የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ያደረጉትን ውይይት በድጋሚ ሰማሁት። የትውልድ አገሬ ኢትዮጵያ የገባችበት ቀውስ በየጊዜው የአለም ሕዝቦችን እያሳሰበና እያስጨነቀ መወያያ መሆኑ አስቆጨኝ። አናደደኝ። አንገቴን አስደፋኝ።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ስግብግብነት፤ ራስ ወዳድነት፤ የስልጣን ጥመኝነት፤ ዘረኝነትና አክራሪነት ምክንያት ከቱባ ትውፊቶቿ ተናጥባ እና ተፈጥፍጣ የዝቅተኛ ዘመኗ ላይ መድረሷ እርግጥም ሀሞት የሚያስተፋ ቁጭት ይፈጥራል።
Ermias Legesse