። ኢትዮጵያ በአፋቸው ላይ እንጅ በልባቸው የለችም- ስለ አገር ብዙም ደንታ የላቸውም፥ ገንዘብ ከተገኘ ይሸጧታል። ጧት የተናገሩትን ለማታ አይደግሙትም። ፋኖ ግን ከዚህ የተለየ ነው ኢትዮጵያ ማህተሙ ነች። በደሙ ታትማለች። ጊዜ ሲቀየር አይለወጥም፥ ገንዘብ ብታወጣም አይሸጣትም። በዚህ ጽናቱ የፋኖ ወይም የአማራ ሲነሳ ያፍቃቸዋል፥ልባቸው በቃር ይቃጠላል። እነርሱ ያፍቃሉ፥ይቃጠላሉ እንጅ ይህን ማንነት መለወጥም:ማኮላሸትም አይችሉም። ሴረኛ ሰው እንደ ሰጋ ይኖራል ይሉ ዘንድ አሁን ሴራቸው በዐደባባይ ተጋለጠ ስለፋኖ ምኖር ስለ አማራ መተባበር እና መደራጀት ሲያዩ ማለቃቀስ ጀመሩ። የየዋሃን አምላክ በመጨረሻም የግፍ ጽዋ ሞልቶ ሲፈስ ከስንት አስርት አመታት በኋላ ተራው የአማራ ህዝብ በእግዜር ሃይል ረጅም እንቅልፉ ተነሳ። ለምን አሁን ተነሳህ ብለው የሚጮሁ የዲያብሎስ ወገኖች የሚገርሙ ናቸው። አዎን አማራ ተነስቷል፥የተነሳው ግን በእናንተ ግፍ ተገድዶ ነው። ከተነሳም የኢትዮጵያን ጎጅ ትህዋስያን ያጠፋል። አማራ የማይጠብቃት እና አማራ የማይኖርባት ኢትዮጵያ አትኖርም። እንድትኖር የሚፈልግ ካለም ፀረ-ኢትዮጵያዊ እና ፀረ-አማራ ነው።