Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ሽኝት ተደረገ (Fana)

Post by sarcasm » 24 Aug 2021, 10:50

የ "ፍቅር ያሸንፋል" በጎ ኣድራጎት ማህበር ኣባላት ወደ ግንባር ዘምተዋል 😃 😃
ዝምብለን ህወሗት ሃሺሽ ትጠቀማለች ኣልን እንጂ ሁላችንም ነን የጦዝነው 😃 😃

https://www.facebook.com/surad.qayel/po ... 4200452913

ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀገርን ህልውና ለማስከበር በግንባር ለመሰለፍ ዝግጁ ለሆኑ የፍቅር ያሸንፋል በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ሽኝት ተደረገላቸዉ።
የማህበሩ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚስባህ ከድር ፥ እንደ ሌሎች ማህበራትና ሀገር ሽማግሌዎች ዕርቅ እንዲወርድ እና ሁሉ ነገር በፍቅርና በይቅርታ እንዲታለፍ መቀሌ ቢሄዱም አለመሳካቱን ተናግረዋል።
እኛ ኢትየጵያውያን እያለን ኢትየጵያ አትፈርስም በማለት ሀገር ለመታደግ ቀጣይ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የመከላከያ ሚዲያ ሥራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብ/ጄኔራል ኩማ ሚደቅሳ በበኩላቸው ፥ የፍቅር ያሸንፋል ማህበር ለሚሠራው በጎ ተግባር ምስጋና አቅርበው ፣ ጁንታው ለራሱ ጥቅም ሲል በሠራዊቱና በህዝቡ ላይ ይቅር የማይባል ክህደት ፈጽሟል ሲሉ ተናግረዋል።
አሸባሪው ህወሓት ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ ቢነሳም አንድ አድርጎናል ፣ ይህ ሀገራዊ አንድነትም ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
ለሠራዊቱ ደጀን ለመሆን ወደ ግንባር ለሚዘሚቱ 50 ወጣቶች በድል እንዲመለሱም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ፣ የማህበሩ አባላት ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ የትግራይ ክልል ተወላጆች እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮችም የተገኙ ሲሆን ፥የትግራይ ዲሞክራስያዊ ፓርቲም አሸባሪውን ጁንታ ቡድን ለመደምሰስ ከፍቅር ያሸንፋል ማህበር አባላት ጋር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Please wait, video is loading...
https://www.facebook.com/surad.qayel/po ... 4200452913