Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
MatiT
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 16 Feb 2013, 10:18

ህወሀት "በእንግሊዘኛ ተወረርን፣ በትግርኛ ዜና ሀወት፣ በአማርኛ ከተሞችን ተቆጣጠርን ፕሮፓጋንዳዋ ተጋለጠ"!!

Post by MatiT » 14 Oct 2021, 16:01

አሜሪካ ጫናዋን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክራ እየመጣች ነው። ሰሞኑን እየተካሄደ ባለው ጦርነት የህወሀት ነገር ረብሿታል። ከመንግስት ምንም ዓይነት መረጃ ባይገኝም ሾልከው ከሚወጡ መረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው ህወሀት በሁሉም ግንባሮች እየተወቀጠ ነው። ከሰማይና ከምድር በሚወነጨፉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እሳቶች የሰው ሃይሉና የመሳሪያ አቅሙ በከፍተኛ መጠን ከጥቅም ውጪ ሆነውበታል። የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ዙር የጀመረው ጥቃት ህወሀትን ከገጸ ምድር ለማጥፋት እንደሆነ ይነገራል። በህወሀት በኩል በእንግሊዘኛ ተወረርን፣ በትግርኛ ዜና ሀወት፣ በአማርኛ ከተሞችን ተቆጣጠርን ፕሮፓጋንዳው አልተቋረጠም። አሜሪካ የህወሀት የድል ወሬ መሬት ላይ እንደሌለ ታውቃለች። ሁኔታው አላማራትም። በጥፍር፣ በጥርስ ጭምር ቧጭራና ነክሳ ልታድነው የተሟሟተችለት ህወሀት እስከወዲያኛው ሊሰናበትባት እንደሆነ ተረድታለች። የመጨረሻውን የኢትዮጵያ መንግስትን ማንበርከኪያ ይሆናል ብላ ያቀደችውን እርምጃ ልትወስድ መሆኗን ፍንጭ ሰጥታለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታን መርጧል። እየተካሄደ ስላለው ጦርነት መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል። የህዝብን መረጃ ከማግኘት መብት ጋር ካየን የመንግስት ዝምታ ትክክል እንዳልሆነ ይገባናል። ይሁንና ለምን ከዚህ ውሳኔ ለመድረስ እንደተፈለገ ምክንያት ይኖራል ብሎ መገመትም ይቻላል። የህወሀት የድል ፕሮፓጋንዳ ከጣርና ሲቃ የመነጨ፣ በደም ስካር ውስጥ ሆኖ የሚደረግ የነፍስ ውጪ፣ ግቢ ትንቅንቅ ስለመሆኑ በግሌ ጥርጣሬ የለኝም። የአሜሪካ አፍጣና አግጣ የመምጣቷ ነገር የሚያመላክተው የህወሀትን በአሸናፊነት መገስገስ ሳይሆን በተቃራኒው ወደማይቀረው ሞት እየተንደረደረ በመሄድ ላይ መሆንን ነው። እንደህወሀት ፕሮፖጋንዳ ቢሆንማ ኖሮ ይህን ጊዜ አሜሪካ ስለማዕቀብ ማስፈራሪያውን ከማዥጎድጎድ ይልቅ ድምጿን አጥፍታ፣ የህወሀትን የአዲስ አበባ ምኞት እውን ለማድረግ በስውር መንገድ በመጥረግ ትጠመድ ነበር።

ረቡዕ ዕለት የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አሜሪካን የኢኮኖሚ ቅጣት ኢትዮጵያ ላይ ለማሳረፍ ከጫፍ መድረሷን በማስጠንቀቅ አስታወቁ። ዛሬ የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ለአፍሪካ ሀገራት አሜሪካን ከሰጠችው ከቀረጥ ነጻ የሆነ ምርቶችን የማስገባት እድል(AGOA) ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያን በተመለከተ ውሳኔው በቅርብ ይፋ እንደሚሆን ገለጹ። ሰሞኑን የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አፍሪካውያንና አውሮፓውያንን በቪዲዮ ኮንፍረስ ጠርተው የኢትዮጵያን መንግስት እጅ ለመጠምዘዝ ስለሚቻልበት መንገዶች መምከራቸው የሚታወቅ ነው። አሜሪካ እረፍት አጥታለች። ከመቃብር ፈንቅላ፣ ህይወት ዘርታ ቆሞ እንዲሄድ የረዳችው ህወሓት ዳግም ወደመቃብር እንዳይገባ ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ ገብታለች።

