Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37229
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

Fb + Video Of Abiy Ahmed:ያለንበት ጦርነት መሠረታዊ ጦርነት ጥይቱ ሳይሆን የሀሰት ወሬው ነው!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 11 Nov 2021, 09:12

Natnael Mekonnen
18Smpt554olf7gt310of05h09 ·
ጥቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ባልተገባ ሁኔታ የወገንን መረጃ ጠላት እንዲያገኝ ማድረግ አይገባም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ በተካሄደዉ የአዲስ ወግ ዉይይት ላይ ነዉ፡፡
#Ethiopia : ያለንበት ጦርነት መሠረታዊ ጦርነት ጥይቱ ሳይሆን የሀሰት ወሬው ነው። በመሆኑም ጠላት ቢዋሽ የሚጠይቀው አካልም ሆነ እንዳይዋሽ የሚከለክለው የሞራል ቁመና የሌለው በመሆኑ እንዳሻው መዋሸትና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ያሰራጫል ሲሉ ተናግረዋል።
ይሁንና መንግሥት በመሰል ሁኔታ ውሸትን ማሰራጨትና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የመንዛት ፍላጎትም የሞራል ፍቃድም የለውም ብለዋል።
ሽንፈት ታሪካችን አይደለም፤ ለኢትዮጵያውያን ወደ ሰላም መመለስ ይፈልጋሉ። ይህንንም ግብ አድርገን እንሠራለን ብለዋል።
ዶ/ር ዐብይ ኢትዮጵያ ጥንታዊት ብትሆንም ባለፉት 30 አመታት ወንድማማችነትን የሚያላላ ብዙ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል።
አሁን የምንሠራው ሥራም ኢትዮጵያን አለት ላይ የመገንባት ታላቅ የሀገር ግንባታ ሥራ ነው፤
ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ አልፋ በፅናት ቀና ብላ የድል ታሪኳን ለሌሎችም የምታስተምር እንድትሆን በርካታ መስዋዕትነት እየከፈልን እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡



================================================================================================