ሆረስ ነኝ፣ ቃላት መፍለጥ አልወድም ። ነገሩ እንደ ሚከተለው ነው።
አንድ፣ የሱዳን ኩዴታን ያቀናበረው አሜሪካ ነው። ለምን?
ሁለት፣ አሜሪካ የግብጽና ሱዳን ጥምር ተላላኪ፣ ፕሮክሲ ሃይል በአፍሪካ ቀንድና ቀይ ባህር ይፈልጋል። ለምን?
ሶስት፣ አሜሪካ እንደ ዋና ጠላታቸው እየተዋጉ ያሉት ከቻይና፣ ሩሲያ፣ ኢራንና ቱርክ ጋር ነው። ስለሆነስ?
አራት፣ እነዚህ አራት አገሮች ማለትም ቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክና ኢራን በአፍሪካ ቀንድ፣ በቀይ ባህር፣ በህንድ ውቂያኖስና በአረብ ሰላጤ ሃይላቸውን በከፍተኛ ደረጃ አጠናክረው በግልም በቅንጅትም አሜሪካንን በመፎካከር ላይ ይገኛሉ ። ስለሆነስ?
አምስት፣ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ አፍሪካ መግቢያ በር ብቻ ሳይሆን የቀይ ባህርና ህንድ ውቂያኖስ መተላለፊያ በሮች ናቸው። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረትና አህጉር ውስጥ የምታደርገው የመሪነት እንቅስቃሴ አሜሪካንን በጣም ማስደንገጥ ብቻ ሳይሆን አናዶአቸዋል።
በመሆኑም የሃያላኖች ትግል፣ ፉክክር፣ ትብብር ሁሉ እኛን ለመቆጣጠርና ተላላኪ ፣ ፕሮክሲ ክላየንት አገሮች ለማድረግ ነው። ዋናው ጉዳይ የቻይና እና ሩሲያ ኢራን ቱርክ ጥቅም ካካባቢው ማስወገድ ያሜሪካ ብቸኛ አላማ ስለሆነ። እናስ?
ስድስት፣ ግብጽ ከወዲሁ ተላላኪ መንግስት ነች፣ በተለይ የግብጽ ወታደራዊ እና ሴኩሪቲ ሃይል። በሱዳን ተላላኪ ያልሆነ ሉዓላዊ መንግስትና ወታደር እንዲኖር አሜሪካ በፍጹም አትፈልግም ። የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ያገር ኢኮኖሚ የሚቆጣጠር ኮርፖሬት ድርጅት ስለሆነ ለሱዳን ነጻነት ሳይሆን ለኢኮኖሚ ጥቅሙ የቆመ ሃይል ነው ። ስለሆነም አሜሪካ እጅግ ተፈላጊ ተላላኪ ፕርክሲ አግኝቷል። ለዚህ ነው የመንግስት ስልጣን እንዲይዝ የተደረገው። ያሜሪካ መግለጫ፣ እቀባ ዉሸት ሚስኢንፎርሜሽን ነው ። እናስ?
ሰባት፣ ኢትዮጵያ የአሜሪካ ተላላኪነት እምቢ ብላ፣ ላሜሪካ አልበረከክም ብላ ብሎም ድጋፍ ለማግኘት ከቻይና፣ ሩሲያ፣ ቱርክ እና ኢራን ጋር የቅርብ ወዳጅነት የገነባች አገር ነች ። ስለሆነም አሜሪካ ከነሩሲያና ቻይና ጋር ለመታገል ኢትዮጵያን ዲእስታቢላይዝ ማድረግ፣ ከቻለም ያቢይን መንግስት በተላላኪ መንግስት ለመተካት እየሰራ ነው ያለው።
ስምንት፣ ይህም በመሆኑ የሱዳን መፈንቅለ መንግስት አሜሪካ በሱዳንና ግብጽ ፕሮክሲ ተላላኪነትና በትግሬና ኦነግ ሸኔ ያገር ውስጥ አሽከርነት በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊና ኢመደበኛ ጦርነት ለማድረግ ታስቦ የተወሰደ እርምጃ ነው ።
ኢመደበኛ (ኢሬጉላር) ጦርነት የሚባሉት እጅግ የረቀቁት የ21ኛው ዘመን ጦርነቶች ሲሆኑ እነሱም የኢንፎርሜሽን ጦርነት፣ የሳይኮሎጂ ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ጦርነትና የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ጦርነቶች ናቸው ።
አሁን በያዝነው ወቅት አሜሪካና አውሮፓ አምስቱንም የጦርነት አይነቶች በኢትዮጵያ ላይ እያካሄዱብን ነው ።
1. ወታደራዊ ጦርነት በትግሬ ባንዳዎችና የሱዳን ወራሪ ጦር፤
2. የፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጦርነት ተመድን ጨምሮ
3. የኢኮኖሚ እቀባ ጦርነት
4. ግዙፍ የሆነ የኢንፎርሜሽን ጦርነት በምዕራብ ሚዲያ ሁሉ
5. ግዙፍ የሳይኮሎጂ ጦርነት፣ ለምሳሌ ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው፣ ረሃብ፣ ፋሚን፣ ውዘተ
ባንድ ቃል የሱዳን ኩዴታ ኢትዮጵያን ለመውጋት የተደረገ ዝግጅት ነው ። ያገሬ ሰው ንቃ! ንቃ! ንቃ!
አሜሪካ ለምንድን ነው በሱዳን መፈንቅለ መንግስት ያደረገው? የሆረስ ትንተና ና ትንቢት!
Last edited by Horus on 28 Oct 2021, 12:35, edited 4 times in total.
Re: አሜሪካ ለምንድን ነው በሱዳን መፈንቅለ መንግስት ያደረገው? የሆረስ ትንተና ና ትንቢት!
ይህ ስሙ! የቀን ጉዳይ ነው! ይህ ያሜሪካ ኩዴታ ነው !!