Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

ሰበር ዜና: አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይት ተይዟል!

Post by Ejersa » 18 Nov 2021, 09:21

አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ በንብረት ግምጃ ቤት ውስጥ የተቀመጠ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይት በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ተይዟል አሸባሪው የህወሓት ቡድን ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት ውስጥ እያከማቸ እና በኃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ግለሰቦችን በተላላኪነት እያሰማራ በበርካታ ንፁሃን ላይ አሰቃቂ እልቂት ሲፈፅም እንደቆየ ይታወቃል፡፡

ይህን የሽብር ቡድኑን ሴራ የተረዳው የከተማዋ ነዋሪ በተለያዩ ቦታዎች የሚመለከታቸውን አጠራጣሪ ጉዳዮችን ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እየሰጠ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ውስጥ በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከ1ሺህ 800 በላይ ጥይት ተይዟል፡፡

በቤተ ክህነቱ ግቢ በሚገኝ የንብረት ግምጃ ቤት ባለ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ማስቀመጫ ውስጥ በተደረገው ብርበራ የተገኘው 1 ሺህ 363 የብሬን እና 493 የሽጉጥ ጥይት ነው፡፡ በተጨማሪም 2 የጥይት ማስቀመጫ ሳጥኖች እና 1 የክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ካዝና ተይዟል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 1 ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ በስልክ፣ በአካል እና ሌሎች የመገናኛ አማራጮችን በመጠቀም እየሰጠ ያለው ጥቆማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።



Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: ሰበር ዜና: አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይት ተይዟል!

Post by Wedi » 18 Nov 2021, 09:47

tarik look at this!! Galla Abiy is destroying our country by appointing Crused lander Tigrayans as head of Ministry of Defense, Head of the church and CEO Ethiopia Airline and many others


Please wait, video is loading...


Meleket
Member+
Posts: 5071
Joined: 16 Feb 2018, 05:08

Re: ሰበር ዜና: አራት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ከ1 ሺህ 800 በላይ ጥይት ተይዟል!

Post by Meleket » 18 Nov 2021, 10:48

ፍቅር ወልድን ከሰማይ ወደ መሬት አወረደው ወይ አመጣዉ ይባላል።

እውነተኛ እምባ አማጽያኑን ከተምቤን ሸዋ አመጣቸው ሊባልም ይቻላል:mrgreen: እኒህ ድምጣቸው በብልጽግና ካድሬዎች የታፈኑ ቅዱስ የሃይማኖት ኣባት እያነቡ የጸለዩት ጸሎት ከላይ የተመለሰላቸው ይመስላል፡ ከማያዳለዉ ኣምላክ!
:mrgreen:
Meleket wrote:
08 May 2021, 04:48
...... የሃይማኖት ኣባቶች እንዲህ ሲያለቅሱ ማየት በጣም ያማል! እያዩ ያላዩ መምሰል ደግሞ ያስጠይቃል!

https://mereja.com/amharic/v2/503674

Post Reply