"ቀይ ሽብር በደሴ ፤"
#Alert
ደሴ ላይ ከሌላ አካባቢ የመጣዉ የድል አጥቢያዉ አርበኛ እና ነፍሱን ይዞ ሸሽቶ የሄደዉ ጀግና ነኝ ባዩ ሁሉ በስመ ፋኖና በሚሊሻ ልብስ እዛ በነበሩና ሸሽተዉ ባልሄዱ ንፁሃን ወገኖች ላይ ጁንታ በሚል ፍረጃና የዳቦ ስም በቂም በቀል፣ የተጣሉዋቸዉን በጥላቻ፣ በቢዝነስ ፉክክር፣ በቡና ቤት ሴት ሳይቀር የተጣሉትን ሁሉ ሳይቀር እየወነጀሉ ያለ ምንም ማጣራት ቀይ ሽብር ለመፈፀምና በደቦ ፍርድ ሰዉን ለመፍጀት፣ ለመጨፍጨፍ እየተዘጋጁ ነዉ።
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ከወራሪዉ ሃይሎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ባይኖራቸዉም የትግሬ ወራሪ ሃይሎች ሲመጡ ዉሃና ዳቦ ሽጣቹሃል የሚሉ ክሶች አሉበት
መሳሪያ ታጥቆ ጥርሱን አግጥጦ የመጣን ሃይል ማስተናገድ በምን መስፈርት ስህተት ይሆናል የሚሉት ነዋሪዎች እንቢ ብንል አዉሬዎቹ ነፍሳችንን ይነጥቁናል ብለዋል።
በዚህ ሰአት በደሴ ከተማ ዉስጥ "በስመ-ፋኖና በሚሊሻ"፣ የፖሊስ ሃይል ስም ያሉት ሃይሎች ግፍ ቀጥሏል! ምንም ዉስጥ የሌሉትን ንፁሃን ዜጎችን ጭምር የሞተ ሬሳ እያሳዩ ቀጣይ "አንተ, አንቺ ነሽ" በማለት ህዝቡን ሽብር ዉስጥ የከተቱት ሲሆን አስገድደው ጉቦ እስከ መጠየቅና እንቢ ወይም ብር የለንም ያሏቸዉንም ወሲባዊ ፍላጎት እስከ መጠየቅ ተደርሷል። ይሄም ጉድና ነዉር በማስረጃ የተገኘባቸዉ አሉ።
ጥብቅ ማሳሳቢያ!
"ይህንን የሚሰማ ማንኛዉም የወሎ አማራም ይሁን የደሴ ነዋሪ ከህግ ዉጪ የሚወሰድን የደቦና የቡድን የድል አጥቢያ አርበኞች እርምጃ በመቃወም እና ወገኖቻችንን በማዳን ለክልሉ ለመንግስት አካል አሳልፎ በመስጠት ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲያቀርቡ ሲል ነዋሪዎች መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።"
Please wait, video is loading...