Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5071
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 09 Nov 2021, 04:49
ኣዪ ኢትዮጵያ ፓትሪያርኩ ሙፍቲዉና ካርዲናሉ የት ሄደው ነው ኦቦሳንጆ መንግሥትንና “ኣማጺያኑን” ሚያሸማግሉት፧?
እኒህ ሶስት ሰዎች እድሉ ልክ እንደ ኦቦሳንጆ ቢመቻችላቸው፡ ኢትዮጵያዊ እውነታን በመጋፈጥና በማፍረጥረጥ፡ ዘለቄታዊ መፍትሔን ይዘው እንደሚያሸማግሉ ሚሊዮኖች ያምናሉ።
ከዚህ በፊት በነዚህ ኣካላት እርቁ ተሞክሮ ነበር የሚሉ ሰዎች ኣይጠፉም፡ እርቅ ለማምጣት ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አይገባም። ኦቦሳንጆም ቢሆኑ ባንዴ ችግሩን ኣይፈቱትም ሶስቴ አራቴ መመላለሳቸው አይቀርም!
ላበሾች የሚያምርባቸው በራሳቸው የሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ችግራቸውን ቢፈቱ ነው። ያለ አንዳች ‘ሪሞርኬ’ ለነዚህ ሶስት የሃይማኖት አባቶች እድሉን ቢሰጡ ኢትዮጵያዊ ውበት ያለው ፈውስ ከውስጥ ማግኘት በቻላችሁ ነበር፡ ብለን ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንመክራለን። ኦቦሳንጆ ደግሞ እነ ሚኒልክ ሳልሳዊ እንዳሉት ኣገራቸው ሄደው የቦኮሃራምን ቀውስ ይፈቱ ዘንድ “የቤት ሥራ” ይሰጣቸው! ኣይሆንም በነዚህ ሶስት አካላት ኣንሸማገልም የሚል ኣካልም “ባዕድ ኣምላኺ” መሆኑን ለሰፊዉ የጦቢያ ህዝብ በገዛ ድርጊቱ ይመሰክራል።
ሰላምና ፍቅር ለታላቋ ስጦቢያ! 
-
Meleket
- Member+
- Posts: 5071
- Joined: 16 Feb 2018, 05:08
Post
by Meleket » 03 Dec 2021, 08:47
ታላቋ ኢስጦቢያ ሞኝ ኣይሉሽ ተላላ፣
ምን ዓይነት ጋኔን ነው ልጆችን ሚያባላ?
ሰላም የሚያሰፍን ፍጠሪ ኣንድ መላ።
እስቲ ቆም ብለሽ አንድ ግዜ አስቢ፣
የማዕዘኑን ድንጋይ ከውስጥሽ ጥረቢ፣
በእጆችሽ ወርቅም ሰላምሽን ገንቢ፣
እንዲያው በፉክክር ዘላለም ኣታንቢ።
Meleket wrote: ↑09 Nov 2021, 04:49
ኣዪ ኢትዮጵያ ፓትሪያርኩ ሙፍቲዉና ካርዲናሉ የት ሄደው ነው . . ። ፧?
. . .
ላበሾች የሚያምርባቸው በራሳቸው የሃይማኖት አባቶች አማካኝነት ችግራቸውን ቢፈቱ ነው። ያለ አንዳች ‘ሪሞርኬ’ ለነዚህ ሶስት የሃይማኖት አባቶች እድሉን ቢሰጡ ኢትዮጵያዊ ውበት ያለው ፈውስ ከውስጥ ማግኘት በቻላችሁ ነበር፡ ብለን ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንመክራለን። . . .
ሰላምና ፍቅር ለታላቋ ስጦቢያ!