Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37256
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 04 Jan 2022, 12:23

Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
6c2uiuui2Stonuc24h630o9e ·
አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከጃፓን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
******************
(ኢ ፕ ድ)

በሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከጃፓን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ታካሺ ሀቶሪ ( Takashi HATTORI) ጋር በኢትዮጵያና ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮ-ሱዳን ግንኙነት እንዲሁም በቅርቡ የተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር-ቤት ኢትዮጵያን በሚመለከት ባሳለፈው ውሳኔ ላይ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ስለአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይም አሸባሪው ቡድን በአገሪቱ ላይ ስለፈጸመውና እየፈጸመ ስላለው ወንጀል በዝርዝር በማስረዳት የተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር-ቤት እ.ኤ.አ ዲሴምበር 17 ቀን 2021 ዓ.ም ኢትዮጵያን በተመለከተ የፖለቲካ አጀንዳ ባላቸው አካላት አቀነባባሪነት ያሳለፈውን የተዛባ ውሳኔ ጀፓን መደገፏ አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸዋል።

አምባሳደር ይበልጣል በማያያዝም ጀፓን እንደ ወዳጅ አገር ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ኢ-ፍትሃዊ የውጭ ጣልቃገብነትን መቃወም ሲገባት የድጋፍ ድምፅ በመስጠት ለውሳኔው መተላለፍ ተባባሪ ሆና መገኘቷ ከወዳጅ አገር ያልተጠበቀ አቋም እንደነበር በማንሳት፣ የኢትዮጵያ መንግስት የተሰማውን ቅሬታ ለመንግስታቸው እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል።

የጃፓን አምባሳደርም በበኩላቸው የተ.መ.ድ የሠብዓዊ መብቶች ምክርቤት ያሳለፈውን ውሳኔም ሆነ የጃፓንን ድምጽ አሰጣጥ የተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው በመግለጽ፣ ጉዳዩን ለመንግስታቸው እንደሚያስተላልፉ ቃል ገብተዋል።

አምባሳደሩ ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ሠፊ ትብብር ያላት አገር እንደመሆኗ የኢትዮጵያን ሠላምና አንድነት በተመለከተ በቅርብ እንደምትከታተለው አንስተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ‼

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/ See less