1.በደሴና ኮምበልቻ ግንባር፣ በአፋር ግንባር፣ በገረገራ ግንባር እና በዛሬማ ግንባር ለምትገኙ የፋሽስት አብይ አህመድ ቡድን ሰራዊት አባላት
ሁሉም ሊባል የሚችል የፋሽስቱ ሰራዊትና አለ የተባለ የጦር መሳርያዎች በደሴና በኮምበልቻ አከባቢ በማሰለፍ የቀቢፀ ተስፋ መንፈራገጥ ሙከራዎች ቢያደርግም፣ ሁሉም ሙከራዎች ከሽፈው ፍልሚያው በትግራይ ሰራዊት ድል አድራጊነት እየተጠናቀቀ ስለሆነ ሁላችሁም የፋሺስት አብይ ቡድን ሰራዊት አባላት ባለቀለትና በማትጠቀሙበት ውጊያ ህይወታችሁን እንዳታጡ፣ ከቤተሰቦቻችሁ ጋር በሰላም እንድትኖሩ፤ ይህን ስርአት ፍፃሜው አፋፍ ላይ ስለሆነ እነዚያ ከኋላ ሁነው ግቡ እያሉ የሚገድላቹ የፋኖ፣ የአማራ ልዩ ሃይል እና አለቆቻችሁም ጭምር አከርካሪያቸው ተሰብሮ በመበታተን ላይ ስላሉ፣ መተኪያ ለሌላት ህይወታችሁ በከንቱ እናዳታጠፉ በግልም ይሁን በቡድን ሳትውሉ ሳታድሩ በሰላም እጃችሁ ለትግራይ ሰራዊት እንድትሰጡና ግብኣተ መሬቱ እየተቃረበ ካለ የፋሽስቱ ስርኣት ጋር ተያይዛችሁ ከመጥፋት ህይወታችሁን እንድትታደጉ ሲል የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በጥብቅ ያሳስባል።
2. ለከፍተኛ እና ለበታች የአብይ ኣህመድ ፋሽሽት ቡድን መኮንኖች
ለኣምባገነኑ የኣብይ ኣህመድ ፋሽሽት ቡድን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘምና የስልጣን ጥማት ለማርካት ስትሉ የብዙ ሺ ሰራዊት ህይወት የቀጠፈ ጦርነት ከኋላ ገዳዮች መድባቹ በጥብቅ እንዲፈፀም ስታደርጉ ቆይታቹሃል፡፡ ሕገ-መንግስት በመጣስ ከባእድ ሰራዊት ጋር ሽርክና በመፍጠርና በመተባበር መብቴ ይከበር ባለ የትግራይ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍና በደል ፈፅማቹኋል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ባደረገው ትግል የኣብይ ኣህመድ ፋሽሽት ቡድን ሽንፈትና ውርደት ተቃርበዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በደሴና ኮምቦልቻ መሽጎ በውትህድርና ያልሰለጠኑ ወጣቶች ግቡ እያለ ሊያስጨርስ ባለቀና ሽንፈቱ በታወቀ ኣጥፍቶ ለመጥፋት እየቃሰተ ስለሚገኝ ካለፈ ትምህርት ወስዳቹ ፤ያለፈ ጥፋት ይበቃናል ብላችሁ ፀሓይ ከጠለቀችበት የኣብይ ኣህመድ ፋሽሽት ቡድን ጋር እንዳትጠፉ እያገለገላችሁት ያለ ሀገርና ተቋም ከውድመት እንድታድኑ እንዲሁም የምትመሩት ወታደር በከንቱ ዓላማ እንዳያልቅ ጦርነቱ በማቆም ሃላፊነታቹ እንድትወጡ ጥሪ እያቀረብን እስከ ኣሁን ድረስ ስትተባበሩ ለቆያችሁ ግለሰቦች ሀገር ከውድመት ለመታደግ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
3.ለደሴና ለኮምበልቻ ህዝብ
የደሴና ኮምበልቻ ከተማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች ናቸው። በተለይ ኮምበልቻ የኢንዱስትሪ ማእከል መሆኗ የትግራይ ሰራዊት አሳምሮ ስለሚረዳ የሰራዊታችን ወታደራዊ ኢላማዎች፣ ከነዚህ ከተሞች ውጭ አድርጎ ጠላትን ድባቅ ለመምታት ኣልሞ እየተዋጋ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በቅርቡ፣ በሃይቅ ከተማ በተካሄደው ውግያ መስጊዶች፣ ቤተክርስትያናት፣ ቤቶችና ድርጅቶች እንዲሁም ከተማ የውጊያ ማእከል በማድረግ የቀቢፀ ተስፋ ሙከራዎች እያደረገ ሲሆን ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ግን ጥበብ በተሞላበት፣ ህዝብ ሳይጎዳ ጠላትን በመደምሰስ ድል በመቀዳጀት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።
ነገር ግን አሁንም ቢሆን ሃላፊነት የማይሰማው የጠላት ሃይል የደሴና የኮምበልቻ ከተሞች ቤተ እምነቶች፣ ድርጅቶች እና ቤቶች እንዲሁም መሃል ከተማ የውጊያ ቀጠናዎች እንዳይሆኑ ለመከላከል የትግራይ ሰራዊት ለህዝብ ደህንት ሲል ከፍተኛ ግምት በመስጠት፣ ውጊያው ከከተማ ውጭ እንዲሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል። ነገር ግን የፋሽሽት አብይ አህመድ ሰራዊት ይህን በመጣስ ውጊያው በከተማ መሃል ለማድረግ ከሞከረ እምቢ እንድትላቸውና ራስህን እንድትከላከል፣ ልጆችህ እና ድርጅቶችህን እንድትጠብቅ የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ በጥብቅ ያሳስባል።
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ
ጥቅምት 17/ 2014 አ.ም
Please wait, video is loading...
503