4htp0f0741gh75hhu9et57d5 ·
ልዩ መረጃ
አቡነ በርናባስ በትግራይ ነጻ አውጪው የህወሓት ጉጀሌ ሽብርተኛ ወራሪ ኃይል ታፍነው ተወሰዱ
#Ethiopia : በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን የዋግኸምራና የካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ በርናባስ በህወሓት ወራሪ ኃይል ከሰቆጣ ከተማ ታፍነው መወሰዳቸው ምንጮች ገልፀዋል።
አቡነ በርናባስ የህወሓት ወራሪ ኃይል ዋግኸምራን ከወረረ በኋላ ሕዝብን በማስተባበር በትህነግ ዘረፋ ምክንያት ለርሃብ የተዳረጉትን ሲያግዙ መቆየታቸው ታውቋል። የትህነግ ወራሪ ኃይል ሰቆጣ ከተማን ሲዘርፍ ያወገዙት አቡነ በርናባስ ሕዝብ ችግሩን እንዲቋቋም ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው ከአካባቢው ተፈናቅለው የመጡ ነዋሪዎች ገልፀዋል። የትግሬ ወራሪ ኃይል ዘረፋ የተቃወሙትና ሕዝብን በማስተባበር ችግሮችን ለመቅረፍ ሲሰሩ የቆዩት አቡነ በርናባስ ጥቅምት 26/2014 ዓ/ም በትግሬ ወራሪ ኃይል ታፍነው መወሰዳቸው ታውቋል።
የትግሬ ወራሪ ኃይል የዋግኸምራ ነዋሪዎች ላይ ድብደባ፣ ግድያና እገታ እየፈፀሙ እንደሆነ ተፈናቃዮች ገልፀዋል። ባለሀብቶችን በየቤታቸው እየገቡ በመደብደብ፣ አፍኖ በመውሰድ እንዲሁም በመግደል ሀብትና ንብረታቸውን እንደዘረፉ ምንጮች ገልፀዋል። የትግሬ ወራሪ ኃይል አቡነ በርናባስን አፍኖ ወስዶ ድብደባ ፈፅሞባቸዋል የሚሉ መረጃዎች እንዳሉም ተገልፆአል።
