Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ጉዳዩን በምን በኩል እንየው ...

Post by sarcasm » 20 Dec 2021, 19:28

ጉዳዩን በምን በኩል እንየው ...
By Finfinne Times


TDF በእነዚህ 30 ቀናቶች ብቻ ከ300 ኪሌሜትሮችን በላይ አፈግፍጓል። ብዙ ስትራቴጂካዊ ምሽጎችን ከተማዎችንም ለቅቆ ወጥቷል።

በእርግጥ TDF በሁሉም አቅጣጫ ለቅቋቸው የወጡ ከተማዎችን በጦርነት ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ ነው ለቋቸው የወጣው። ስልታዊ ማፈግፈግ ልንለው እንችላለን።
ከወር በፊት ደብረብርሃንን ከቦ የነበረው የTDF ሀይል በአንድ ጊዜ እስከ ወልዲያ ድረስ ለቅቆ ሊወጣ አይችልም። ምክንያቱም ወልዲያ ከትግራይ በጣም ቅርብ ናት። የTDF ስትራቴጂካዊ ማፈግፈግ የመጨረሻ ድንበር ወልዲያ ዙሪያ ይሆናል ተብሎ ተጠብቆም ነበር። ነገር ግን አልሆነም።

የሆነው ሆኖ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ግንባር ዘመቻ በኃላ ያሉትን ወታደራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መገለባበጦችን ስንመለከት ሂደቱን እንድንገመግመው ያደርገናል። በድጋፍ መነፅር ሳይሆን በገለልተኛ አይን ጉዳዩን ማየትም አለብን።

አሁን መቶ በመቶ የተረጋገጠ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የወረደ የድርድር ሰነድ ላይ የመንግስት ሰራተኞች እየመከሩ ናቸው። የብሔራዊ እርቅና ድርድር ኮሚሽን ሊቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወስኗል። በእኩል ሰአት የተጠና የዲፕሎማሲ የሚዲያ የአለምአቀፍ ተቋማት በትሮች መንግስት ላይ እየተሰነዘሩ ናቸው።

የፖለቲካ እስረኞችን አስመልክቶ ከከፍተኛ የብልፅግና ባለስልጣናት አፍ የተሰሙ ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እንደሚፈቱ ነው። የፕሮፓጋንዳው አጀንዳዎች ተቀይረዋል .. ከዘመቻ ወደ ንብረት ቆጠራ ተሸጋግሯል ፤

እንግዲህ በይፋ ሲገለፁ ሲገመቱ የነበሩ ወታደራዊ ዘመቻዎች ወሬ በሁለቱም በኩል ቀዝቅዟል። የጦርነት አንዱ ማሸነፊያ ነጥብ ፕሮፖጋንዳ ነው።
ደማቅ ፕሮፖጋንዳ የጠላትን ሀይል ስነልቦናዊ ሆነ አካላዊ ሁኔታውን ይበጠብጠዋል። ይህ ሁኔታ ሲቀዛቀዝ ነገሩን እንድንጠራጠር ያደርገናል።

በእርግጥ በብልፅግና በኩል በይፋ ስለ ድርድሩ እየተነገረ ቢሆንም ... በTDF ሆነ በOLA ብሎም በሌሎች ፓርቲዎች አፍ የተሰማ ተጨባጭ ነገር የለም።
የTDF ቃል አቀባይ የሆኑት ጌታቸው ረዳ ከወር በፊት በCNN ቴሌቨዥን ቀርበው በትግራይ የመንግስት አገልግሎት ከተጀመረ ፤ የሰብዓዊ እርዳታዎች ወደ ትግራይ እንዲገቡ ከተፈቀደ፤ ሁሉም የትግራይ መሬቶች ከተመለሱ ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን አስቀምጠው በመንግስት በኩል የሚፈቱ ከሆነ አማራና አፋር ክልል ያለውን የTDF ሰራዊት አስወጥተው ለመደራደር ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀው ነበር።

በእርግጥ ድርድር ሂደት ነው። በፖለቲካ ሜዳ በአንድ ጀንበር የሚጣላም የሚስማማም የለም። በጦርነት ታጅቦ የነበረን ጉዳይ ለመፍታት ደግሞ የጊዜ ሂደቶች ወሳኝ ናቸው። ተደራዳሪዎቹ ቅድመ ሁኔታዎቹ ላይ ከተስማሙ በጊዜ ሂደት ነው መተማመኖችን ፈጥረው ወደ ድርድር ጠረጴዛ የሚቀመጡት።

በአንፃሩ የድርድር ሂደት ካለ የአማራ ተስፋፊ ልሂቃንና የኤርትራ ጉዳይ ብሎም የመሬት ዘረፋ መፈፀሙ መረሳት የለበትም። ሌላኛው በትግራይ ክልል የተፈፀሙ የጦር ወንጀለኝነት ጉዳዮችን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስለያዘው ይህ ጉዳይ አያሳስብም።

በእኔ አይን ነገሩን ሳጠቃልለው ... ጠ/ሚ አብይና TDF በሰሜኑ የሀገራችን የፖለቲካ ቀውስ ላይ ለድርድር ከተስማሙ ያለጥርጥር የማረጋግጠው ነገር ...የአማራ ተስፋፊ ልሂቃንና ኤርትራ ላይ የተሰራ ቁማር አለ።

ቁማሩ እስኪበላ ድረስ የድርድሩ ሂደት አወዛጋቢ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ከቁማሩ በኃላ አስተማማኝ ከባቢ አየሮች ሲፈጠሩ በቅርቡ እንመለከት ይሆናል። እስከዛ ግን እያንዳንዱ በዚህ ሰአት እየተደረገ ያለው አጠቃላይ ሁኔታ በህዝቡ ስነልቦና ጉዳዮች ላይ ማጠንጠኛውን እንዳደረገ መናገር እንችላለን።

ስለ ድሮኗ ጥቃት እንደ ፖለቲከኛ ሆኜ መናገር ስላልፈለኩ ትቸዋለሁ።
Finfinne Times

Please wait, video is loading...