በምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ በአማራ የፀጥታ ኃይሎች ጅምላ እሥር ግድያና መፈናቀል እንደተፈፀመ የሚናገረው "ያልተረጋገጠ" ያለው አዲስ ሪፖርት ዩናይትድ ስቴትስን በእጅጉ ያሳሰባት መሆኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ ዛሬ ገልጿል።
ካለፈው ዓመት ኅዳር ወዲህ ከምዕራብ ትግራይ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በኃይል መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስታወቁን መሥሪያ ቤቱ አስታውሶ
“ሁሉም የአማራ ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀምን ጥቃት እንዲያወግዙ” እንጠይቃለን ብሏል። “የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን” ሲል አክሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት አቤቱታዎቹን እንዲመረምርና ጥቃት ፈፃሚዎችን በተጠያቂነት እንዲይዝ፣ ሁሉን አሳታፊ የሆነ ግልፅ ምርመራ እንዲያደርግ፣ ሁከቱ እንዲቆም፣ ታጣቂ ወገኖች ሁሉ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ባልተገደበ ሁኔታ እንዲደርስ መሥሪያ ቤቱ ጠይቋል።
“ሁሉን አካታች ውይይት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲጀመርም ጥሪያችንን በድጋሚ እናሰማለን” ብሏል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ።
Continue reading https://amharic.voanews.com/a/state-dep ... 59305.html