የሀገር ልዑላዊነትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚዛን ላይ ተቀምጠዋል። የሀገር ክብርና ኩራት ከቁስ ነገሮች ጋር ለምርጫ ቀርበው ከኢትዮጵያውያን ፊት መጥተዋል። ኢትዮጵያ ሁነኛ የታሪክ ምዕራፍን ተጠግታለች። በዚህን ዘመን የምትወስደው እርምጃ የመጪውን ትውልድ እድል እጣ ፈንታ የሚወስን ይሆናል። የሀገር ልዑላዊነትን ወደ ጎን አድርጋ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ከመረጠች የልጆቻችንና የልጅ ልጆቻችን ህይወት በምዕራባውያን መዳፍ ውስጥ ገብቶ በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ቀንበር ሲማቅቁ የሚኖሩ ይሆናል። ክብርና ኩራታችንን ለቁስ አሳልፈን የምንሰጥ ከሆንን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከካርታ ላይ በአጽሟ ቆማ የምትታይ፣ ህይወት የሌላት፣ ማንም እየተነሳ የሚረግጣትና የሚያሽከረክራት ሀገር ሆና ትቀራለች። ምርጫው ግልጽ ነው። ሌላ በአማካይ የሚታይ አማራጭ ፈጽሞ የለም። ነጭና ጥቁር እንጂ ግራጫ የሆነ ምርጫ አልቀረበልንም።

የኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ባለው አቋሙ የሀገር ሉዑላዊነትን መርጧል። የኢትዮጵያን ክብርና ኩራት ለማስከበር እስከቀራኒዮ ድረስ እንደሚዘልቅ አስታውቋል። ለስንዴ እርዳታ ተብሎ በልዋጭ የሚሰጥ የኢትዮጵያ ክብር እንደማይኖር ፈርጠም ባለ ሁኔታ ምላሹን ሰጥቷል። የትኛውም የምዕራባውያን አርጩሜ እንደማያስጎነብሰው በግልጽ ቋንቋ አሳውቋል። በኢትዮጵያ ቆይታዬ ከክልል ፕሬዝዳንቶች ጀምሮ ያነጋገርኳቸው ሚኒስትሮች በአንድ አይነት ስሜትና መንፈስ የኢትዮጵያን ክብር ለማስጠበቅ ቁርጠኛ አቋም ላይ መሆናቸውን አረጋግጬአለሁ። በአንዲት ቅጽበታዊ አጋጣሚ ያገኘኋቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድም መንግስታቸው በምዕራባውያን ጫና የሚንበረከክ እንደማይሆንና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ልዑላዊነት ለማረጋገጥ ከምንግዜውም በላይ በጠንካራ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ገልጸውኛል። ይህ የመንግስት አቋም እስከመጨረሻው የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአድዋ ድል ታሪክ በመድገም የእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን በማሸነፍ ለመላው ጥቁር ህዝብ አርዓያነቷን ታረጋግጣለች።
መሳይ መኮንን

Aba
Member
Posts: 4018
Joined: 15 Apr 2011, 17:52

Re: ህወሀት "በእንግሊዘኛ ተወረርን፣ በትግርኛ ዜና ሀወት፣ በአማርኛ ከተሞችን ተቆጣጠርን ፕሮፓጋንዳዋ ተጋለጠ"!!

Post by Aba » 14 Oct 2021, 16:30

Moron shaebi,
"ኣሳን መብላት በብልሃት::" What do you want them to say, that they're kicking everybody's asz? Fool.
:lol: :mrgreen: :lol:
MatiT wrote:
14 Oct 2021, 16:01

Post Reply