t31ho1nsoe ·
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የደስታ መግለጫ ላኩ
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደስታ መግለጫ መላካቸውን የውጭ ጉዳይ ሚስቴር አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በደስታ መግለጫቸው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
በቀጣይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ ነው የገለፁት።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያችሉ ስምምነቶች መፈረማቸው ይታወሳል። See Less
