Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
netsi
Member
Posts: 188
Joined: 06 Oct 2019, 04:29

ሰበር ዜና፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢያንስ ዘጠኝ ሠራተኞቹ እና የቤተሰብ አባሎቻቸው አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለጸ።

Post by netsi » 09 Nov 2021, 14:00

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢያንስ ዘጠኝ ሠራተኞቹ እና የቤተሰብ አባሎቻቸው አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለጸ።

ሮይተርስ የዜና ወኪል የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይን ጠቅሶ እንደዘገበው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደኅንነት ባለሥልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉትን የድርጅቱን ሠራተኞች ጎብኝተዋል።

የፈረንሳይ ዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ) በበኩሉ የተመድ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የዋሉት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ናቸው።
ኤኤፍፒ የዜና ወኪል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መሠረት በማድረግ መንግሥት በርካታ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል ሲል ዘግቧል።

የዜና ወኪሉ ጨምሮም አንድ ምንጭ "አንዳንዶቹ ከመኖሪያ ቤታቸው ነው ተይዘው የተወሰዱት" ሲሉ ተናግረዋል ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በፀጥታ ኃይሎች ተይዘዋል የተባሉትን ሠራተኞቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እንደጠየቀ ሮይተርስ የድርጅቱን ቃል አቀባይን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በጉዳዩ ላይ መንግሥት እስካሁን ያለው ነገር የለም። ሮይተርስ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉን አስተያየት ለማካተት ያደረኩት ጥረት አልተሳካም ብሏል።

መንግሥት ከአንድ ወር በፊት "የአገሪቱን ሉአላዊነትን የሚጥስና ለብሔራዊ ደኅንነት ስጋት የሚሆኑ ድርጊቶችን ፈጽመዋል" ያላቸውን ሰባት የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ማባረሩ ይታወሳል።

30/02/2014

ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ

netsi
Member
Posts: 188
Joined: 06 Oct 2019, 04:29

Re: ሰበር ዜና፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢያንስ ዘጠኝ ሠራተኞቹ እና የቤተሰብ አባሎቻቸው አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለጸ።

Post by netsi » 10 Nov 2021, 09:56

netsi wrote:
09 Nov 2021, 14:00

Post Reply