
ያበሎ፥
ስለ ስልጣኔ ኣጫጭር ጥያቄዎች ልጠይቅህ። ከኣሁን በፊት ብወንድሙም እንዳንተዉ ሲጽፍ ኣንብቤ ተመሳሳይ ሀሳቦችን ማንሳቴን ኣስታዉሳለሁ።
አፈር ነዉ ወይስ ኣእምሮ ነዉ የሚሰለጥነዉ?
ስልጣኔ ማለት ኣይኖች አፈር ላይ የምያዩት ነዉ ወይስ አእምሮ የሚገነዘበዉ ኣንደበት ነዉ፧
ያለ ስልጣኔ አንደበተ ርቱዕ መሆን ይቻላል? ሎሬት ጸጋዬ የቦረናን ሰዉ አንደበተ ርቱዕ ያለዉ ከግማሽ ምዕተ ዐመት በፊት ነዉ።
የሚከተሉት ሁለት አጫጭር ዓረፍተ ነገሮች እዉነት ናቸዉ ወይስ ሃሰት?
፩) ስልጣኔ ጦር ከመወርወር ይልቅ በአንደበት መርታት ነዉ።
፪) የስልጣኔን ማነስ ከእርጥብ አፈር ይልቅ እርጥብ አእምሮ ይገልጻል።
በመጨረሻም አፈር እና ድንጋይ መከመር መቻል ብቻዉን ስልጣኔን የሚገልጽ ከመሰለህ ጥንት ጊዜ አክሱም እና ግብጥ የተከመሩት በቂ ማስረጃዎች ኣይዴሉም? ወይስ አክሱም እና ግብጥ ለቦረና ምኑ ናቸዉ ባይ ነህ?
የምታዉቀዉ ጃል ጅሎ የምለዉ የአቡሽ ዘለቀ የረቀቀ የባህል ዘፈን ስልጣኔን ከማያዉቅ ማህበረስብ ሊፍልቅ ይችላል?