Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Educator
Member
Posts: 2370
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

ማን ነበር ህወሃት አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ነው ያለው ያለው?

Post by Educator » 21 Aug 2021, 17:29

#አረመኔያዊ ዜና

በፋሺስቱና አንባገነኑ የአብይ አህመድ ብልፅግና መንግስት ስር ያለው የቂሊንጦ አስተዳደር እና ፖሊሶቹ ዛሬም ከሠዓት በተለመደው የመጠየቂያ ሠዓት ለጿሚዎቹ እስክንድር ነጋና ስንታየው ቸኮል መታወቂያዬን አሳይቼ ምሳ ይዤ ከገባሁ በኋላ ውስጥ ያሉት ተረኞቹ ጥበቃ ሀላፊዎች እነ እስክንድር ጋር መሆኔን ስላወቁ አይቻልም ብለው ምሳውን እንኳን ለማቀበል ብለምናቸው አይሆንም ከዛሬ ጀምሮ የምሳ መስጫ ፕሮግራም ተቀይሯል ብለው ከልክለው መልሠውኛል።

በጥላቻ ባአበደው አረመኔው ናዚ ኮማንደር ጫላ የሚመራው ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ምንም አይነት ማስታወቂያ ባልተለጠፈበት ሁኔታ እና ለጠያቂ ቤተሠቦች ሳይነገርና እና ሳያሳውቅ በፈለገው ግዜ እና ሠዓት የመጠየቂያ ሠዓትን እየቀያየረ እና ሲያሻው እየከለከለ ለእስክንድር ነጋና ስንታየው ቸኮል እንዲሁም ለኛ ለጠያቂዎቹ ከህወሃት ወያኔው ግዜም በላይ ለመጠያየቅ እንዳንችል እጅግ አዳጋች አድርገውብናል።

ከዚህ በተጨማሪም እኔ እዛው እያለሁ ከፖሊሶቹ ጋር ስከራከር እነ እስክንድርን ለመጠየቅ የመጣ ዘመነ የሚባል የአዲስ አበባ ነዋሪና የእስክንድር ዘመድ ቂሊንጦ ድረስ መቶ እጅግ እያዘነ ከነ ስንቁ እንዲመለስ ተደርጓል።

ማን ነበር ህወሃት አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ነው ያለው ያለው?

#Alex Sheger