Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

መቆሚያችን መረብ ወንዝ ብቻ ነው!

Post by Za-Ilmaknun » 10 Aug 2021, 13:16

:mrgreen: በትናንትናው አውደ ውጊያ ከጋይንት መስመር ወደ መቄት ያቀናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፋኖ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ እንዲሁም የጋይንት ታጣቂ ህዝብ እንዲሁም ወጣቱ ሴት ወንድ ሳይል በወያኔ ቡድን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። ወያኔ ይዛው የመጣችው አራት መድፍ በመከላከያ ከባድ መሳሪያ ዶግ አመድ ሆኗል። ከዚህ በፊት የዘረፈችው አንድ ታንክ ገቢ ተደርጓል። በአሽሽ ጦዞ የመጣው የወንበዴ ቡድን እንደ ሸንኮራ እየታጨደ ወድቋል።

ከፍተኛ ምት የደረሰበት ወያኔ በአፈ ቀላጤው በኩል ደቡብ ጎንደርን እየሸነሸነው ነው ብሎ ፅፏል አሉ። መሸንሸን ምን እንደሆነ በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይል አሳይቶታል። እነዚህ ሰዎች ጦርነት ምን ማለት እንደሆነ ትናንት በነበረው ውሎ ተረድተዋል። በእርግጠኝነት የምንናገረው ይህ ቦታ የወያኔ መቀበሪያ እንደሚሆን ነው። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ወንበዴ ቡድን ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልተሳካለትም። በወገን ጦር በኩል የደረሰ ጉዳት እዚህ ግባ አይባልም። ቀላል ቁስለት ብቻ ተመዝግቧል። በተቃራኒው ያለው ወንበዴ እየበረረ የመጣው ሁሉ በወገን ጦር ቅንጅት በመቄት ተራሮች ስር ተደፍቶ እንዲቀር አድርጎታል።

የመከላከያ ተጋድሎ የሚደንቅ ነበር። ኮማንዶው ይዋጋል አይገልፀውም። የልዩ ኃይላችን ትብብር ግሩም ነው። ፋኖ ጦርነትን ይሰረዋል ማለት ይቻላል። ህዝባዊ ኃይሉ የሚደንቅ ተጋድሎ አድርጓል። ቁስለኛ በማግለል፣ ምግብ በማቅረብ የአካበቢው ህዝብ ያሳዬው መሯሯጥ ታሪካዊ ነበር። የደቡብ ጎንደር ዞን እና የአካባቢው አስተዳደር፣ ከክልል የመጡ አመራሮች ያሳዩት አመራርነት የሚያስመሰግን ነው። ታሪክ የማይረሳው መናበብ እና ተጋድሎ ተደርጓል። ዛሬም እየፈረጠጠ ያለውን የወያኔ ኃይል የወገን ጦር ከኋላ ደርሶ እያካለበው ነው። መቆሚያችን መረብ ወንዝ ብቻ ይሆናል...!

ጋሻው መርሻ

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: መቆሚያችን መረብ ወንዝ ብቻ ነው!

Post by Za-Ilmaknun » 10 Aug 2021, 21:07

ሰበር ዜና‼️
===
ምሽቱን የጁንታው አመራሮች መተራመስ ጀምረዋል። ከማጨው አከባቢ ወደ መቀሌ ከመሸ የገቡት የተወሰኑ አመራሮች መጠነኛ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን መቀሌ ከቆዩት ውስጥ የተወሰኑት ከተማውን ለቀው ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ታጣቂዎች መንገዱን ዘግተው ነገ ይደረጋል ከተባለው ስብሰባ በፊት ማንም ሰው ከከተማ አይወጣም ብለው እየጠበቁ እንደሆነ ተነግሯል። መቀሌ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ስትሆን የርዳታ ሰራተኞች የውጭ ሃገር ዜጋ የሆኑትም ያልሆኑትም ባስቸኳይ መቀሌ ወዳለው የስምሪት ጣብያ እንዲመጡ ዛሬ ተንግሯቸዋል።

Post Reply