Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Prosperity Party's Library and TPLF's 52 Universities & 100,000 schools

Post by sarcasm » 06 Jan 2022, 09:00

የኢህአዴግ ትምህርትና የብልጽግና ላይብረሪ ወግ ....

By Finfinne Times


ኢህአዴግ 52 ዩኒቨርስቲዎችን ገንብቷል። በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ቢያንስ ከሶስት በላይ ትላልቅ ቤተመፅሀፍቶች ይኖሩታል። በመላው ሀገሪቱ የተገነቡ ቁጥራቸው ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት አይረሱም።

በዘመነ ኢህአዴግ ከተሰሩ መሰረተ ልማቶች በተለይ በትምህርትና በጤና ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች አስደናቂ ነበሩ።

በ2010 አመተ ልደት በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ከ30 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኙ ይፋ ሆኖ ነበር። በዘመነ ኢህአዴግ በተለይ ከ2003 በኃላ በአመት በአማካይ ከ100 እስከ 300 ሺህ ተማሪዎች ከመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ ሙያዎች ተመርቀው ይወጡ ነበር።

ካለው የህዝብ ቁጥር ከተጨባጭ የሀገራችን ሁኔታ አንፃር የትምህርት ተደራሽነት ላይ ትኩረት አድርጎ ቀስ በቀስ ወደ ትምህርት ጥራት ማተኮር አስፈላጊ ነበር። ኢህአዴግም በጨለማው 27 አመታት ውስጥ ይህንን በተግባር አሳክቶታል።

በእነዚህ ሂደቶች የትምህርት ፖሊሲን ጨምሮ የገጠሙ የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም ለአንድ ሀገር የእድገት መሰረት የሆነው ትምህርት ላይ ታሪክ በፍፁም የማይረሳው ስራዎች ተሰርተዋል።

ኢህአዴግ መሃይም ያልተማረ ፥ የደነዘዘ ምንም አይነት ጠቀሜታ የሌለው ትውልድ አፍርቷል ብለው ጭፍኖች ሲናገሩ እገረማለሁ። ትምህርትን ያስፋፋና በነፃ ያቀረበ መንግስት ላይ ትውልድን በመግደል ሲታማ እስቃለሁ።

የትምህርት ጥራት ፖሊሲው ፥ የሚያጋጥሙ አሉታዊ ተግዳሮቶች .. ወዘተ ይኖራሉ። ነገር ግን እጁን እየቆጠረ ሂሳብ የሚሰራ ፥ ትምህርት ምን እንደሆነ የማይታወቅበት ፥ ትምህርት ቤቶች ያልነበሩት አካባቢዎች ላይ ቢያንስ ቢያንስ አንድ ትውልድ እስከ አስረኛ ክፍል እንዲማር አድርጓል።

በእርግጥ ኢህአዴግ ጥቂት የመሃል ሀገር ሰዎች ልብ ወለድ የሚያነቡበትና የሚዝናኑበት ላይብረሪ አልሰራም ይሆናል። ነገር ግን መላው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች እንዲማሩ ያስቻለ የትምህርት ተደራሽነትና የእውቀት አብርሆት እንዲፈነጥቅ ያደረገ አስደናቂ ስራዎችን ሰርቷል። ማንም ቢክድ ታሪክ ግን በፍጹም አይክደውም !!

Finfinne Times
Please wait, video is loading...

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: Prosperity Party's Library and TPLF's 52 Universities & 100,000 schools

Post by Assegid S. » 06 Jan 2022, 12:42

ህወሃት በሃያ ሰባት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ ለኢትዮጵያ ዕድገት አስተዋፆ አበርክቼበታለሁ ብሎ ከሚጠቅሳቸው ዘርፎች መካከል በጣም በጣም እጅግ በጣም የሚያበሳጨኝ እና ለመስማትም ሆነ ለማንበብ የማልፈልገው የትምህርቱ ዘርፍ በተለይም የዮኒቨርሲቲዎች ግንባታና ቁጥር ሲጠቀስ ነው። ዩኒቨርሲቲን ዩኒቨርሲቲ የሚያሰኘው እኮ የድንጋይ ክምር ሳይሆን የዕውቀት ድምር ነው

ህወሃት ገንባሁት ከሚለን የዩኒቨርሲቲ ተቋማት ተምረው የሚወጡት ተመራቂዎች እኮ "ምሁራን" ሳይሆኑ ... በአጭር ቃል አእምሮ-ስውራን ናቸው፤ ማሰብ ማገናዘብ የማይችሉ! በተመረቁበት ዘርፍ የጠራ ዕውቀት ማካበቱን እናቆየውና ... even ድፍድፍ እንኳ የማይገኝባቸው ባዶ ጉድጓዶች።

ህወሃቶች፦ "መንገድ ሰራን" ፣ "ህንፃ ገንባን" ፣ ወዘተ ወዘተ ብላችሁ እንዳሻችሁ አውሩ፤ ግን እባካችሁ ፈጣሪንም ባታውቁ እንኳ በፈጠራችሁ ... ለጊዜውም ቢሆን ሥራ አጡን ማቆያ ተቋማት እንጂ "ዩኒቨርሲቲ" ገነባን ስትሉ አልስማችሁ።

Post Reply