On Sep 21, 2021

የሱዳን መንግስት ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መካሄዱን የሀገሪቱ መንግስት ሚዲያ አስታውቋል።
በተለያዩ ሚዲያዎች አሁን እንደተዘገበው ማንነታቸው ያልተገለጸው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ አካላት በካርቱም ኦምዱርማን የሚገኙትን የሀገሪቷን የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለመቆጣጠር ሙከራ ማድረጋቸውም ነው የተገለፀው፡፡ መንግስት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
በአሁኑ ሠዓት ታንኮች ወደ ኦምዱርማን ድልድይ እና ወደ ሀገሪቷ ፓርላማ ህንፃ ተጠግተው መንገዱን በመዘጋት እንደተቆጣጠሩት ሲገለፅ በአካባቢው የጸጥታ አካላት እንደተሰማሩም ነው የተመላከተው፡፡
በካርቱም የሱዳን የጸጥታ አካላት ናይልን ከኦምዱርማን የሚያገናኘውን ድልድይ ቢዘጉም፣ በአካባቢው ሁኔታዎች ተረጋግተው እንቅስቃሴዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ መቀጠላቸው ነው የተሰማው፡፡


