ጻድቃን ሲያስነጥስ ሸዋ ሮቢት ድረስ የሸሹ ደካሞችን ጀግና ብሎ ማርሻል ጀነራል ብሎ መሸለም የሚሊተሪ ዲስፕሊንን ማግማማት ነው!!![]()
![]()
ገዥዎቹ ቀልብ አጥተዋል።
ብዙ ስህተቶች እየተሰሩ ያሉ በገዥዎቹ ነው። ጦርነት ሲመጣ ምን እንደሚሆን አይተናል። ትንሽ ጋብ ያለ ሲመስል ደግሞ መልሰው የሚያዘናጉት ራሳቸው ናቸው። ገዥዎቹ ቀልብ እንደሌላቸው በዛሬው የማዕረግ እድገት ማየት ይቻላል። የሕግ ባለሙያዎቹ ተገኘ ዘርጋውና በላይነው አሻግሬ እንደፃፉት በመከላከያ ሰራዊቱ አዋጅ 1000/2011 መሰረት የመጨረሻው የሰራዊት ማዕረግ ጀኔራል እንደሆነ ይደነግጋል።
ሕገመንግስቱ ዝርዝር ጉዳይ ስለማይዝ፣ በሕገ መንግስቱ ተጠቅሶ አዋጅ ይወጣል። ያ አዋጅ አልተሻረም። ገዥዎቹ አቅል ከማጣታቸው የተነሳ ሕጉ ላይ ያለ እና የሌለ ነገር እንኳን እያስተዋሉ አይደለም።
