የተዘበራረቀው ፎለቲካ .... By Finfinne Times
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው እለት... "ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን" .. ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ አሳልፏል። ኮሚሽኑ በደፈናው በቀጣይ ሊካሄድ ለታሰበው አጠቃላይ ሀገራዊ ብሔራዊ መግባባት የሚመራ ተቋም እንደሆነ ተነግሯል።
በእርግጥ አካታችነቱ ገለልተኝነቱ ስልጣኑ ተግባሩ .. ወዘተረፈ በህግና ዲሞክራሲ ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ በኩል ረቂቅ ህግ እስኪመጣ ድረስ በዝርዝር ስለ ኮሚሽኑ አሁን ላይ መናገር አይቻልም።
አብይ አህመድ ከ15 ቀናት የሿሿ የጦር ሜዳ ግንባር ማግስት ወደ ቢሮዬ ተመልሻለሁ ካለ በኃላ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ወጣ ባለ መልኩ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ ትኩረት ማድረጉ ያስጠረጥራል። በደፈናው የተደረገ ሳይሆን የታቀደ እንደሆነም መገመት ይቻላል።
TDF በወታደራዊ ስትራቴጂ እቅዶች ምክንያት ተቆጣጥሮ የነበረው አብዛኛውን መሬቶች መልቀቁን አስታውቋል። ይህ የእቅድ ለውጥ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የጦር ግንባር ዘመቻ ጋር መገጣጠሙ በእራሱ የሚያጭረው ጥርጣሬ አለ። በTDF ስልታዊ ማፈግፈግ አብይ አህመድ በእሱ ካምፕ ከፍተኛ የፖለቲካ ትርፍ እንዲያገኝም አስችሏል።
በድሮን ተፅዕኖ ብቻ ከ30 ከተማዎች በላይ መልቆቅ ጥያቄን ያጭራል። ምክንያቱም TDF ደብረብርሃን ለመድረስ የጠላት ከባድ ምሽጎችን ሰብሮና ብዙ ጦርነቶችን አድርጎ ነው የተጓዘው።
ታዲያ በድጋሚ በአዲስ ወታደራዊ ስትራቴጂ የሚመለስ ከሆነ ሌላ ጦርነት እንደሚኖር ጥርጥር የለውም። የድሮን ጥቃቱ በድጋሚ ላይኖር የሚችልበት ምክያንትም የለም።
ምንአልባት አሜሪካን ለአብይ አህመድ የድሮን ሽያጭ የሚያደርጉ ሀገራት ላይ ጫና አድርጋ ልታስቆም የምትችልበት መንገድ ይኖራል። ከዚህ በፊት ዱባይ ለኢትዮጵያ ድሮን እንዳትሰጥ ከልክላ ነበር።
በድጋሚ የፈቀደችበት ምክንያት በእራሱ አወዛጋቢ ነው። ቱርክ የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት የማትቀበል ሀገር ስለሆነች ደግሞ የድሮን ተፅዕኖ ሚና ሊቆም የሚችልበት አጋጣሚ አናሳ ነው።
ሌላኛው ነጥብ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ላይ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በዘር ማጥፋት ወንጀሎች የአሜሪካን መንግስት እስከ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ውድቅ የሆነው በዚህ ሳምንት ነበር። ይህ ውሳኔም የሚነግረን ነገር አለ።
የሆነው ሆኖ TDF ለቅቋቸው የወጡ ከተማዎች የተፈጠሩ የጦር ወንጀሎች በገለልተኛ ወገን ከተጣሩ ለመቀበል ፈቃደኝነቱን ገልጿል። የጦርነቱ ሂደት (የስርዓት ለውጥ) በዚሁ መንገድ ቀጣይ ቢሆን ኖሮ ይህንን ማለት አስፈላጊ አልነበረም።
የፌደራሉ መንግስት የተለቀቁ ከተማዎች ላይ እያደረገ ያለው ፈጣን የመንግስት አገልግሎቶችን የመመለስ ውሳኔዎች ብሎም የፕሮፓጋንዳ ማጠንጠኛው መቀየር ሌላ ጥያቄን ያጭራል።
እንደኔ ሀሳብ TDF በቀጣይ ሊያደርግ የሚችለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ምዕራብ ትግራይን መቆጣጠርና ከአማራ ክልል ጋር ያለውን የጦርነት ስጋት ተፅዕኖን ማጥፋት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ።
ከፌደራሉ መንግስት ጋር ለመደራደር እንደ ቅደመ ሁኔታ ያቀረባቸው ጥያቄዎች ምንአልባት በድብቅ የይሁንታ ውል ካላቸው ክልላዊ ውጥረቱን የመፍታትና የትግራይ ህዝብን ስጋቶች የማቃለል ስራን ያከናውናል።
ብሔራዊ መግባባቱ አቅጣጫ የሚያደርገው ህገመንግስቱን ስለሆነ ለ27 አመታት የነበረው የፖለቲካ የድንበር የአስተዳደር ጉዳዮች ተግባራዊ ሆነው ሊቀጥል ይችላል።
የአማራ ተስፋፊ ልሂቃን ይህንን ላይቀበሉ ይችላሉ። ነገር ግን ሽኩቻቸው የሚጀምረው አዝለውት ከመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ነው የሚሆነው። ምንአልባትም ዙሩ ከከረረ ሌላኛው ህግ የሚከበርበት ክልል ሶስት ሊሆን ይችላል። ገና ካሁኑ ማጉረምሞች እየተሰሙም ነው።
ብቻ ፖለቲካችን እንዳወዛገበን ይቀጥላል ....
Finfinne Times
Please wait, video is loading...





