ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተነካችው ዛሬ አይደለም። ኦርቶዶክስ የተነካችው ቤተክርስትያኗ እና ገዳሞቿ በውጪ ሀይል ተዘርፈው ሲወድሙ ነበር። ኦርቶዶክስ የተነካችው በአክሱም ፅዮን ደጃፍ እነዛ ሁሉ ሲገደሉ ነበር። ኦርቶዶክስ የተነካችው ልጆቿ ሲተራረዱ ነበር። ፓትርያርኩ እንደዛ መናገር አቅቷቸው በድብቅ ተቀርፀው ሲናገሩ እና ሲታፈኑ ነበር ኦርቶዶክስ የተነካችው። አባቶች በቤተክርስቲያን ጦርነት ሲያውጁ ነበር የተነካችው። ኦርቶዶክሳውያን ውጊያ ይቅር ቢሉ ምን ያህል ሰው ማትረፍ እንችል እንደነበር አስባችሁታል? ስለ እውነት የቆሙ አባቶችን ግን ሳላመሰግን አላልፍም።
ረሱል የላካቸውን ጃንደረቦች የተቀበልን የሚል የሀይማኖት መሪ አልነጃሺን የሚያክል ቅርስ ፈርሶ አይናገርም። ደም መፋሰስን በማስቆም የሚገኝ አጅርን ትቶ ስለ አደባባይ የሚናገሩትን ሳይ ያሳዝነኛል። የሀይማኖቱ መሪዎች ይህን ጦርነት ለማስቆም እና መስጊዶች እንዳይፈርሱ ለማድረግ ምን ያህል ሰርተዋል?? አስባችሁታል ይሄ ሁሉ ህዝበ ሙስሊም ጦርነት ይቁም ብሎ ቢወጣ የሚተርፈውን የሰው ብዛት?
ትላንት የሀይማኖት አባት የተባለው ፓስተር የወታደር ልብስ ለብሶ ሲፎክር አይቶ ተው ይሄ የእየሱስ መንገድ አይደለም ያላለ ዛሬ መስቀል አደባባይን ካልወረስኩ ብሎ ይመጣል። በጌታ ፊት በመስቀል አደባባይ መዘመር ሳይሆን ደም እንዳይፈስ መጮህ እና መስራት ነበር ዋጋ የነበረው። የprotestant መሪዎች ህዝቡን ለሰላም ቢያሰልፉት ሀገራችን ዛሬ እንዲህ ባልሆነች።
ስለ ሀይማኖት አልናገርም ብዬ ዝም አልልም። የሀይማኖት አባቶች ስራቸውን አለመስራት ነው ለዚህ ያበቃን። ይሄ ሁሉ አማኝ ባለበት ሀገር ሺዎች ሲተራረዱ እያየሁ የሀይማኖት አባቶችን አትናገር ብትሉኝ ቀልድ ነው።
Please wait, video is loading...