Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ብሄራዊ መግባባት ለምን? - ኢስሃቅ እሸቱ

Post by sarcasm » 10 Dec 2021, 08:56

ብሄራዊ መግባባት ለምን?
╚════════════╝
.
እያበላላን ያለው የአገራችን የውስጥ ችግር በጦርነት ሊፈታ አይችልም። የፖለቲካ አስተሳሰቦችን እና ቡድኖችን በጠመንጃ ለማጥፋት በመሞከር ሊሳካ አይችልም። ችግራችን ሥር‐ሰደደ በመሆኑ ሥር‐ነቀል መፍትሄ ይሻል። ከፕሮፓጋንዳ ግብዓት ያለፈ ብሄራዊ መግባባት ያሻናል። ❝ለምን?❞ ለሚለው ጥያቄ የተወሰኑ መልሶችን ላስቀምጥ…
.
———
🌴 ⑴ አገሪቷ ባሳለፈችው እስካሁንም ያልሻረ የማንነት ድፍጠጣ እና አሁንም በዘለቀው ይህንኑ ሕመም የመካድ ችግር ምክንያት የብሄረ-መንግሥት ምሥረታው ላይ ጥልቅ ስንጥቃቶች በመፈጠራቸው፤
.
———
🌴 ⑵ በአገሪቱ የፖለቲካ ማኅበረሰብ መካከል የሚስተዋሉት እጅግ የሰፉ የታሪክ እና ትርክት ልዩነቶች ያለብሄራዊ መግባባት ሊፈቱ የማይችሉ በመሆናቸው፤
.
———
🌴 ⑶ በፖለቲካው መካረር እና "ሤራ መል" ባህሪ ምክንያት ማኅበረሰባዊ የጎንዮሽ ትስስሩ እየተበጣጠሰ እና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተዳከመ በመምጣቱ፤
.
———
🌴 ⑷ የረጅም ጭቆና ዋና መገለጫ የነበረው የማንነት ድፍጠጣ (አሲሚሌሽን) ፖሊሲ በከፊል ከተቀለበሰ በኋላ መልሶ እያኮበኮበ ያለው የዳግም ድፍጠጣ ዝንባሌ እና የፌደራሊዝም አደጋ ውስጥ መግባት አገር የመበተን አደጋ ስለጋረጠ፤
.
———
🌴 ⑸ የጥልቅ ችግራችን መገለጫ የሆነው አግላይ ጠቅላይነት እና የእሱ ውልድ የሆነው የመጠፋፋት ፍላጎት ተካርሮ በመሣሪያ ኃይል ገፊነት ዳግም ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ስለከተተን፤
.
———
🌴 ⑹ የፌደሬሽን እና የብሄር ብሄረሰብ ውክልና መርሆች ተጥሰው ጠመንጃ ዋና የመዳኛ ቋንቋ ሆኖ መምጣቱ የጨዋታውን ሕግ ቋሚ ቀውስ በሚፈጥር መልኩ ስለለወጠው፤
.
———
🌴 ⑺ በየትኛውም አገር ፖለቲካ ውሰጥ ሤራ ቢኖርም የእኛ አገር ፖለቲካ ግን ዲፎልት መገለጫው ራሱ "ሤራ" ወደመሆን ተሸጋግሮ መልካም አሥተዳደር እንዲጠፋ በማድረጉ፤
.
———
🌴 ⑻ ለረጅም ጊዜ ተተግብሮ ልናየው ያልቻልነው ዴሞክራሲያዊ ምኅዳር ከሕልምነት አልፎ በተግባር ይሠፍን ዘንድ የብሄራዊ መግባባት እና ዕርቅ መኖር የግድ አስፈላጊ ስለሆነ፤
Please wait, video is loading...