ይህን ፎቶ ተመልከቱ።
በዚህ ጦርነት፣ እንደ ኦሮሞና የኢትዮጵያ ህዝበ ሙስልም፣ ለዳግም ባርነት እራሱን ለማጥፋት እየሰራ ያለ የለም።
አሁን ያለው ጦርነት ዋና ዓላማ የሚንልክና ኃይለስላሴ ግዜን በኢትዮጵያ ለመመለስ የሚደረግ የዘረኞቹና የፋሽስቶቹ ጦርነት ነው።
ለማወናበጃ ካልሆነ በስተቀር፣ ይህን ጦርነት ከኢትዮጵያ ህልውና ጋር የሚያገናኝ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ማለት የአማራ ክልል ነው ካልተባለ በስተቀር።
በዚያ የምንልክ የባሪያ አሳዳሪ ዘመንና በሃለስላሴ የጭሰኛ ዘመን የሙስልሙና የኦሮሞ ህዝብ ቦታ ምን እንደነበረ ይታወቃል።
ሙስልሙ፣ የክርስቲያን ደሴት በነበረችው ኢትዮጵያ፣ አገር አልባ ነበር።
ኦሮሞ ደግሞ መሬቱንና ማንነቱን ተቀምቶ ጭሰኛ ነበር።
ኦሮሞና ሙስልም በኢትዮጵያ እውቅና ያገኙትና ትንሽ መተንፈስ የቻሉት በደርግና በህወሃት ዘመን ነው።
አሁን በደርግና በህወሃት በከፊል የፈረሰውን የዘረኞችና ፋሽስቶቹን አገዛዝ መልሶ እራሱ ላይ ለመጫን፣ ኦሮሞና የኢትዮጵያ ሙስሊም በዚህ ጦርነት የሚሳተፍበት ምክንያት አለ?
የኦሮሞ ህዝብና ህዝበ ሙስልሙ ለተቀሩት መብቶቹ መከበር መታገል አንድ ነገር ነው።
ለዳግም ባርነት መታገል ግን በዓለም ታርክ ታይቶም፣ ተሰምቶም የማይታወቅ እንቆቅልሽ ነው።
ፎቶው፣ ከStalin Gebreselassie ገፅ የተወሰደ ነው።

Please wait, video is loading...



