20m ·
በካርቱም ተቀማጭ ለሆኑ የአገር ውስጥና አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጡ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በካርቱም ተቀማጭ ለሆኑ የአገር ውስጥና አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጥተዋል።
አንዳንድ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከዕውነታው የራቀ የፈጠራ መረጃ በማሰራጨት የአገራችንን ገፅታ ጥላሸት እየቀቡ በመሆኑ ሱዳናዊያን እና ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ዕውነታውን እንዲረዱ መሥራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።
የአሸባሪው ቡድኑ ወደ አዲስ አበባ እየገሰገሰ እንደሆነና አዲስ አበባም ከበባ ውስጥ ናት በሚል የፈጠራ መረጃ በማሰራጨት ውዥንብር እየፈጠሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
በመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ቢሆን ኖሮ አሸባሪው ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ነበር ያሉት አምባሳደሩ በወሬና በሽብር የሚፈርስ አገርና ህዝብ ስለሌለን ኢትዮጵያ ባጠረ ጊዜ ሠላምዋን እንደምታረጋግጥ፣ በየግንባሩ በሠራዊታችን ስለተመዘገቡ ድሎችና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የተሰጠውን መግለጫ መመልከት ብቻ በቂ እንደሆነ ተናግረዋል።
አሸባሪው ትህነግ በአለማችን ያሉ አሸባሪዎች ሁሉ የፈጸሙትን ወንጀል አሟልቶ የፈጸመ፣ የሰውን ልጅ ብቻ ሳይሆን እንስሳትን ጭምር የሚገድል ወንጀለኛ መሆኑ እየታወቀ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ሌሎች አካላት ለዚህ ቡድን ሲወግኑ መታየታቸው አሳዛኝ እንደሆነ አምባሳደሩ ተናግረዋል።
ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ከመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅ መሆኑን፣ ነገር ግን ተጨማሪ አጀንዳ በመያዝ የአንድን አገር ሠላምና ደህንነት ለማወክ መተባበር ግን ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ ድርጊት መሆኑን ተናግረዋል።
የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት በቅርብ እንደሚከታተሉ፣ የሱዳንን ሠላምና ልማት ኢትዮጵያዊያን እንደራሳቸው ሰላምና ልማት እንደሚያዩት፣ አሁን አገሪቱ የገጠማትን ችግርም ቢሆን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሱዳናዊያን በራሳቸው የመፍታት ብቃቱ አላቸው የሚል ጽኑ- ዕምነት በኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ዘንድ እንዳለ መግለፃቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
